ታህሳስ 22 2005 ዓ ም
የምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ሀላፊ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለክልልምምክር ቤት አባልነት ምርጫ መወዳደራቸውንም አጋልጦል።
ጊዜዊ ኮሚቴው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው 18 ጥያቄዎች ማስረጃ ያላቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምርጫ ቦርድን ለፓርላማ አፈጉባኤ እንደሚከስ አስታውቆል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡት 18 ጥያቄዎች ማስረጃ የላቸውም ብሎ ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው ወሳኝ ያላቸው ማስረጃዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ኮሚቴው ይፋ ያደረገው።