Friday, June 28, 2013

አዛዛኙ ክስተት !!! ከ 110 በላይ ኢትዮጵያዊ ባህር ላይ ቀሩ


xc

ስለ ስደተኛው የቁራሌው ጩኸት እስከ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ….
በግሩም ተ/ሀይማኖት
…ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ተቃዋሚ ሀይሎች ከጅቡቲ ወስደው መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው ነበር፡፡ ብዙ እናውቀለን…›› ይህን በስደት ዙሪያ የአዞ እንባ ያነባው ኢቲቪ ለውይይት ከጋበዛቸው ውስጥ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ያዳለጣቸው ነው፡፡ ያዳለጣቸው ያልኩት መንግስት ያን ሁሉ ማስመሰያ ያደረገበት ምክንያት ምን እንደሆነ አባሳደሩ በግልጽ ሳያውቁ ስላስቀመጡት ነው፡፡ የስደተኛው ህይወት አሳዝኗቸው አይደለም፡፡

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው

ከኢየሩሳሌም አርአያ
ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ “አላማና ግብ” አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ “በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ።” ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው።

***ታሪክ መማሪያ እንጂ የዘር መቁጠሪያ መሳሪያ አይደለም!***

አንድ ሰው የአፄ ቴወድሮስን ታሪካዊ ጀግንነትና ራዕይ ለመዘከር የግድ ጎንደር መወለድ የለበትም፥ አፄ ዮሐንስ ለሀገራቸዉ የከፈሉትን መስዋትነት ለማመን የግድ ትግራይ መወለድ የለበትም ፣የአፄ ምንሊክን የአድዋ ጀግነነት ለመመስከር ሽዋ መወለድ የግድ አይልም፣ የአብዲሳ አጋን ከኢትዮጵያ እስከ አዉሮጳ የዘለቀ አርበኝነት ለመቀበል ወለጋ መወለድ ወይም ኦሮሞ መሆን አያሻም:: የነበላይ ዘለቀ፣ አሉላ አባነጋ እና የሌሎችን ኢትዮጵያዉያን ጀግኖችን ታሪክ ለመቀበል የግድ እነሱ ከተገኙበት አካባቢ መወለድ አያስፈልግም ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ እና ያልተጠቀሱ ጀግኖች መስዋትነት የከፈሉት እና የተዋጉት ለሀገራቸው እንጂ ለአካባብያቸዉ እና ለብሄራቸዉ ነው የሚል የታሪክ ድርሳን እስካሁን አላየሁም ነገር ግን በዘመናችን የተንሸዋረረ የፖለቲካ መነፅር እያዩ እንደዚህ የሚያወሩና የሚያስቡ ሠወች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም:: ከዚህ ላይ ታሪካዊ ሰዎች በተለይ መሪዎች ሰዉ እንደመሆናቸው መጠን በዘመናቸው የሰሩት ጥፋት ይኖራል ስለዚህ ጥንካሬአቸውን ማድነቅና መውሰድ ከድክመታቸውም መማር እንጅ በጎጠኝነት አስተሳሰብ ታጥሮ የጎጣችን እና የብሄራችን የሆነዉን ፍፁም እንደሆነ አድርጎ ማሞገስ የሌላዉን ምንም ቁም ነገር እንዳልሰራ ጥፋቱን እያጋነኑ ማራከስ እኛን ቢያስገምተን እንጂ እነሱ የሰሩትን ታሪክ አይቀይረዉም ::

ከሰብኣዊ

***ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል።***

***ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል።***

ተፈጥሮ የለገሰችንን ነፃነት ሰው መንጠቅ አይችልም።
ኧረ ማንም!!
ነጻነት እኛ ሰዎች በልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ።
ደስ ሲል!
 ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንም ስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲለየን መፍቀድ የሌለብን ኃብት ነዉ።
ደስ ሲል!
ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበት፤ እንዳንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደወያኔ አይነቱ ፀረ ህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግለን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ።
እውነት ነው።
 እኛ ኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ  ይህንን ፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትን ነዉ።
እውነት ነው።
መፈናቀላችን፤ ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ  ስንታገልት ብቻ ነዉ።
እውነት ነው።
ወገን ሁሉ ለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊ ግዴታውን እንዲፈጽም ለራሱ ጥሪ ማቅረብ አለበት።
ቅስቀሳ አያስፈልግም!

Thursday, June 27, 2013

ኢሳት


(በደረጀ ሀብተወልድ)

ከሁለት ሣምንት በፊት ኢትዮ- ሲቪሊቲ ፓልቶክ ባዘጋጀው የጋዜጠኞችና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ውይይት ላይ ኢሣትን በመወከል ተሳትፌ ነበር። በክፍሉ ታዳሚ ከነበሩት 500 በላይ ተሳታፊዎች መካከል በጣም የሚበዙት የኢሳት ደጋፊዎች መሆናቸውን ሳይ ደስታ ሳይሰማኝ አልቀረም። ከደስታው ባሻገር የተሰማኝ ሌላ ስሜት ግን፦ሰው እንደዚህ ሲደግፋችሁ፤ የበለጠ በርትቻችሁና ጠንክራችሁ መሥራት አለባችሁየሚል አደራዊ ሸክም ነው።
ደጋፊዎቻችን የመብዛታቸውን ያህል ታዲያ ከጥቂት ሰዎችም ቢሆን ቅሬታ አዘል ጥያቄዎች መሰንዘራቸው አልቀረም።ኢሳትን በተመለከተ የተሰነዘሩት እነዚህ ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች ሲጨመቁ፦ኢሳት የግንቦት 7 ነው፣ ግንቦት 7 እና መሪዎቹ ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ያገኛሉ፣ ጭራሽ የሚዲያ ሽፋን የማትሰጧቸው ፓርቲዎች አሉየሚሉ ናቸው።
ለሦስቱም ጥያቄዎች ለመስጠት የሞከርኩትን መልስ ነው እዚህ በመልኩ ለማስቀመጥ የሞከርኩት፦
1-
ኢሳት የግንቦት 7 ነው የሚለውን በተመለከተ፦

ዋልድባ ገዳም በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ

June 26, 2013


በታሪካዊው በዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ሰበብ እየደረሰ ያለውን ችግርና በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ፣ ከዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እናድን ኮሚቴ) የተሰጠ መግለጫ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Wednesday, June 26, 2013

ሚሚ ስብሃቱና አያ ጅቦ

እንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በቅርቡ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል አቢይ ርዕስ የህዝባዊ ንቅናቄ ጥሪ ለህዝብ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡አንድነት በዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ የአንድ ሚልዮን ዜጎችን ፊርማ በማሰባሰብ የዜጎችን የማሰብ፣ የመናገር ፣በነጻነት የመደራጀትና ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ጨምሮ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጋጫል ያለውን የጸረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝ ህጋዊ መስመርን በመከተል ጫና እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ መግለጫ ተከትሎ የዛሚዋ ሚሚ ስብሃቱ በምትመራው ‹‹የጋዜጠኞች የክብ ጠረጴዛ ››የውይይት መድረክ የአንድነትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከግብጽና ከግንቦት 7 ጋር በማቆራኘት ‹‹ፓርቲው ይህንን እንቅስቃሴ ያደረገው የህዳሴው ግድብ እንዳይሳካ ከሚፈልጉ ሀይሎች የገንዘብ ድጉማ ተደርጎላቸው ነው፡፡››በማለት የወረደና የተለመደ ፍረጃዋን አስደምጣለች፡፡