አስፈላጊ ሆና ስላገኘዋት እንዲ አድርጌ አቅርቤዋለው በአገራችን በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እንዴት ነው ነገሩ? የሚያሰኝ ዕድገት የማይታይባቸው ብዙ ዘርፎች አሉ፡፡በተፃራሪው ደግሞ ፈጣን ዕድገትና መሻሻል ሲጠበቅ ሒደቱና ውጤቱ ግን ‹‹የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ልኳንዳ ተገኘ›› የሚለው የአበው ተረት የሚተረትባቸው ዘርፎችም አሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ሕንፃዎችና ሰፋፊ መንገዶች ተገንብተዋል፤ አሁንም እየተገነቡ ናቸው፡፡ የከተማ ቀላል የባቡር መስመር እየተዘረጋ ነው፡፡ በርካታ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ የንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሕክምና ተቋማት፣ ወዘተ በብዛት ተገንብተዋል፡፡ ይህን ስናይ ይበል እንላለን፡፡ ከተማችን ከጥቂት ቀደምት የአፍሪካ ከተሞች አንዷ ሆና ስናያትም እንኮራለን፡፡ እውነትም የአፍሪካ መዲና እንላለንም፡፡ በሀቅ! ከልብ፡፡ዲሞክራሲን መጎልመስን አትወክልም! እንደውም ብሶበታል! እውነቴን ነው ምነው ፈራቹ መስክሩ እንጂ?
Thursday, February 28, 2013
የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል
“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ አዲስ የሚሾሙትን ፓትሪያርክ ህዝቡ እንዳይቀበል ጥሪ አቀረበ
ሲኖዶሱ በላከው መግለጫ አገሪቱን እስር ቤት አድርጎ ህዝቡን በባርነት ለመግዛት የተነሳው ሀይል የቤተ ክርስቲያንን ሀዋርያዊና የነጻነት አንደበት ለመዝጋት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች ተቀዳሚውና ዋነኛው ለህገ ቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ ፈቃድ ተገዢ የሆነ ሰው በፓትሪያርክ ስም በቤተ ክርስቲያን መንበር ላይ በማስቀመጥ ቤተክርስቲያንን መድፈር ነው ብሎአል።ሲነዶሱ ” ላለፉት 21 አመታት በመንግስት አስተባባሪነትና ደጋፊነት በህገ ወጥ መንገድ በተቀመጡት አባት ምክንያት ቤተ ክርስቲአንን ክፉኛ የጎዳው መከፋፈል እና መለያየት ሳያንስ አሁን ደግሞ እነዚህ ጥቂት አባላት በስልጣን አለውን የመንግስት ሀይል መከታ አድርገው ፓትሪያርክ ብለው የሚሰይሙትም ፣ አባትነቱ የሀሰት አባት፣ ሹመቱም የሲሞ ን መሰርኢ ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ያወግዘዋል።
Wednesday, February 27, 2013
Humanity before ethnicity
Motivated by the truth
that no one will be free until all are free, we envision an open, free and
reconciled society in Ethiopia, a society where humanity comes before ethnicity
and where the same rights, opportunities and privileges are available to all.
We work to mobilize Ethiopians in the Diaspora and within Ethiopia to unite in
a coalition across ethnic, regional, political, cultural and religious lines
around principles of truth, justice, freedom, civility, equality and the
protection of human rights.
Tuesday, February 26, 2013
ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!
እንደ ጉርሻ
በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
‹‹ሐይማኖቴን፣ሐሳቤን፣መብቴን፣ የመግለጽ ነጻነት አለኝ ››
ነፃነት ዘመቻ የምደግፈው የዚህኛው ወይም የዚያኛው ርዕዮተዓለም ደጋፊ ስለሆንኩ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ የሐሳብ ነጻነት ፈላጊ ነኝ።
(Freedom of Religion,Expression, Right) ደጋፊ ነኝ፡፡
(Freedom of Religion,Expression, Right) ደጋፊ ነኝ፡፡
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ተፈጥሮ የለገሰን ነጻነት ነው፡፡ ሰው ሁሉ ሐሳብ አለው፤ ሐሳብ ያለው ሁሉ የመናገር ተፈጥሯዊ ተሰጥኦ አለው፤ በሕገ-መንግሥቱ እስከተፈቀደልኝ ድረስ ይህንን ተፈጥሯዊ ስጦታዬን መጠቀሜ እና የሌሎችን ማክበሬ ለማንም ወገንተኛ ብሆንም ባልሆንም የማምንለት እና የከራከርለት ነው፡፡
የሚያዝያው ምርጫ ነጠላ አልበም - Quick Fix!
