በ1997 ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ስርዓትን በቃኝ ብሎ በድምጹ ከወሰነና በኋላም ህወሀት አስከፊ እልቂት በመፈጸም በስልጣን ላይ መቆየቱን እንዳረጋገጠ ነው። በመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች: መምህራን: ሰራተኞች: ነጋዴዎች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየተራ ያን መከረኛ ስልጠና እንዲወስዱ ዘመቻ የታወጀበት ጊዜ ነው። በአዋሳ ስልጠናው እየተሰጠ በአንዱ ቀን እንዲህ ሆነ። የብአዴኑ አመራር አቶ ተፈራ ዋልዋ በፕላዝማ ስልጠና ይሰጣል ። አማራው እንዴት አድርጎ ሌላውን የኢትዮጵያ ብሄረሰብ እንደበደለ: የሰው መሬት እንደተቆጣጠረ ያልተጻፈ ታሪክ እየጠቀሰ መርዝ የሆነ የዘር ማጥፋት ድርጊት እንዲፈጸም ጥሪ ያደርጋል።
ሰልጣኙ ግራ ገባው። ሰውዬው የአማራ ተወካይ ነኝ እያለ አማራው ላይ መዓት እንዲወርድ ሲሰብክ ሁሉም ሰው ተደናገጠ። ቃል በቃል ተፈራ ዋልዋ እንዲህ ነበር ያለው
" ተመልከቱ አከባቢያችሁን። ማን ነው ባለወፍጮ? ማን ነው ሰፊ መሬት ይዞ በተንጣለለ ቪላ ቤት የሚኖር? ማን ነው ባለሱቅና መደብር ባለቤት? ይሄ ነገር መስመር መያዝ አለበት። ....." ተፈራ ይሄን የዘር ማጥፋት ጥሪውን በወቅቱ ከአማራው ክልል በቀር በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች በፕላዝማ በተመሳሳይ ሰዓት ያስተላልፍ ነበር። በጣም አስደንጋጭ ነገር እንደሚፈጠር ያልገመተ አልነበረም። ከ1997 ዓም በኋላ በጌዲኦ ዞን ቡሌ: የኣማራ የሚባል ባለሱቅና ንብረት ያለው በጠራራ ጸሀይ ዶግ አመድ ሆነበት ። በጉራፈርዳ ምጽአተ አማራ ታወጀ ። ቤንሻንጉል የአማራው ህዝብ የስቃይ ምድር ሆነ። በምእራብ ሸዋ: በጅጅጋ በሌሎችም አከባቢዎች የተፈራ ዋልዋ ጥሪ ተግባራዊ ሆነ። እነመለስ በእርግጥም ብአዴንን አምጠው መውለዳቸው ያለምክንያት አልነበረም። አማራውን አከርካሪውን ለመስበር ብለው ካስጠኑት ፕሮጀክት ዋናው ብአዴን የተባለ ድርጅት ጠፍጥፎ መስራት ነበር። ይሄው ላለፉት 20 ዓመታት በላይ የአማራው ህዝብ መዓት ወረደበት ። .....ብአዴን እንኳን ለ35ኛ ዓመት የሎሌነት ዘመን አበቃህ።

No comments:
Post a Comment