Saturday, September 8, 2012

ኢትዮጵያን አትንኩ አትከፋፍሉ!!



        የኢትዮጵያ የገዥዉ መንግስት፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ተቋማት፣ድርጅቶችና በአጠቃላይ ግለስቦች ኢትዮጵያ የሚያገለግሉ እንጂ ከኢትዮጵያ በላይ አይደሉም :: በኢትዮጵያ ሊጠቀሙና ሊጠናከሩ የሚችሉትም ለኢትዮጵያ ሲሰሩና ለኢትዮጵያ ሲቆሙ ብቻ ነዉ።
     ኢትዮጵያን እያፈረሱ እንድትነካ  እንድትጎዳ እየሰሩና እየተንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ቆሜያለሁ ማለት አይቻልም።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነት፣ የመስመር ልዩነት፣ የአመለካከት ፣የአስተሳሰብና የአፈጻጸም  ልዩነት ሊኖር ይችላል ቢኖርም አያስደንቅም :: የአመለካከት  ልዩነት ያለባትንና ዲሞክራሲ የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለመገንባት ነዉ የምንመኘዉ የምንሰራዉም ነገር ግን የአመለካከትና ሌላም ሌላም ልዩነት ቢኖርም  ኢትዮጵያን በመጠበቅ ፣በማክበርና  በማስከበር  ልዩነት ሊኖረን አይገባም:: እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን ከሆንን ማለት ነዉ።
      ይኧዉ ዛሬ  የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተዳድረዉ ወያኔ የህዝብ መብት በመንቀፍ ፣ዘረኝነትን በማስፋፋት ፣ሃገርን በመከፋፈል ፣ጎሰኝነትን በማስተማር፣ አገር በመዝረፍ ፣አገርን በመሽጥ፣ ሰዉን ከሚኖርበት ቅዬ በማፈናቀል፣ በመቻቻል እንዳይኖር በማድረግ፣ ዘር ከዘር ጥላቻን ማስፈን፣ ቀጥሎበት ሃያ አንድ ዓመታትን አስቆጠረ። እስከመቸ ይኧን ነገር ዝምብለን ማየት እንችላለን ::
ዘር ለገበሬ ብቻ ነዉ እንጂ ለሰዉ ልጅ ዘሩ ምን ያደርግልሃል ማንፈልጎስ ከማን ዘር ተወለደ።

