Tuesday, September 30, 2014

አስደንጋጭና አሳፋሪ ምስጢር ሲገለጥ፡ Shocking!

በሴቭ አድና
አስደንጋጭና አሳፋሪ ምስጢር ሲገለጥ፡ Shocking!

አስደንጋጭና አሳፋሪ ምስጢር ሲገለጥ፡ Shocking!

ትላንት ሀይማኖተኛ፣ ፈሪሀ እግዚአብሄር የያዘና ጨዋ የነበረ ህዝብ እንዴት እንዲህ በሙስና፣ የንዋይ ፍቅርና በውሸት እንዲህ ረከሰ?
ባንድ ነገር መስማማት እንችላለን፡፡ የዛሬ አያድርገውና ህዝባችን ሙስናን፣ ስርቆትን፣ ውሸትን፣ ጭቆናን የሚፀየፍ፤ ተካፍሎ መብላትን እንጂ መስገብገብን የማይሆንለት፤ ክብሩን የጠበቀ፣ የሌላ መብትም የማይነካ ኩሩና በራስ መተማመን የተጎናፀና ከፍ ያለ የሞራል እሴቶች የነበሩት ነበር፣ ከአንድ ሁለት ዐስርት ዐመታት በፊት፡፡
አንዳንዶች ጥቂት አባባሎችን (ለምሳሌ “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚለውን የአማርኛ ምሳሌ) እያነሱ “ባህላችን ሙስና ያበረታታል” ለማለት ዳርዳር ቢሉም ማለት ይህ ከእውነታ የራቀ ነው፡፡

Sunday, September 28, 2014

በ9 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን 800 ሺ በላይ ስራ አጦች ተመዘገቡ!!

ኢሳት ዜና ፦ ባለፈው ዓመት በዘጠኝ ወራት ብቻ የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ ለማጠናቀር ታስቦ በተካሄደ ምዝገባ በመላ ሀገሪቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሥራ ፈላጊዎች በፈቃደኝነት መመዝገባቸውንና ከነዚህ ውስጥ ከ351ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጆች ምሩቃን መሆናቸውን ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘ ጥናት አመለከተ። ይህ ጉዳይ መጪው ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል የገመተው ኢህአዴግ በተለይ በአዲስ አበባ ባለፉት ሳምንታት የሥራ አጦች አዲስ ምዝገባ ቤት ለቤት በማካሄድ ላይ ይገኛል። በ2006 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ የተመዘገቡት ሥራ ፈላጊዎች 1 ሚሊዮን 759 ሺ 768 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 41 ሺ 298 የዩኒቨርሲቱ ምሩቃን፣ 310 ሺ 10 የኮሌጅና ቴክኒክና ሙያ ምሩቃን፣ የተቀሩት 1 ሚሊዮን 444 ሺ 460 ያህሉ በተለያየ የትምህርት ደረጃ የሚገኙ ሥራ ፈላጊዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።

