Wednesday, July 23, 2014

***ኩዲታ ግዜው ደርሷል***

መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚያስፈልገው የተራዘመ ትግል ሳይሆን ፈጣን ዕርምጃ ነው
ለመልካም አስተዳደር ችግሮች በተራዘመ ትግል መፍትሔ አመጣለሁ ሲል ዕድገቱን ቁሳዊ እያስመሰለው ነው፡፡ ለሰብዓዊ ጉዳዮች መወሰድ ያለበት ዕርምጃ በዘገየ ቁጥር ቁጣ ይቀሰቅሳል፡፡ ይህ ቁጣ ሲጋጋም አብዮት ያስከትላል፡፡ ይህ አብዮት ደግሞ ጠራርጎ ይወስዳል፡፡ አሁንም ይህንን ሐሳብ የሚያጠናክሩ በርካታ ምልክቶች አሉ፡፡ የዲሞክራሲያዊና የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ዜጎች የመሰላቸውን ሐሳብ በነፃነት እንዳያንሸራሽሩ ማፈንና ተቃውሞን ፀጥ ለማሰኘት መንቀሳቀስ ብሶት እየፈጠሩ ናቸው፡፡ ሕጋዊ መንገዶች እየተዘጉ በሄዱ ቁጥር ሕገወጥነት ይንሰራፋል፡፡


በአሁኑ ጊዜ ከክልል እስከ ፌዴራል ባሉ መንግሥታዊ ተቋማት ከሠራተኞች ጀምሮ እስከ ተገልጋዮች ድረስ በመልካም አስተዳደር እጦት ይሰቃያሉ፡፡ ይህ ችግር የብሶት መንስዔ እየሆነ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በመላ አገሪቱ የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩ ሁላችንንም ያግባባናል፡፡ የዚህ ችግር መሠረታዊ ምክንያት ምንድነው ብለን ስንጠይቅ መልሱን በቀላሉ እናገኘዋለን፡፡ በመላ አገሪቱ በመንሰራፋት ላይ ያለው ሙስና የመጀመሪያው ተጠያቂ ሲሆን የተሿሚዎች ብቃት ማነስ፣ የሕዝብ አገልጋይነት መንፈስ መኮስመን፣ ደንታ ቢስነትና በራስ ያለመተማመን፣የመንግስት አምባገነንነት ይጠቀሳሉ፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግር ዋነኛ ጠንቅ የሆነው ሙስና ከአነስተኛው የአስተዳደር እርከን ከወረዳ ጀምሮ የህውሃት ፌዴራል መንግሥት መዋቅር ውስጥ ሰርጎ ገብቷል፡፡ አንድን አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጡ መመርያዎችና ደንቦች የሚፈጥሯቸውን ክፍተቶች በመጠቀም ባለጉዳዮችን በማጉላላት በሕገወጥ መንገድ የሚጠቀሙ በዝተዋል፡፡ በመሬት አስተዳደር፣ በግንባታ ፈቃድ፣ በብቃት ማረጋገጫ፣ በንግድ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ አሠራሮች፣ ማስረጃ በማረጋገጥ፣ በኮንዶሚኒየም ቤቶች አሰጣጥ፣ ወዘተ ተገልጋዩ ሕዝብ በሕግ የተከበረለት መብት ተጥሶ የሙሰኞች ሲሳይ እየሆነ ነው፡፡ አንገታቸውን ደፍተው የሚሠሩ ትጉሃን ሠራተኞችን የሚያሳቅቁ ድርጊቶች ይፈጸማሉ፡፡

በብዙዎቹ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ተሿሚ የሆኑ ግለሰቦች ማንነት ሲታይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ በሚቻል ሁኔታ የገዥው ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ አባል በመሆናቸው ብቻ የማይመጥኑት ኃላፊነት ላይ ተቀምጠው ከሚያግበሰብሱት ሕገወጥ ጥቅም በተጨማሪ፣ በአቅም ማነስ ምክንያት ሥራ መሥራት ያቃታቸው አሉ፡፡ ድሮ ልበለው እንጂ ጠንካራ ግምገማና ቁጥጥር ስለነበር ራሱን ያላዘጋጀ ሰው ሥልጣን አያገኝም ነበር፡፡ ዛሬ የመልካም አስተዳደር ችግር የዜጎችን አዕምሮ እያወከ የለብ ለብ ግምገማ ሲደረግ እንኳን አይታይም፡፡ በዚህ ላይ ደንታ ቢስነትና በራስ ያለመተማመን ጣሪያ በመንካታቸው የሕዝቡ ምሬተ በየዕለቱ እየጨመረ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ችግር ለያዥ ለገናዥ ሲያስቸግር እንዴት የተራዘመ ትግል ያስፈልጋል ይባላል? ደፋርና በራሱ የሚተማመን የነበረ ዜጋ ተሸማቆ አድርባይነት ሲነግሥ እንዴት ዝም ይባላል?
ብቻ አንባገነንነት ሲባዛ ህዝብ መፈንቅለ መንግስት ያደረጋል ይህ ደግሞ አይቀሬ ነው!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment