ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩን ያስጠነቀቀው፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ሳምንታዊ ስብሰባውን ባካሔደበት ወቅት ነው፡፡ የቤተ ክህነቱ የፋክትምንጮች እንደተናገሩት፣ የማስጠንቀቂያው መንሥኤ÷ አቡነ ማትያስ ምክራቸውን ለሥልጣነ ፕትርክናቸው አይመጥኑም ከተባሉ አማሳኝ ግለሰቦች እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ክብርና ነፃነት በመጋፋት ከሚወቀሱ አፅራረ ሃይማኖት አካላት ጋራ በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔና ልዕልና የሚፃረር ተግባር በየጊዜው መፈጸማቸው የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ክፉኛ በማሳሰቡ ነው፡፡
Sunday, January 31, 2016
የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !
ኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ ቁጭቱን በቻለው መንገድ ሁሉ ሊገልጸው ሞክሯል።
ሰበር መረጃ የአባይ ግድብ እና የቦንድ ገንዘብ ዘረፋ (ወያኔ)
February 6, 2014 8:15AM የአል ጀዚራ ባልደረባ የሆነዉ ሃሰን ሁሴን (Hassen Hussein) እንደዘገበዉ ጃንዋሪ 8 ላይ ግብጽ የአባይ ግድብ ግንባታ እንዲቋረት ጠይቃለች ይህዉም በሁለቱ ሐገራት መካከል ዉስጥ ለዉስጥ እየተካረረ የመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጸብ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እንደሚሄድ ሲነገር ቆይቶ ሰንብቶ ነበር። በ2017 ይጠናቀቃል የተባለዉ የአባይ ግድብ የተለያየ ችጎች ሲገጥሙት ቆይተዉ በስተመጨሻ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከግብጽ ጋር ሚያደርጉት አለመግባባት ከተካረረ ግብጽ በኤርትራ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ትጎዳናለች ወደሚል ስጋት ስለጣላቸዉ ብቻ የካዮዉን መንግስት (Cairo’s collaboration) ለድርድር በመጥራት እሹሩሩ ጀመረች በስተመጨረሻም ግድቡን ዉሃ ላለመሙላት በመስማማት አጭብጭባና ተጨብጭባ ወደ ወደምትዋሸዉ ህዝብ ተመለሰች።
በኑዌር እና አኝዋክ መካከል የተፈጠረው ግጭት ለግዜው ጋብ ቢል ከፍተኛ ውጥረት አለ ።
* ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲንና የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት ሹፌር መካከል በመኖርያ ቤት መሬት ጉዳይ በተፈጠረ የግል ፀብ ም/ዲኑ የአኝዋኩን ተወላጅ ሹፌር እጅ በጥይት መምታታቸውን አምነው ተናግረዋል ። ከዛ በኋላ ግጭቱ ከግለሰቦች ወደ ተማሪዎች የቡድን ፀብ ተጠናከረ ።
* በግጭቱ የተነሳ ቆስሎ የነበረ አንድ ወጣት በሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ ህይወቱ በማለፉ የወጣቱ ወንድም ትምህርት ላይ ያሉ የአኝዋክ ተማሪዎች ላይ ቦንብ በመወርወር ብዙዎችን አቆሰለ ።
ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳዎች ይልቅ የሙጋቤ መልእክት ትኩረት አግኝቷል
የአፍሪካ ህብረት የሊቀመንበርነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት የዚምቧቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ26ኛው የመሪዎች ስብሰባ ለተተኪያቸው ቦታቸውን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ ህብረቱን በመወከል በተባበሩት መንግስታት፣በነጮችና በባራክ ኦባማ ላይ ጠንከር ያለ ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡
ሙጋቤ ንግግር ለማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ሲያመሩ ከአጋሮቻቸው ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፣ ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው ከተለመደው ከፋ ባለ መልኩ ምዕራባዊያንን፣ነጮችንና የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት አብጠልጥለዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን የ91 ዓመቱ ሙጋቤን ንግግር እያደመጡ በተቀመጡበት ወንበር በጭንቀት ተውጠው ተስተውለዋል፣ ‹‹ሞተዋል አልያም በጠና ታመዋል›› የሚሉ ወሬዎች ሲነዙባቸው የሰነበቱት ሙጋቤ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ካላገኘች ድርጅቱን ለቅቃ እንደምትወጣ ዝተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን የ91 ዓመቱ ሙጋቤን ንግግር እያደመጡ በተቀመጡበት ወንበር በጭንቀት ተውጠው ተስተውለዋል፣ ‹‹ሞተዋል አልያም በጠና ታመዋል›› የሚሉ ወሬዎች ሲነዙባቸው የሰነበቱት ሙጋቤ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ካላገኘች ድርጅቱን ለቅቃ እንደምትወጣ ዝተዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)