የቅዳሜ ውሎ በቃሊቲ

 እስረኞች መብት አላቸው፡፡ አንዳንድ እስረኞች ግን ከሌሎቹ የተለየ መብት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ምንም መብት የላቸውም››
ዛሬ ወደቃሊቲ አቅንተን ነበር፡፡ የእነ አቶ በቀለ ገርባ፣ የአዛውንቱ ሲሳይ ብርሌ፣ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ምክር፣ ትንታኔና ተስፋ አንዳች ጥንካሬ ይሰጣል፡፡ የእነዚህ ታሳዎች ጥንካሬ ቃሊቲ እስር ቤት መሆኑን ሁሉ ያስረሳል፡፡
political-prisoners-ethiopia2
መጀመሪያ እነ በቀለ ገርባን ጠይቀን ነው ወደ ጋዜጠኛው ያቀናነው፡፡ ውብሸትን ለመጠየቅ ስናቀና የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል የነበረው ገብረወሃድ እስረኞች ከሚጠየቁበት ውጭ አንድ ጥግ ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር ሰብሰብ ብሎ አየነው፡፡ እስረኞች ወደሚጠየቁበት ስናመራ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዳይሬክተር የነበረው መላኩ ፋንታና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለመጠየቂያነት የተከለለው ቦታ ላይ ጎን ለጎን ቆመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እያወሩ ደረስን፡፡
ከውብሸት ጋር ለተወሰኑ ደቂቃዎች ካወራን በኋላ ይበቃል ተባለ፡፡ ገና ወደ ውብሸት ስንመጣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የነበሩት መላኩ ፋንታ አሁንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እያወሩ ነው፡፡ ገብረ ወሃድም እንደዛው፡፡ እንግዲህ በእስረኞች መካከል የሚፈቀደው የሰዓት ገደብም ይለያያል ማለት ነው፡፡ ለ‹‹አሸባሪ›› ጋዜጠኛ 10ና 20 ደቂቃ፣ ለ‹‹ኪራይ ሰብሳቢ›› ባለስልጣን ደግሞ የፈለገውን ያህል ጊዜ ይሰጣል፡፡

ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ …ከኤርምያስ ለገሰ

በቅድሚያ መጵሀፉን ጊዜ ሰጥተህ በማንበብ አስደማሚ ምልከታ በመስጠትህ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተጳፈበትም አንዱ አላማ ይህ ስለሆነ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእይታህ ላይ እነዚህ ጉድለት ይታይባቸዋል ብለህ ያነሳኸው እና የወደፊት ግምቶችህ ላይ የተወሰነ አስተያየት ለመስጠት የሚጋብዙ ስለሆነ ትንሽ ማለት ፈለኩ። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች በመጵሀፉ ይዘት ላይ ዝርዝር ግምገማ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለእያንዳንዱ አስተያየት መስጠት ከጊዜ አኳያ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የማልዘልቅበትን መንገድ ልጀምረው አልፈለኩም ። የጋዜጠኛ ተመስገንን በልዩ ሁኔታ መመልከት የፈለኩበት የራሱ ምክንያቶች አሉት። ተመስገን ሀገር ቤት ባለ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በድፍረት መጵሀፉን ማንበቡን በአደባባይ ገልጶ በመጵሄት ሳይቀር መክተቡ ልዩ ያደርገዋል ። አንዳንድ የቀድሞ ” የትግል ጓዶቼ! ” በሚስጥር ቢሮ እየቆለፉና እቤታቸው እየደበቁ ባነበቡበት ሁኔታ የተመስገን ፊትለፊት ማውራት ምንያህል የህሊና ራስ ምታት እንደለቀቀባቸው ማሰቤ ሁለተኛ ምክንያት ነው( ቢያንስ ሁለት “ሚኒስቴር ደረጃ ያሉ ሰዎች ” የተፃፈው ሐቅ ስለሆነ ማስተባበል አይቻልም ” የሚል አስተያየት መስጠታቸውን እርግጠኛ ከሆነ ምንጭ ሰምቻለሁ ።

Wednesday, September 24, 2014

ኢህአዴግ ከጠ/ሚኒስትሩ ህልፈት በኋላ ደንግጧል

ከኢትዮጵያ ቴሌኮም ይልቅ ህልሜን አመንኩት!
ባለፈው ሳምንት በህልሜ ያየሁት ነገር አስገራሚ ነው፡፡ በአብዛኛው በህልማችን የምናየው ነገር የግል ህይወታችን ላይ የሚያተኩር ይመስለኛል፡፡ መቼም ናላውን ከሚያዞረው የኑሮ ውድነት ሃሳብ ወጥቶ ስለአገሩ ባለ ሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ ዕድገት በህልሙ የሚያይ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ (ቢያይማ ከኑሮ ውድነት ይወጣ ነበር!) ስለ አገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት ወይም ስለ ስልጡን የፖለቲካ ባህል መዳበር ተኝቶ የሚያልም አለ ብዬ አልገምትም፡፡ (በህልም ዲሞክራሲ ማየት እንዴት ነው? ) በነገራችሁ ላይ ኢህአዴግ በህልሙ ያየውን ነገር ሁሉ እኛም ብናይለት (“ኮፒ ፔስት” ነው ታዲያ!) እንዴት ጮቤ እንደሚረግጥ አልነግራችሁም፡፡ በቃ ሃሳባችን ከሃሳቡ፣ህልማችን ከህልሙ ቢገጥምለት በእድሜው ላይ 40 ዓመት ይጨምር ነበር (ከ30-40 ዓመት በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካሰበው ውጭ!) አንዳንዴ ሳስበው “እኔን ምሰሉ!” ማለት ምን ክፋት አለው እላለሁ፡፡

የህወሓት ትውልድ ገዳይ ስውር መርዝ

አሁን እጅግ በላቀ የዕድገት ደረጃ ሆኖው የሚናያቸው የአለም አገራት መሰረታቸው እውቀት ነው::ያለ እውቀት ፈጠራና ምርምር÷ጥበብና ክህሎት÷ዕድገትና ልማት ሊኖሩ አይችሉም::
ትምህርት የእውቀት ቤት ነው:: እውቀት ካለ ደግሞ ምክንያትነት አለ:: ምክንያትነት ካለ ደግሞ ምርምርና ጥናት አለ::ምርምር ካለ ደግሞ መጠየቅ አለ:: መጠየቅ ካለ ደግሞ መከራከርና መወያየት አለ:: መከራከር ካለ ደግሞ የለውጥ መንገድ አለ:: የለውጥ መንገድ ካለ ደግሞ ዕድገት አለ!!!!
ህወሓት ገና በረኻ ደደቢት እያለች 1973 “የወደፊት የኔ ጠላት ሙሁሩ ክፍል ነው” ማለቷም “የኔ ጠላት ዕውቀት ነው” ከሚል ሐሳብ ጥልቅ የሆነ ግንኙነት አለው::በአሁኑ ዘመን ትምህርት ምላሷ እንጂ ተክለ ሰውነቷ(ቁመናዋ) የለም ማለት ይቻላል:: ይህ ማለት ደግሞ የዕውቀት ግንብ ፈርሷል ማለት ነው::ይህ ማለት ደግሞ የጥበብና የምርምር ቤት ተንዷል ማለት ነው::

ከቤተመንግስት ዘርፎ የወሰደው የጃንሆይ ወርቅ ከአገር እንዲወጣ በመለስ ዜናዊ ድጋፍ እንደነበረ አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋለጠ።

ብስራት አማረ ከቤተመንግስት ዘርፎ የወሰደው የጃንሆይ ወርቅ ከአገር ያወጣው አቶ መለስ ዜናዊ በተሳፈሩበት አውሮፕላን እንደነበረ አንድ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋለጠ። በአሜሪካ ኦሀይ ግዛት የሚኖረው የቀድሞ የሕወሐት አባልና የደህንነት ሹም ብስራት አማረ ከቤተመንግስት ከዘረፈው የጃንሆይ ወርቅ ጋር በተያያዘ እንዲታሰር መደረጉን ያስታወሰው ምንጩ ይህን ውሳኔ ያስተላለፉት ጥቂት የፓርቲው አመራሮች መሆናቸውን ጠቁሟል። ብስራት በሆለታ እስር ቤት እንዲታሰር ቢደረግም ወርቁን ግን አሳልፎ እንዳልሰጠና ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ከእስር ተፈቶ ወደ አሜሪካ ማምራቱን ያመለከተው ምንጩ በሚሊዮን የሚገመት ዶላር የሚያወጣው ታሪካዊ ወርቅ አቶ መለስ ዜናዊ በተሳፈሩበት አውሮፕላን ተጭኖ አሜሪካ መግባቱንና ብስራት አማረ እንደተረከበ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቀው ምንጭ አጋልጧል።

