Sunday, August 4, 2013

***በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቀናቃኝነት ከአባት ገዳይ በላይ ጠላትነት የሚታይበት ነው፡፡***

በዳበረ ዲሞክራሲ ውስጥ ያለ ሕዝብ ሀብታም ወይም ደሃ፣ ነጭ ወይም ጥቁር፣ ሒስፓኒክ ወይም እስያዊ ወይም ነባር ሕዝብ፣ ወጣት ወይም አዛውንት፣ አካለ ሙሉ ወይም አካል ጉዳተኛ፣ ዲሞክራት ወይም ሪፐብሊካን፣ ወዘተ በድምፃቸው ልዩነት መፍጠራቸው ነው የተወሳው፡፡ ‹‹እንደ ፖለቲካችን የተከፋፈልን ሳንሆን የጋራ ራዕይ ያለንና የወደፊቱን የምናልም ነን፤›› ነበር ያሉት ኦባማ፡፡ ከግለሰባዊ ፍላጎታችን ይልቅ አሜሪካዊነታችን ይቀድማል በማለት ነው የገለጹት፡፡ ለነገሩ የዲሞክራሲ ትልቁ መገለጫ ልዩነት አይደል? የተለያዩ አመለካከቶች መኖራቸው የተሻለውን ለመምረጥ ስለሚያግዝ ሁሌም ‹‹ልዩነት ለዘለዓለም ይኑር›› የሚለውን የፈረንሳዮች አባባል መቀበል የግድ ነው፡፡
የእኛ ፖለቲከኞች ልዩነትን እንዴት ያስተናግዳሉ? በተለይ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ የምናውቃቸው ፖለቲከኞቻችን ለልዩነት ያላቸው አመለካከት እንዴት ነው? በልዩነት ውስጥ አንድነትን ለማስተናገድ ያላቸው ፈቃደኝነትስ እንዴት ይገለጻል? እነዚህ ቀለል ያሉ ጥያቄዎች ሲነሱ ደስ የማይላቸው ወገኖች አሉ፡፡ ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጀምሮ እስከ ተለጣፊ ተቃዋሚ ድረስ ያሉ ፖለቲከኞቻችን ስለ ዲሞክራሲ ሲደሰኩሩ እንሰማለን፡፡ በመካከላቸው የተሰነቀረውን ልዩነት ለመፍታትና ለመነጋገር ያላቸው ዝግጁነት ግን የሚያሳዝን ነው፡፡ የፖለቲካ ተቀናቃኝነት ከአባት ገዳይ በላይ ጠላትነት የሚታይበት ነው፡፡ በአገር ጉዳይ ላይ ተቀራርቦ ለመመካከር አይደለም በሩቅ እንኳን ተሁኖ ሐሳብ ለመለዋወጥ ሲሞከር አይታይም፡፡ ሁሌም አፍራሽ ቃላትን በመጠቀም፣ ‹‹ጎጠኛ፣ ጠባብ፣ ትምክህተኛ፣ ገንጣይ አስገንጣይ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ሽብርተኛ፣ ወዘተ›› በመባባል ለአገር ሊውል የሚችለው ወርቃማ ጊዜና ዕድል ይበላሻል፡፡ አገሪቱ አራት ጊዜ ምርጫ ብታካሂድም ውጤቱን ሁላችንም እንዳየነው ነው፡፡ ከአሜሪካ ጋር አይደለም ከቢጤዎቻችን ጋር እንኳ ሊወዳደር አልቻለም፡፡ በዲሞክራሲ ስም እየተማለ የአምባገነንነት አባዜ ነው የሚታየው፡፡ ገዥው ፓርቲ ተቀናቃኞቹን በሙሉ ለሕዝብ የማይበጁ ብሎ ሲፈርጅ ተቃዋሚዎቹ ሁሉ የአገር ጠላት ናቸው ይላል፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ ጽንፈኛ አቋም ምክንያት ዲሞክራሲን ማሰብ ቅንጦት ሆኗል።
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment