የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ድጋፍ ማሰባሰቢያ በደማቅ ሁናቴ ተጠናቀቀ
ቅዳሜ ሴፕቴበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀና በተሳካ እንዲሁም የሕዝቡ ቁርጠኝነት በታየበት
ሁናቴ ተከናወነ ።
በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ አስተባባሪነት
ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ድጋፍ ለመስጠት የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ
በተሳካና በአማረ ሁናቴ እንዲካሄድ በማድረግ በኖርዌይ የሚገኙ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች
፣የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባሎችና ደጋፊዎች፣በኖርዌይ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከተለያዩ
አገራት ከስዊዲን፣ከኢንግላንድ፣ከሲዊዘርንድ የመጡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን
በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለአገራቸው ለውጥ ለማምጣት የገቢ ማሰባሰቢያውን
ገንዘብ በማዋጣት ለግንቦት 7ሕዝባዊ ኃይል አለኝታ መሆናቸውን አሳይተዋል።