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች – ከተመስገን ደሳለኝ

temesgen-desalegn
በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ
ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል
አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር
ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ለጥቆ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞው
የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በኤምባሲው ግቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁት የዕራት ግብዣ ላይ (ግንቦት 19/2001
ዓ.ም) ድንገት ተገናኝተን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤ ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው፣ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ግንቦት 7 እና እነጀነራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ዕለት እንደ አፄ ኃይለሥላሴ የክብር ዘብ፣ ከሽመልስ
ከማል ጋር በረከት ስምዖንን ግራና ቀኝ አጅቦ በተገኘበት ወቅት ነው፡፡ በተቀረ በመንግስት ሥልጣን ሲገለጥ ብዙም
አላስተዋልኩም፡፡ ከዚህ ይልቅም ኢህአዴግነቱን ለማሳየት የሞከረበትን አንድ ገጠመኝ አስታውሳለሁ፤ ይኸውም “የፍትሕ”
ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው እና አሁን በስደት ሀገር የሚገኘው ባልደረባዬ ማስተዋል ብርሃኑን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባለው
ቢሮው ድረስ በመጥራት ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ከሰነዘረበት በኋላ፣ ዛሬ የቀድሞ ጓዶቹ ሥራዬ ብለው እንደቀጠሉበት አይነት
በጋዜጣው ላይ የሀሰት ውንጀላ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ከኃላፊነቱ ራሱን እንዲያገል አስጠንቅቆት እንደነበር ከራሱ ከባልደረባዬ
ማስተዋል አንደበት ሰምቻለሁ፡የሆነው ሆኖ አቶ ኤርሚያስ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፉ በተመላኪው ሰው አመራር “ሁሉን
አዋቂነት” ላይ የቆመው መንግስት ምን ያህል በጠባብ የወንዝ ልጅነት የተተበተበ እና በዘራፊ ባለሥልጣናት የተዋቀረ
እንደሆነ በስፋት ተርኮልናል፡፡

የኦጋዴን ኡኡታ

g7-logoዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በወጣትነታችን ብረት አንስተን ጫካ እንድንገባ አደረገን ብለዉ የሚናገሩት በወቅቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተንሰራፍቶ ይታይ የነበረዉ በብሄር ብሄረሰቦች ጭቆና ነበር። ወያኔዎች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለእነሱ ለራሳቸዉ የሚመች ህገ መንግስት ጽፈዉ ትልቁን የኢትዮጵያ ችግር ፈታን ብለዉ የሚናገሩት ይህንኑ ዛሬም ድረስ እናት አገራችንን ኢትዮጵያን እንደ ነቀርሳ በሽታ ቀስፎ ይዞ የሚቆጠቁጣትን የብሄር ብሄረሰቦች ችግር ነዉ። ወያኔ በ1994 ዓም ህገመንግስቱን አጽድቆ የፌዴራል ስርዐት ከመሰረተ በኋላ ድምጹን ከፍ አድርጎ የጮኸዉ ማንም መፍታት ቀርቶ ሞክሮት አንኳን የማያዉቀዉን የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ችግር እኔ ፈታሁት የሚል ለሱና ለደጋፊዎቹ ብቻ የሚሰማ ጩኸት ነበር። ወያኔ የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ከታሰሩበት ሰንሰለት ፈትቼ “ነፃ” አወጥቼ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲመሩ መንገድ ከፈትኩላቸዉ ብሎ ከተናገረ ከሃያ አመታት በኋላ ዛሬም ኢትዮጵያ ዉስጥ የትኛዉም ብሄረሰብ እራሱን በራሱ ማስተዳደር ቀርቶ የአገሪቱ ዜጎች ባሰኛቸዉ ቦታ መኖር እንኳን አይችሉም። የሚገርመዉ ነጻነትና እኩልነት የሠላም ጠላቶች የሆኑ ይመስል ዛሬ ወያኔ ነጻ ወጡ የሚላቸዉ ብሄረሰቦች በሚኖሩበት አካባቢ ሁሉ የሚታየዉ የአገራችንን አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል ብጥብጥ፤ ግጭትና ክልሌን ለቅቀህ ዉጣ የሚል ወያኔ ይዞብን የመጣዉ መፈክር ነዉ።

የሌላ ሰው የመመርቂያ ጥናት ዘርፎ በኖርዌይ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀው ኢትዮጵያዊ ዲግሪው ተሰረዘ

degree2ቁምነገር ምፅሄት ቁጥር 187 ለሶደሬ
በዘነበ ወላ
ሐሳዊ ምሁራንን በሀገራችን እያየን ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜያት በምዕራቡ ዓለም መሰነባበታቸውን አስታክከው በሌላቸው እውቀትና ክህሎት አንቱታን የመሻት አባዜ የተጠናወታቸውን ሰዎች ማየት የተለመደ ክስተት ከሆነም ሰነባብቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎቻችን ፤ በየመሥሪያ ቤቶቻችን አድፍጠው የተቀመጡት አደባባይ ወጥተው ‹ዶክተር ኢንጅነር› ነን ብለው በድፍረት ከነገሩን በቁጥር ይልቃሉ፡፡ ያልመረመሩትንና ያላጠኑትን የሌላን ሰው ጥናት ና የምርምር ውጤት የራስ አድርጐ በማቅረብ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ከሚገኘው የትምህርት ተቋማት መመረቅ እያቆጠቆጠ ያለ ሌላው ችግር ነው፡፡በቅርቡ በኖርዌይ ትሮምሶ (Tromso) ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው የምርምር ጽሁፍ ዘረፋ ለዚህ አባባል አንዱ ማሳያ መሆኑን የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያምናል፡፡ የዚህ ችግር ሰለባ ከሆኑት አያሌ ሰዎች አንዱ አበራ ኃይለማርያም ወልደየስ ነው፡፡

Sunday, September 21, 2014

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ካልተካሄደ የከፋ ሁኔታ ሊከተል ይችላል!!

በአንድ ሀገር የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ዘላቂ ሰላም መልካም አስተዳደርና የልማት ተነሳሽነት ሊኖር የሚችለው የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ የህዝቡ የስልጣን ባቤትነት የሚረጋገጠውም ወቅቱን ጠብቆ በሚካሄድ ሁሉን አቀፍ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ነው፡፡ ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅሜን ያሰጠብቁኛል፣በትክክል ያገለግሉኛል ይበጁኛል ብሎ ያመነባቸውን ተወካዮቹን በነጻነት በመምረጥ ዕውነተኛ የስልጣን ምንጭና ባቤትነቱን ለማረጋገጥ አልታደለም፡፡የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግስት ለጋሽ መንግስታትንና በአጠቃላይም ዓለምአቀፊን ማህበረሰብ ለማታለል እንደሚሞክረው አንድም ጊዜ ቢሆን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በህዝብ አልተረጠም፡፡

ህወኃት በወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የዘር ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው፣

የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ተከዜን ተሻግሮ እስካሁን በሃይል የወሰዳቸው የጎንደር ወልቃይትና ፀገዴ ቦታወች ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ፀለምት፡ እና ከፀገዴ ከነበሩት ጠቅላላ 39 ቀበሌወች ውስጥ 25ቱን ቀበሌወች ወደ ትግራይ ወስዶ አንድ ወረዳ የመሰረተ ሲሆን ወደ አማራ ክልል ከፀገዴ የቀረው 14 ቀበሌ ብቻ ነው። አካባቢው በለምነቱ የታወቀና ድንግል መሬት ያለበት ሰፊ አካባቢ ሲሆን በብዛት የሚመረቱት የአዝርዕት አይነቶች ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ ሩዝ፣ስኩኣር አገዳ፣ ፍራፍሬና አትክልት በስፋት ይመረታሉ። በዚሁ በወልቃይት ፀገዴ አካባቢ የሚገኙና ወደ ትግራይ የተወሰዱ ትላልቅ ከተሞች ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ማይፀብሬ፡ ዳንሻ፣ ማክሰኞ ገበያ/ ንጉስ ከተማ/ና ዲቪዥን የተባሉ ከተሞች ተወስደዋል።የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ይህንኑ የመስፋፋት ስስቱን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት አንገረብ ወንዝን በመጠቅለል የፀገዴ ቀሪ ቀበለወችን እና የታች አርማችሆ ለም መሬትን ለመውሰድ እየተዘጋጀ እንደሆነ ያካባቢው ጭብጦች ያስረዳሉ።

የጋምቤላዉ የርስ በርስ ግጭት

ከጳጉሜ5 2006 ጀምሮ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመዥንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ለህልፈተ ህይወትና ስደት መዳረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። በአካባቢው ለረጅም አመታት በመምህርነት እንዳገለገሉ የሚናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ ራሳቸውን የአካባቢው ነባር ብለው በሚጠሩት ነዋሪዎችና መጤ በሚሏቸው ደገኞች መካከል መፈጠሩን ገልፀዋል።

በጋምቤላ ግጭት የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው

ሸፍተው የነበሩ የዞኑ የፖሊስ ልዩ ሃይል አዛዥና የሚሊሽያ አባላት እጃቸውን ሰጡ
በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጎደሬ ወረዳ፣ በመዠንገር ዞን በተቀሰቀሰውና አሁንም ድረስ በአንዳንድ ቦታዎች በቀጠለው ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ የክልሉ ባለስልጣናት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡ በአዲስ አመት ዋዜማ የተቀሰቀሰውና ከ40 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት መነሻ ከመሬት ባለቤትነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ለአዲስ አድማስ የገለፁት ምንጮች፤ “ደገኞች መሬታችንን ይልቀቁ” የሚሉ የአካባቢው ተወላጆችና አንዳንድ የክልሉ ባለስልጣናት በመንግስት ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የሰፈራ ፕሮግራም ተገን በማድረግ ነባር ይዞታ ያላቸውን ነዋሪዎች በማፈናቀላቸው ግጭቱ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ለብድር ዕዳ አደጋዎች የመጋለጥ ዕድሏ እየሰፋ ነው አለ

ስሪ ሙሊያኒ ኢንድራዋቲ
ሰሞኑን ለሦስት ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የኦፕሬሽን ዋና ኃላፊ ስሪ ሙሊያኒ ኢንድራዋቲ፣ እያደገ የመጣው የብድር ዕዳ መጠን በኢትዮጵያ ላይ አደጋዎችን ሊያስከትል እንደሚችል ገለጹ፡፡
ኢንድራዋቲ ባለፈው ረቡዕ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ምንም እንኳን የአገሪቱ የብድር ዕዳ መጠን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አኳያ ያለው ድርሻ አነስተኛ ቢሆንም፣ የዕዳውን መጠን በግልጽነት ለማስተዳደር የሚችልና ግልጽነት የሰፈነበት አስተዳደር ማስፈን የመንግሥት ግዴታ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ምሁራን የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ፡፡

መንግስት ፀረ-ሽብርተኛ ናቸው ብሎ ያሰራቸውን ጋዜጠኞችና ጦማሪያን እንዲፈታ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ምሁራን ቡድን ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ አቅርቧል፡፡
የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ምሁራኑ የኢትዮጵያን መንግስት የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን ያለአግባብ በመጠቀም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሰ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኞች፣ የጦማሪያን፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖለቲከኞችና ሌሎች አካላት ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየተነፈገ መሆኑን የምሁራን ቡድኑ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችን ሊያከብርና የፀ-ሽብርተኝነት ህጉን በአግባቡ መጠቀም ይኖርበታል ተብሏል፡፡ አዲስ ስታንዳርድ

ወጣቶቹ የአንድነት አባላት ጥላዬ ታረቀኝ እና ዳንኤል ፈይሳ ሃገራቸውን ጥለው ተሰደዱ።

የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ምክትል ፀሐፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ መሰደዱ የታወቀ ሲሆን በተያያዘ ሁኔታ የሚለዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል በተደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የእስረኛ ቱታ በመልበስ የገዥው ፓርቲን አምባገነናዊነት ካሳዩ ወጣቶች መካከል ዳንኤል ፈይሳም በተመሳሳይ ሁኔታ ለስደት መዳረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡Image

