Thursday, May 2, 2013

ሰበር ዜና: በእነ አንዱዓለም አራጌ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለለፈው ፍርድ በ/ጠ/ፍ/ ቤት ፀና፡


በእነ አንዱዓለም አራጌ እና በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለለፈው ፍርድ በ/ጠ/ፍ/ ቤት ፀና፡፡ እነ አንዱዓለም አራጌ ያቀረቡትን ይግባኝ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ጠ/ፍ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 24 ቀን 2ዐዐ5 ዓም በሰጠው ብይን፣ ይግባኝ ባዮች በሽብርተኛነት ተግባር ላለመሳተፋቸው አሳማኝ የሆነ መከላከያ አላቀረቡም ብሏል፡፡ በዚህ የተነሳ የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አፅንቷል፡፡

“እውነት ተደብቆ አይቀርም” እስክንድር ነጋ (ከፍርዱ በኋላ በችሎት ውስጥ)  “የተከራከርነው ፍትህ እናገኛለን ብለን አይደለም፤ ፍትህ ወዳድ በመሆናችን ነው” ናትናኤል
“ የእኛን ጉዳይ ለመከታተል እዚህ ስለተገኛችሁ እናንተ የእኛ ጀግኖች ናችሁ” አበበ ቀስቶ “የእስክንድር ወንጀል አገር መውደድ ብቻ ነው” (ሰርካለም ፋሲል- ከፍ/ቤት ውሳኔ በኋላ)
“ግንቦት ሰባት የእስክንድርን እጅ የመጠምዘዝ ኃይል የለውም” (ሰርካለም ፋሲል በችሎት ውስጥ የተናገረችው)

No comments:

Post a Comment