የመብራት ኀይል “ትራንስፎርመር” ተቃጠለ (ትራንስፎርሜሽኑስ?)
ቴሌኮም “ሲምካርድ ከእኔ፤ ኔትዎርክ ከእናንተ” ቢለን ይሻላል
ምርጫ ቦርድ “ምርጫው እንጂ ምህዳሩ አያገባኝም” ብሏል
ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የሞባይሌ ቴክስት ሜሴጅ (SMS) ድምፅ ነው፡፡ በጣም ተናደድኩኝ፡፡ ሰዓቱ እኮ ገና አንድ ሰዓት አልሆነም፡፡ ቀን ቀን በኔትዎርክ መጨናነቅ ከአገልግሎት ክልል ውጭ የሚሆነው ሞባይሌ በዚህ ሌሊት እንዴት ይረብሸኛል? ይሄኔ እኮ የራሱ የቴሌኮም ማስታወቂያ ይሆናል… ብዬ አሰብኩ፡፡ “የ100 ብር ካርድ ስትሞሉ 15 ደቂቃ ነፃ የአየር ሰዓት ታገኛላችሁ” የሚለው አይነት ማለቴ ነው (ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ!) ሌላ ሌላው ማትጊያ ቀርቶብን ኔትዎርክ ብናገኝ እኮ ይበቃን ነበር፡፡ አሊያም ደግሞ ሃቁን በይፋ ቢነግረን ቁርጣችንን እናውቀዋለን፡፡ “አያችሁ ከዛሬ ጀምሮ የኔትዎርክ ጉዳይ አይመለከተኝም፤ ሲም ካርድ ከእኔ፤ ኔትዎርክ ከናንተ” ቢለን እኮ አርፈን እንቀመጣለን፡፡ ወይም ኔትዎርክ ከቻይና እናፈላልጋለን ፡፡
ቴሌኮም “ሲምካርድ ከእኔ፤ ኔትዎርክ ከእናንተ” ቢለን ይሻላል
ምርጫ ቦርድ “ምርጫው እንጂ ምህዳሩ አያገባኝም” ብሏል
ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የሞባይሌ ቴክስት ሜሴጅ (SMS) ድምፅ ነው፡፡ በጣም ተናደድኩኝ፡፡ ሰዓቱ እኮ ገና አንድ ሰዓት አልሆነም፡፡ ቀን ቀን በኔትዎርክ መጨናነቅ ከአገልግሎት ክልል ውጭ የሚሆነው ሞባይሌ በዚህ ሌሊት እንዴት ይረብሸኛል? ይሄኔ እኮ የራሱ የቴሌኮም ማስታወቂያ ይሆናል… ብዬ አሰብኩ፡፡ “የ100 ብር ካርድ ስትሞሉ 15 ደቂቃ ነፃ የአየር ሰዓት ታገኛላችሁ” የሚለው አይነት ማለቴ ነው (ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ!) ሌላ ሌላው ማትጊያ ቀርቶብን ኔትዎርክ ብናገኝ እኮ ይበቃን ነበር፡፡ አሊያም ደግሞ ሃቁን በይፋ ቢነግረን ቁርጣችንን እናውቀዋለን፡፡ “አያችሁ ከዛሬ ጀምሮ የኔትዎርክ ጉዳይ አይመለከተኝም፤ ሲም ካርድ ከእኔ፤ ኔትዎርክ ከናንተ” ቢለን እኮ አርፈን እንቀመጣለን፡፡ ወይም ኔትዎርክ ከቻይና እናፈላልጋለን ፡፡
Monday, February 25, 2013
ማስተዋል ከልብ! ልብ ያለ ልብ ይበል !
ከ3000 ዓመት በላይ በሐይማኖት፣
በበዓል፣በታሪክ ተደጋግፋ ያለችውን ሀገር በ21 ዓመት አምባገነናዊ የወያኔ ስርዓት ለመቀየር መሞከር የማይሳካ የህልም እንጀራ ነው!!
የኢህአዴግ/ ህውሃት መንግስት ከሙስሊሙ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ጋር ለማጣመር ያሰበውን አረመኔያዊ የጭካኔ የሽብር ስራ እጅግ ጥብቅ በሆኑ ታማኞቹ እየተሰራ አንደሆነ ያውቃሉ ??
የኢህአዴግ/ ህውሃት መንግስት ከሙስሊሙ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ጋር ለማጣመር ያሰበውን አረመኔያዊ የጭካኔ የሽብር ስራ እጅግ ጥብቅ በሆኑ ታማኞቹ እየተሰራ አንደሆነ ያውቃሉ ??
UN Held Talks About Ethiopian Asylum Seekers In Norway
Finally, the international community gives concern for Ethiopian refugees in Norway. Human right defenders are still struggling against the repatriation agreement held on Jan 26,2012 between the dictatorial Meles regime and the Norwegian government.