     የሚያሳዝነዉ ግን በኢትዮጵያና  በኢትዮጵያዊነት ስም ኢትዮጵያን የሚጎዳና የሚነካ እንቅስቃሴ በአገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም እየተደረገ ነዉ:: ዘረኝነትን በማስፈን የሚታወቀዉ ወያኔ ዛሬ ለተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ፈተና እንዳይሆንባችሁ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል :: ልዩነታችሁን አጥባችሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ አብራችሁ ሰርታችሁ ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ እንጂ እንደ ወያኔ በዘር ተከፋፍላችሁ ብትሰሩ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ፣ አንድነት ስላልያዛችሁ ለእኛ ኢትዮጵያን ምን ትጠቅሙናላችሁ?
     የተለያያ የተቋዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ልትኖሩ ትችላላችሁ ቁም ነገሩ ግን የኢትዮጵያን አንድነት ፣ዲሞክራሲ የሰፈነበት አገር ገንብቶ ብሔርን ሳያበላልጥ  የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ አስፍኖ መስራት ተቀዳሚ ተግባር ማድረግ አለባችሁ:: ኢትዮጵያን አትንኩ ፣አትከፋፍሉ!!
     በተቃዉሞ ስም የሚካሄደዉ እንቅስቃሴ በሁለት ይከፈላል ሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ተከትለዉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች አሉ ነገሩ ግን ወዲህ ነዉ ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ግን የሰላማዊዉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ብዙም የሚያስኬድ አይመስለኝም ምክንያቱንም ከምርጫ 97 በኋላ ያየነዉ ይመስለኛል ስለነበረዉም ምርጫ ብዙ ነገር እንደነበር ስለሚታወቅ ምንም ለማለት እንኳ አልቃጣም ዉስጡን ለቄስ ይባል የለ::
ሁለተኛዉ ደግሞ በትግል ላይ ያላችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠናክራችሁና  በርትታችሁ ከሌላዉ የትግል የፖለቲካ ድርጅት ጋር አብራችሁ ሰረታችሁ ልዩነታችሁን አስወግዳችሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመስራት አምባገነኑን የወያኔ መንግስት ለመጣል ከሕዝብ ሆናችሁ መስራት ይጠበቅባቸዋል ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ይጠቅማልም ይደግፋልም ነጻነት የሚሻ ሕዝብ ከዚህ በላይ መስዋትነት ይከፈላልና የአገርን ጥቅምና ኢትዮጵያዊነት መንፈስን የሚያስቀድም ተቃዋሚ ይደግፋል ብቻ ሳይሆን ሊጠናከርና ሊበረታታም ይገባዋል::
   ግን ! ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ሕዝብን የሚከፋፍል፣ የሕዝብ መብት የሚጋፋ፣ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር የሚያብርና የጠላት መዝሙር የሚዘምር የወያኔን ሴራ እንቅስቃሴም እየታዘብን ነን ፓርላማ ወይንም በኢቲቪ ላይ በጮኁና መግለጫ በሰጡ ቁጥር የተጠናከሩ ይመስላቸዋል  እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእንቅስቃሴያቸዉ እዉነቱን ስለሚያዉቅ ሳይደናገጥ እነዚህ ስልጣን ይዘዉ ከሚቆዩ የመጣዉ መቶ ይህን አምባገነን መንግስት መጣል ያለብን ሰዓት ነዉ እያልኩ ማስገንዘብ እፈልጋለው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕዝብን በማነቃቃትና በማበረታታት የትግሉ አዉራ መሪ ሆናችሁ ከፊት መቆም አለባችሁ::
    በሰለጠኑ አገሮች ጠንካራ የመንግስትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ የፈለገዉ ልዩነት ቢኖርም አገርን አይነኩም አገርን አትንኩ አትከፋፍሉ በሚል መፈክር ሁሉም ወገኖች ይስማማሉ::
