Friday, September 21, 2012

ቁም ነገር ተናጋሪ የሌለበት አገር…………..



      የሚናገረው የማያጣ መንግስት፣ የሕዝቡ አመል የማይታወቅበት ፣ የሚያዳምጠው መሪ ያጣ ህዝብ ።ይህ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ። እኛ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ የሚነገረን እንጂ የሚያዳምጠን መሪ ለማግኘት አለመታደላችን ። ያለመታደል ብቻ ሳይሆን ብናገኝ እንኳን አሜን ብለን ለመቀበል ያልታደልን ፍጥሮች ሆነናል ። ልክ እንደሌሎቹ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ስልጣን የባለስልጣኖች እንጂ የሕዝብ ሆኖ አያውቅም ። በዚህ ሁናቴ ነበር ኢትዮጵያ ውስጥ አዳማጭ ያገኘ ሕዝብ መስለን ስንታይ የነበርነው ። ትንሽ ሰዎች ወይንም የስርሀቱ ደጋፊዎች እንሆናለን አድማጭ አግኝተን መላው ሕዝብ እንዳገኘ አድርገን ስንሰብክ የነበረው በውሸት ለማስመሰል አድማጭ መሪ እንዳለን ስናወራ ከነበረ ግን ውሸት የትም አያደርስምና ዋጋ መክፈላችን አይቀሬ መሆኑንም መረዳት መቻል ይኖርብናል ።  << የህዝብ ይሁንታ >> የሚለውን ቃል መቀለጃ ከሆነባቸው ሀገሮች መካከል አንዷ የኛዋ ኢትዮጵያ እንደሆነች መናገር ደፋር አያስብለኝም ። ደግሞ እናውራው ፣ እንፃፈው ከተባለ ምሳሌውስ ቢሆን ሞልቶ ተርፎን የለ።

Sunday, September 9, 2012

ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ.....

እያወቅን በትርጉም !
      የእድገትና ልማት አብሳሪው ብቻ የሆነውን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሁልጊዜ አንድም ፕሮግራም ሳያስቀር በንቃት እና በትግስት ከሚከታተሉት ውስጥ ነኝ ምክንያቱም ምንም አማራጭ ከሌለው ሰው ስለነበርኩ ። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ፕሮግራሙን ሲጀምር << እንደምን አመሻቹ ዲሽ የሌላችሁ >>  ብሎ የሚጀምር ሳተላይት ቴሌቪዥን ይመስለኛል። ውሸት የመሰራቤቱ ባህሪው ስለሆነ ማለቴ ነው ። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ስመለከት ምን ውሸት ተገኘ ብዬ ሰለምመለከት በትግስቴ ሁሉም ጓደኞቼ የቤተሰብ አባላት እንዲሁም የስራ ባልደረቦቼ እንደተደነቁብኝ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ።

Saturday, September 8, 2012

ኢትዮጵያን አትንኩ አትከፋፍሉ!!



        የኢትዮጵያ የገዥዉ መንግስት፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ተቋማት፣ድርጅቶችና በአጠቃላይ ግለስቦች ኢትዮጵያ የሚያገለግሉ እንጂ ከኢትዮጵያ በላይ አይደሉም :: በኢትዮጵያ ሊጠቀሙና ሊጠናከሩ የሚችሉትም ለኢትዮጵያ ሲሰሩና ለኢትዮጵያ ሲቆሙ ብቻ ነዉ።
     ኢትዮጵያን እያፈረሱ እንድትነካ  እንድትጎዳ እየሰሩና እየተንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ቆሜያለሁ ማለት አይቻልም።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነት፣ የመስመር ልዩነት፣ የአመለካከት ፣የአስተሳሰብና የአፈጻጸም  ልዩነት ሊኖር ይችላል ቢኖርም አያስደንቅም :: የአመለካከት  ልዩነት ያለባትንና ዲሞክራሲ የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለመገንባት ነዉ የምንመኘዉ የምንሰራዉም ነገር ግን የአመለካከትና ሌላም ሌላም ልዩነት ቢኖርም  ኢትዮጵያን በመጠበቅ ፣በማክበርና  በማስከበር  ልዩነት ሊኖረን አይገባም:: እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን ከሆንን ማለት ነዉ።