የኢትዮጵያ ተቀዋሚዎች ሁሉ ተባበሩ
ትግሉ የሥልጣን ብቻ ሳይሆን የርዕዮተ ዓለምም ነው!
ካርል ማርክስ “የዓለም ሰራተኞች ተባበሩ፤ ከሰንሰለቱ በስተቀር የሚቀርባችሁ ነገር የለም ብሎ ነበር”፤ እኔም እላለሁ፤ የኢትዮጵያ ተቀዋሚዎች ሁሉ ተባበሩ፣ ከእስራት ሰልሰለቱ በስተቀር የሚቀርባችሁ
ምንም ነገር የለም (All
Ethiopian Oppositions, Unite! You have nothing to lose but your chains) እዚህ ላይ ማርክስን መጥቀሴ ማርክስሲት ሆኜ አይደለም፤ አባባሉ እውነትነት ያለው ሆኖ ስለአገኘሁት
እንጂ! ለነገሩ ማርክስን በደንብ ሳያውቁ ማርክሲስትም ፀረ ማርክስሲትም መሆን አይቻልም።
በወጣቱ ትውልድ ላይ ኢንቨስት ይደረግ!
በወጣቱ ትውልድ ላይ የተለያዩ ወቀሳዎች ሲሰነዘሩ ይሰማል፡፡ ‹‹የጫትና የሺሻ ትውልድ ሆነ፤ ስደት ይወዳል፤ በአቋራጭ ሀብታም መሆን ይፈልጋል፤ ሥራ አይወድም፤ ሞራልና ሥነ ምግባር የለውም፤ ስለታሪክ ደንታ የለውም፤ ኢትዮጵያዊነት አይሰማውም…›› ወዘተ፣ ወዘተ የሚል፡፡እንደዚህ ዓይነቱ አመለካከት ከመነሻውም ስህተት ነው፡፡ መድረሻውም አያምርም፡፡ ከወዲሁ ሊታረምና ሊስተካከል ይገባል፡፡ ወጣቱ ትውልድ ጠንካራ ሠራተኛ፣ አገር ወዳድ፣ በሥነ ምግባር የተሞላ፣ የበለፀገና ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ መሆን አለበት፡፡ ይህን ለማድረግ ግን በወጣቱ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል፡፡ወጣቱን ጠንካራና ስኬታማ ትውልድ ለማድረግ ‹‹ወላጆች ይምከሩ›› ወይም ‹‹መንግሥት ይርዳው›› ተብሎ የሚተው ጉዳይ አይደለም፡፡ ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብና መንግሥት በጋራ የሚሸከሙትና የሚወጡት ኃላፊነት ነው፡፡
Friday, February 22, 2013
WE NEED FREEDOM OF EXPRESSION
I like this freedom of
expression campaign that was kicked off by online democracy activists. We
should aim at convincing many Ethiopians to appreciate the value of freedom of
speech and expression.
እርስ በእርስ መሻኮት ይብቃን
“ነጻ ስለመሆን የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ሰው በሰውነቱ የሚከበርበት አገር እስከምንመሰርት ድረስ እንታገላለን። የብሶታችንና የትግላችን መነሻ ለናንተ ለኔ አዲስ ትግል አይደለም” መብታችን ይከበር ነው የምንለው፣ ነፃነት ያስፈልገናል፣ማንም እንዳሻው ተነስቶ ህወሃትን አምልኩ እንዲለን አንፈቅድም!
ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ እየተሻኮትን ለወያኔ እድሜ የምንጨምርለት? ፖለቲከኞቹሰ ብንሆን የምንታገለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ነው ካልን ልዩነታችንን አጥበን አንድ ላይ ማበር ያልቻነው ለምንድን ነው?
Thursday, February 21, 2013
አይ ባይ ያጣው ህውሃትና ጀሌዎቹ!
በመነኮሳት ስም ያደራጃቸው አባላቱም በቤተ ክህነቱ የተለያዩ እርከኖች ላይ በመቀመጥ ቤተ ክርስቲያናችን የክርስቶስ ሳይሆን የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ዓላማ ማስፈጸሚያ እንድትሆን አስገድደዋታል። ወታደራዊው መንግሥት እንኳን ያላደረገውን የቤተ ክህነቱን መዋቅር ከዋናው እስከ አጥቢያው ካባ በለበሱ ካድሬዎች በማደራጀት ቤተ ክርስቲያኒቱ የክርስቶስ መንግሥት ሳይሆን የህውሃተና ጀሌዎቹ! አገልጋይ እንድትሆን አድርገዋታል።
Subscribe to:
Posts (Atom)