በእኛ አገር ግን የትም ፍጭዉ ስልጣኑን አምጪዉ አቆይዉ የሚል መፈክር የተጠናወታቸዉ አምባገነን መሪና ባለስልጣኖች የሰፈሩባት ስለ አገር የማያስቡ ከእንሰሳ በታች  የሚያስቡ የወያኔ አባሎች ብቻ የሚኖሩባት ሀገር ሆናለች የሚያስቡት ስልጣንን ብቻ ነዉ።
    የወያኔ  መንግስት የአመለካከት ልዩነትን አያስተናግድም እናዉቃለን  ተቃዋሚ ፓርቲ እንዳይኖር ይፈልጋሉ ነጻ እትመት እንዳይኖር ይፈልጋሉ ነጻ ሃሳብን ይዞ የሚጽፍ ሰው ጸረ- ሽብርተኛ ተብሎ እንደሚታሰር እናዉቃለን የሚተቸዉን ሰዉ ከቻሉ ማሰር ካልቻሉ እንዲሰደድ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራቸዉ ነዉ  እናዉቃለን በወገናቸዉ ላይ ክህደት ይፈጽማሉ መግቢያ መዉጫ ያሳጣሉ ከእነሱ የተለየ አመለካከት የማስተናገድ ብቃትና ፍላጎት የመሪነት አቅም ያለዉ ሰዉ ማሰር የተካኑበት ሙያቸዉ ነዉ:: ዘርን ከዘር መለየት መርሀ- ግብራቸዉ ካደረኩትም ብዙ አመታን አሳለፉ አረ ምን ተባለነ >>>> በዚህም ኢትዮጵያን እየከፋፈሉ ናቸዉ ለግል ጥቅማቸዉ ብለዉ ኢትዮጵያን ይነካሉ ::
    አሁን አሁንማ የሚገርም ደረጃ ላይ እየተደረሰ ነዉ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚባሉት ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆሩት ሰዎች በአንድነት በጋራ በመተሳሰብና እኩልነት የሚሰብኩ ሰዎች የማርያም ጠላት በመባል እያሳደዱ መግደላቸዉን ማሰራቸዉን የቀጠሉበት አረመኔዉ ዘመን  መሆኑ ... ኢትዮጵያ አትከፋፍሉ።  ለሃይማኖቴ እያለ የሚታገለዉን፣ ለነጻነቱና ለሕዝቡ መብት እንዲጠበቅ የሚጽፈዉ ጸረ- ሽብርተኛ እያሉ እየከሰሱ እያሰሩ ወያኔ ከዚህ በላይ ምን ያድርግ ? ማን ይዳኘው !! ክቡር የሆነዉን የሰዉ ልጅ አበላልጦ በመግዛት የወያኔን ሎሌዎች የበላይ ሆነዉ እንዲኖሩበት ከማድረግ በላይ ምን ሌላ ነገር ይመጣልስ­ ­­? ይህ አምባገነን መንግስት ከጭፍሮቹ ጋር የሴራ መዝሙር እየዘመሩ እስከመቼ እንተዋቸዉ ? ኢትዮጵያዊነት ስሜት እያጠፉ የሕዝብ ጠላት ሆነዉ እያየን ዝም ማለት እስከ መቼ ?  ተዉ! ኢትዮጵያን አትንኩ!!
     ኢትዮጵያን አትከፋፍሉ አትንኩ የሚለዉ አባባል የወያኔ መንግስት ብቻ አይደለም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሆናችሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የማታምኑ በአንድነት በእኩልነት የማታምኑ ዘረኝነት የምታራምዱ ካላችሁ አሁንም እንላለን ኢትዮጵያን አትንኩ አትከፋፍሉ!!
    ለግል ጥቅምና ለግል ክብር ለስልጣን ቅድሚያ እየሰጡ የአገርን ጥቅም የሚዘነጉ የሚረግጡ ሰዎችንም እያስተዋልን ነን በተቀመጡበት የስልጣን  ወንበር ኢትዮጵያን ለማጠናከር ሳይሆን ኢትዮጵያን ለመዝረፍ( ለመቦ) ሲጠቀሙበት እያስተዋልን ነን  እነሱንም ኢትዮጵያን አትንኳት እንላለን::
የአመለካከት ልዩነት፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች መብት ሲኖር፣ እንዲሁም ትግል ሲኖር ዲሞክራሲ ይጠናከራል የመደራጀትና የመናገር መብት ሲከበር ዲሞክራሲ ያብባል የፕሬስ ነጻነት ሲጠናከር ዲሞክራሲ ዋስትና ያገኛል እኩልነትና ሰብዓዊ  መብት ሲከበር ዜጎች ነጻነታቸዉ ይረጋገጣል።
 ለጊዜዉ መጥፎ  እየሰራን ጥሩ የሰራን ሊመስለን ይችላል ነገር ግን የምንሰራዉ ነገር ነገ ሊያስጠይቀን ሊያሳፍረን ሊያሸማቅቀንና ሊያስወነጅለን  ይችላል::
ለኢትዮጵያ የሚጠቅምና የሚበጅ ነገር ሁሌም እንፈልጋለን።
             ግን ኢትዮጵያን አትከፋፍሉ አትንኩ እንላለን በማያሻማና በአጽንኦት ቃል በተደጋጋሚ !
          ኢትዮጵያን ግን አትከፋፍሉ ኢትዮጵያን ግን አትንኩ !!
                                            ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!                           
                                                                                          ከዘካሪያስ


No comments:

Post a Comment