በ1997 ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ስርዓትን በቃኝ ብሎ በድምጹ ከወሰነና በኋላም ህወሀት አስከፊ እልቂት በመፈጸም በስልጣን ላይ መቆየቱን እንዳረጋገጠ ነው። በመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች: መምህራን: ሰራተኞች: ነጋዴዎች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየተራ ያን መከረኛ ስልጠና እንዲወስዱ ዘመቻ የታወጀበት ጊዜ ነው። በአዋሳ ስልጠናው እየተሰጠ በአንዱ ቀን እንዲህ ሆነ። የብአዴኑ አመራር አቶ ተፈራ ዋልዋ በፕላዝማ ስልጠና ይሰጣል ። አማራው እንዴት አድርጎ ሌላውን የኢትዮጵያ ብሄረሰብ እንደበደለ: የሰው መሬት እንደተቆጣጠረ ያልተጻፈ ታሪክ እየጠቀሰ መርዝ የሆነ የዘር ማጥፋት ድርጊት እንዲፈጸም ጥሪ ያደርጋል።
Sunday, November 22, 2015
ኃይሌ ገ/ስላሴ ለእኔ
የስፖርተኞች ስም የተለጠፈበት ልብስ ለብሼ አላውቅም፡፡ ግን በስማቸው የታተመ ልብስ ብለብስላቸው ከማያሳፍሩኝ መካከል ኃይሌ አንዱ ነበር፡፡ ገና በልጅነቴ በሬድዮ የሀይሌን ማሸነፍ ሰምቼ ዘልያለሁ፣ ተሸነፈ ሲባል በጣም አዝኜ አውቃለሁ፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለኃይሌ የተለየ ስሜት ነበረኝ፡፡ በቅርብ ግን ኃይሌ እየወረደብኝ መጣ፡፡ በቅርብ አመታት ኃይሌ ለምን ድሆችን (አካል ጉዳተኞችም፣ ህጻናትና አዛውንቶችን ጨምሮ) እንደማይረዳ ሲጠየቅ በተደጋጋሚ ‹‹ሰርተው ይብሉ!›› ሲል አዳምጬ ገርሞኛል፡፡ የሜቄዶንያው ቢኒያም ይህ የኃይሌ አባባል እንዴት ያናድደው?!
ከ3 አመት በፊት ግን የኃይሌ ስም ያረፈበትን ቲሸርት ብለብስ ኖሮ ይቆጨኝ እንደነበር የሚያስታውስ ነገር ሲናገር ሰማሁት፡፡ ‹‹ለምን ሰርተው አይበሉም!›› የሚለው ኃይሌ ሰርተውም የዋጋቸውን የማይከፈላቸው መምህራን ‹‹የስራ ዋጋችን ይከፈለን፣ ደመወዝ ይጨመርልን!›› የሚል ጥያቄ ሲያነሱ፣ እሱን የለመኑት ይመስል ይህን ጥያቄ ቅብጠት አድርጎ ሲወርፋቸው በሬዲዮ ሰማሁ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)