Thursday, September 4, 2014

መንግስትን ከምቃወምባቸው ምክንያቶች 2ኛው: * የግማሽ ሚሊዮን ኮንትራት ሰራተኞች አበሳ በሳዑዲ አረቢያ

Saudi arabia ethiopia 1
Saudi arabia ethiopia 2
Saudi arabia ethiopia 3
Saudi arabia ethiopia 4
ከነብዩ ሲራክ (ሳዑዲ አረቢያ)
* የግማሽ ሚሊዮን ኮንትራት ሰራተኞች አበሳ … !
ህገ ወጡ የስደት መንገድ ይቆም ዘንድ በሚል እሳቤ የኢትዮጵያ መንግስት የሳውዲ አረቢያ የኮንትራት ሰራተኛ ማቅረብን ተስማሙ ተባለ። ስለተደረገው ስምምነት ውል ግን የሚታወቅ ነገር ጠፋ ። ከሁለትዮሽ ስምምነት የወጣ ውል ነው ተብሎ በሚታወቀው የተሸፋፈነ ስምምነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኮንትራት ስራተኞች ወደ ሳውዲ ገቡ።

በኢትዮጵያ ምን ዓይነት መንግሥት አለ? ( መንደርደሪያ ሃሳብ )

እስከመቼ ቅፅ ፲ ቁጥር ፲፯
አንዱ ዓለም ተፈራ
ሰኞ፤ ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓመተ ምህረት ( 09/01/2014 )
ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ነው። በተለይ በትግሉ ላይ የተሰማራነው ኢትዮጵያዊያን፤ ለዚህ ትክክለኛ መልስ መሥጠት አለብን። ለዚህ የምንሠጠው መልስ፤ ትብብሮችን ወይንም ውህደቶችን፣ ልዩነቶችን ወይንም መራራቆችን ያስከትላል። ከዚህ መሠረታዊ ጥያቄና ለዚህ ጥያቄ ከምንሠጠው መልስ፤ ማንነታችንን ብሎም የተሰባሰብንበትን ድርጅት ማንነት ማወቅ ይቻላል። እንግዲህ ሀገራችን ባለችበት ቀውጢ ሰዓት፣ የታጋዩ ክፍል ባለበት የተበታተነ ሀቅ፣ የተበታተነ ትግል በመከተል ትግሉ ማዕከል ባልያዘበት ሁኔታ፣ ትግሉን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ ካልፈለግን፤ ድርጅቶችን መመሥረትና በትግል ላይ ነኝ ከማለት አልፈን፤ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መልስ መሥጠትና ይህን ግልጽ ማድረግ አለብን።

Tuesday, September 2, 2014

የህወአት ታላላቅ የታሪክ ክህደቶች ከ“ፍኖተ ገድል” (ገብረመድህን አርአያ )

ለአነባበብ ይረዳ ዘንድ ጽሁፌን ከመጽሃፉ እያጣቀስኩ ለመልሱ ከራሴ እና አስረጅ ይሆናሉ ካልኳቸው ዋቢ ማስረጃዎች ጋር አድርጌ የራሴን እነሆ እላለሁኝ።
የታሪክ ክህደት ቁጥር 1:
ይህ ጉዳይ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የትግሪኛ ፕሮግራም ላይ አረጋዊ በርሄ እና ስብሃት ነጋ ቀርበው የተወያዩበት/የተከራከሩበት እና እና ስለ መጽሃፉ በተለይ እኛ ከአገር ውጪ ያለን ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማንበት ጭብጥ ነው -የአክሱም ስልጣኔ ጉዳይ።

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ

ሰነዱ አሜሪካንን ጨምሮ ለኃያላን አገሮች ቀርቧል
puntland somaliland
ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች “እንሰጋለን” ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል