የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ”….. ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።….”። ግን በ’ኛ ሀገር ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ’ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ”ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ”ጎጠኝነት” አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ”ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።” ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?
Wednesday, October 31, 2012
Thursday, October 25, 2012
ታጋይን በማሰርና በመግደል ትግሉን ማሰር አይቻልም !!!
የሚመቸውን ህግ በማውጣት ሰውን በፀረ ሽብርተኛ በመክሰስ በማሰርና በመግደል ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ ለሱ የሚመቹትን እና ለሱ የሚሰግዱትን በማገልገል ሌላውን ሕዝብ ከሌላ አገር የመጣ ይመስል እያሰቃየው በሚገኝበት ወቅት ላይ መሆኑን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም ! ‹‹ ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም›› የሚል ፅኑ መፈክር በማሰማት በበርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ወደስልጣን የወጣው የኢህአዴግ መንግስት መፈክሩን በመዘንጋት“ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው ያለፉትን ገዥዎች ታሪክ እየደገመ ይገኛል፡፡ደርግ ራሳቸውን ‹‹ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ ወንበዴ፣ ሽፍታ…››የመሳሰሉ ስሞችን እየሸለመ ለማጥላላት እንደሞከረው ሁሉ ኢህአዴግም ከጣለው አምባገነን መንግስት ምንም ሳይማር ‹‹ህገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ›› እና አሁን ደግሞ ‹‹ሽብርተኛ››በማለት ዘላለማዊ ሆኖ በመቆየት በመሻት የሰላማዊ ትግሉን ፈርለ ማስለቀቅ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር የሆኑትንና ጋዜጠኞችን በማሰርና የፈለገውን ፍርድ በመስጠት እፎይታ ለማግኘት ሲሞክር እያስተዋልን ነው ፡፡የኢህአዴግን አገዛዝ ከደርግ የሚለየው ደርግ በአደባባይ ገድሎ ሲፎክር ኢህአዴግ ደግሞ ህግ አውጥቶና ህግ ጠቅሶ ሞት ይበይናል።
Sunday, October 14, 2012
ምን ይበጃል ? ምንስ ይሻላል ?
የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ካከተመ በኋላ እና አለም ወደ አንድ የርዕዮት ዓለም ካምፕ እየገባች ባለችበት አጋጣሚ የስልጣን አክሊል የደፉት ገዢዎቻችን የነፃውን ፕሬስ ዓለም በዚች ሀገር እውን እንዲሆን ሁኔታዎችን ብናመቻች የሰለጠነው አለም ያከብረናል በማለታቸው በርካታ ጋዜጦችና መጽሄቶች ለህትመት በቅተው እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ሆኖም ግን የነፃው ፕሬስ አርበኞች አደገኛውን የጎሳ ፖለቲካ መርዝ ለማርከስ እና የስርዓቱን ብልሹ አሰራር እንደ እሳት በሚፋጅ ብእራቸው ስለተቹ ጥሩ ነገርም ከተሰራ በማመስገናቸው የተነሳ የአገዛዙ አማካሪዎችም ሆኑ ፊት አውራሪዎች በበጎ አይን አልተመለከቷቸውም፡፡ የተለያዩ ስልቶችንም እየተጠቀሙ የነፃውንፕሬስ አባላት የመበተን እርምጃ ወስደዋል፡፡
Thursday, October 11, 2012
ኢህአዴግ ነፃውን ፕሬስ ለማጥፋት የጀመረውን ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!!!
የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት
ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ እናምናለን፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ
አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡
የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ
ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡
፡ ወደ እኛ ሃገር ስንመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው
እናገኛቸዋለን፡፡ ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ ለባለፉት 21 ዓመታት
ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል
እንጂ ከዚያ በዘለለ በተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር
የሞከራቸውንም እንደ ቀንዳውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ
በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን ገዢ ፓርቲ ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ
ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፈንታ አጥፊና ደምጣጭ
ሆኖ እየሰራ ነው፡፡
Tuesday, October 9, 2012
እውነተኛው ምርጫ መቼ ይሆን ??
ከ2ዐዐ2 ምርጫ ዋዜማ ጀምሮ አሁንም ድረስ ያልበረደ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንበ (ለነገሩ ህግ ነው) ለምን አትፈርሙም ከኢህአዴግ የሚቀርብ ያልተቋረጠ ጥያቄ ነው፡፡ ይህንን እንከን የለሽ የምርጫ ሥነ- ምግባር ደንብ ካልፈረማችሁ ንግግር ብሎ ነገር የለም በማለት በፓርላማ ቀርበው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ተናግረዋል፡፡ አሁንም ሌሎች እየነገሩን ያሉት ቃል በቃል ይህንኑ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ላለመደራደር፣ ላለመወያየት ይህ ምክንያት እስካለ ድረስ ሌላ መፈለግ አይጠበቅባቸውም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ለሕዝብ ዝርዝሩን ማሳወቅ ተገቢ ስለሆነ ዛሬ በዚህ ጽሑፍ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
Saturday, October 6, 2012
ሲሞቱ ዲሞክራት የሆኑ መሪ
ገድል እንደሰራ ሰው እንዲሰበክላቸው መደረጉ መነጋገሪያ ከሆነ ወራቶች አለፉ ,,, እውነት ለመናገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት እያሉ አምባገነን መሆናቸውና ጥፋቶችን በዜጎች ላይ መፈፀማቸው ከማንም የሚሸሸግ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ባያስደስትም የተወሰኑ የራሳቸውን ሰዎች አስደስተው አርፈዋል ። መጥፎ ተግባራትም ነበሯቸው፡፡ ሆኖም ከፈፀሟው ጥፋቶች አንፃር በየመንደሩ፣ በየትራንስፖርት አገልግሎቱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በየቤተክርስቲያኑና በየመስጊዱ ስለሳቸው ጥሩ ነገር አይወራም ነበር፡፡
Thursday, October 4, 2012
መቻቻል ወይስ መቻል !!!
በአገራችን ያለው የፖለቲካ አለመግባባት እንዲፈታ
በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ እንሰማለን፡፡ በተለይ ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በየመድረኩ ጮኸዋል፡፡ የአገራችን ጉዳይ
ያገባናል ያሉ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ሁኔታ የእርቅ ጥሪውን ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በኢህአዴግ በኩል ግን ማን ከማን
ተጣላና ነው እርቅ የሚያስፈልገው? ሲባል ሰምተናል፡፡ ስለ ዛሬው ከመነጋገር ይልቅ ወደ ኋላ እየተመለሱ ያለፉትን ሥርአቶች
ማውገዝ እንደ ባህል ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም፡፡ የአገሪቱ ጉዳይ የዜጎቿ ጉዳይ ነው ተብሎ
ይታመናል፡፡ማንም ስለማንም አውቅልሃለሁ የሚልበት ጊዜ ማክተም ያለበት አሁን ይመስለኛል።
እውነት ይነገር! ውሸት ይቁም!
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ዜና
ረፍትን ተከትሎ የታክስ ከፋዩ ሕዝብ ንብረት በሆነው
የመንግሥት ብዙሃን መገናኛ የሚነገሩትን የፕሮፓጋንዳ
ውርጅብኝ እየተከታተልን ነው፡፡ ኢትዮጵያን የምድር ገነት
የማስመሰሉ ጥረት የተሳካላቸው የሚመስላቸው ካሉ
ተሳስተዋል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችንን እየኖርንባት
ነው፡፡ የምናውቃት ነች፡፡ ከውጭ አገር አልመጣንም፡፡
በዘር እንዳንዘረዘር !!
የጓደኛችን ቋንቋው፣ ዘሩ፣ ሃይማኖቱና ፖለቲካዊ አመለካከቱ ምን ያደርግልሃል? ደጋ ውስጥ ቢፈጠር ቆላ፣ ወይናደጋ ቢወለድ ተራራ ጫፍ ላይ፤ አንዴ ተፈጥረናልና ሰው ስለመሆናችን ብቻ ማሰቡ ይበልጣል።
ከመጀመርያው ዓለም ጦርነት ማገባደጃ ቦኋላ በጀርመን ማደግ ጀምሮ የነበርው ´´የናሺናል ሶሻሊስት ፓርቲ´´ የናዚ የፖለቲካ ዘይቤን በማስፋፋት ፣ የፋሺስቶች የቀኝ ክንፍ እንቅስቃሴ በዛን ወቅት በዋናነት ይታገል ፣ ይዋጋ ነበረው አንዱ ኮሚኒስቶችን ነበር ፡፡ እነዚህን ክፍሎች ዒላማ ካደረገበት ምክንያት አንዱ ፣ በወቅቱ በዓለማችን ዙርያ እየተጠናከረ የነበረውን ፣ የኮሚኒስቶች እንቅስቃሴ ለመቋቋምና ፣ በስራቸው እየተደራጀ የነበረውን የሰራተኛውን ክፍል (working class ) ከኮሚኒስቶች ነጥሎ በናዚስቶች ስር ለማሰለፍና ነበር ፡፡Monday, October 1, 2012
ኃይለማሪያም ደሳለኝን ተስፋ አታድርጉ
ኃይለማሪያም ወይም ኃይለ ወያኔ ክፍት ወንበር ላይ ቂጢጥ ማለቱ አይገርመንም:: ድሮም
አውታንቲ ሾፌር ይሆናል :: ግን መኪናውም መንገዱም ያው ነው :: ምኑ ላይ ነው
ዓሥራትነቱ ወይም ተስፋነቱ ? እስቲ እንግዲህ እንዴት እንደሚያፋድስ እናየዋለን::
ዘንድሮ ጉድ እኮ ነው ! የአገር ቤቱ አዘንተኛ ሲገርመን ለካስ በተቃዋሚው ሰፈርም ነጠላ
ያዘቀዘቁ ነበሩ :: አገር የማዳኑ ጉዳይ ቀረና እንታረቅ፤ እንቻቻል ሆነ ለቅሶው ።
Subscribe to:
Posts (Atom)