Monday, July 14, 2014

***አናቱን የሚያሳክከውን እግሩን ብናክለት ሆነ ነገሩ***

***አናቱን የሚያሳክከውን እግሩን ብናክለት ሆነ ነገሩ***
ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉት የሰላማዊ ተቃዋሚ ታጋዮችን torture እያደረገ ነው ያለው የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በሰጡት መግለጫ 99 የተለያዩ ፓርቲዎች አሉ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣቹ ከምጨውብን ተደራጅታቹ ወጣቹ ብጮሁ ይሻላል ነው ያሉት ዛሬ በሰላማዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉት አመራሮች አንበርክኮ በመግረፍ እና ሰላማዊ ሰልፍ አትወጡም በማለት የተለያዩ በደል ሲፈፅምባቸው እያየን ምንድነው የሚጠበቀው።
በግል ጥላቻ የተነሳ የተለያዩ አስተያየት ይሰጣል።አንዳንዱ ተቃዋሚዎች አመፅ እንዲመጣ ይፈልጋል እያሉ ሟርት የሚናገሩ ሰዎች አሉ ለዚህ ሁላ ተጠያቂው ወያኔ ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም፣በፍትህ፣በዲሞክራሲ፣በህግ ህገ መንግስቱን አንተርሶ ጥያቄዎችን እያቀረበ መልስ ሳይሰጠው በየአደባባዩ በጥይት መደብደብ ፣መታሰር ፣መሰደድ ሆኗል መልሱ ስለዚህ አላፊነቱን መውሰድ ያለበት ወያኔ እንጂ ተቃዋሚው አይደለም።

ታዲያ ተቃዋሚው ብረት አንስቶ ቢታገል ምንም አይገርምም በተለይ ለውጥ ፈላጊ ነን የሚሉ ድርጅቶች ይህን የትግል አጋር መሆን ሲገባ ትችቱ ከየት የመጣ ነው ? ወያኔ አምባገነን ስርዓት ነው እያሉ ትግል ደግሞ አያስፈልግም ማለት ከሀሳባቸው ጋር የሚጣረስ ስለሆነ እራሳቸውን ዞር ብለው ቢመለከቱ መልካም ነው።
ሰርቶ ማሳየት ነው እንጂ ተቃዋሚ ሆኖ መግለጫ ማውጣ ህዝብን ማደናገር ይብቃ።አንዳንድ ተቃዋሚ እንዴት መታግል እንዳለባቸው የገባቸው አይመስለም::ትግል ምን እንደሆነም የሚያውቁ አይደሉም::ማነን ነው የምታሰተባብሩት ለሚለው ጥያቅም መልስ የላቸውም::በአንድ ቦታ ተሽጉጠው መግለጫ ማውጣት ብቻ ነው ስራቸው::መግለጫ ማውጣት የትግል ውጤት አይደለም::የሚጨበጥና የሚታይ ነገር ይዞ ብቅ ማለት ይሻላል::ታግሎ ውጤት ማምጣት ከአልተቻለ ቦታውን ለሚታገሉ ድርጅቶች በስላምና በቅንነት መልቀቅ እራሱ አገርን እንደመርዳት ይቆጠራል::ከፈረሱ ጋሪው ይቀድማል ብሎ ማስብ ዓይነት ትግል ከመታገል በሚመጥናቸው ቦታ መስማራት ይገባል:: ለትግል የሚሆን ድርጅት አይደለም::የሚሰራውን ድርጅት ከመተቸት አለን የምትሉ ከሆነ አቅርቡት እንይላችሁ::
‹ኢትዮጰያ፣ ኢትዮጵያ› ማለት ብቻውን ጉንጭን ማልፋት ነው፤ የወገን ፍቅር ይኑረን – ያንንም በተግባርና ለማስመሰል ሣይሆን ከእውነት እናሳይ፤ አናቱን የሚያሳክከውን እግሩን ብናክለት ኅሊናችንም ታካኪውም ይታዘቡናልና በአፋጣኝ እንለወጥ፤ በሞተ ሕዝብ ላይ ለመንገሥ ከምንራወጥ የሚሞተውን ሕዝብ ጠላቶቻችን ናቸው ብለን ከፈረጅናቸው ወገኖች ጋርም ቢሆን “ተመሳጥረን” እናድነው፤ ከወገን ጋር ተባብሮና ተመሳጥሮ ሕዝብን ከመግደል ይልቅ ከጠላት ጋር ተባብሮ ሕዝብን ማዳን በፈጣሪም በታሪክም ታላቅ ዋጋ አለውና አሁን ለአቃቂርና ለወሬ ስለቃ ጊዜ እንዲኖረን ፈቃዳችን አይሁን፡፡ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ደግሞ ሁሉም ወገን መተባበር አለበት፡፡ ወገን እየተሰቃዬ፣ እየተሰደደ፣ አካሉ እየተቆራረጠና ለመለዋወጫነት እየተሸጠ … ባለበት የሚዘገንን ሁኔታ በድሎትና በቅንጦት መኖር፣ ገንዘብንም በአልባሌ ሥፍራና ለአልባሌ ተግባር ማዋል በእግዚአብሔር ዘንድ በኃጢኣተኝነት ባይሆንም እንኳን በነውረኝነት ሳያስፈርጅ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እናም ከዚህ አንጻር ብዙዎቻችን ብዙ መሥራት፣ ራሳችንንም በጥሞናና በተመስጦ መፈተሸ ይጠበቅብናል፡፡ በተለይም እዬዬም ሲደላ ነውና ሕዝባችን ላይ የተሰኩትን እሾሆች ለመንቀል ምንም ጥረት ሳናደርግና ፈቃደኝነት ሳይኖረን እርስ በርስ በነገር ጦር ብንጠዛጠዝ ታሪክ ምሮ አይምረንም።
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment