ምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምክረው እንደሚሉት አበው 25 ዓመት ሙሉ ሲመከር ሲለመን ሲዘከር ምክርን እንደ ስድብ ልመናን እንደ ፍራቻ ዝክርን እንደ ማታለል አድርጎ በመቁጠር ዝም በሉ ዝም ካላላችሁ ዝም አደርጋችሃለሁ ረግጫችሁ እገዛችኋል አማራና ኦሮሞን አጋጭቶ በመሃል እኔ ስልጣኔን እያደላደልኩኝ 100 ዓመት እገዛለሁ ብሎ የቀየሰው ስልት ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር ወደሚቻልበት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ በመግባቱ ታውቋል። ኦነግና አርበኞች ግንቦት 7 የተቀናጀ ድምጽ አሰምተውን ኦነግ በአሶሳ ፤በሀረር ፤በቦረና ወያኔን እየደመሰሰ ወደ ፊት እየመጣ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር፤ በጎጃም ፤በደቦብ በድሬደዋና በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ትግሉን በማቀጣጠል ወያኔን መቆሚያና መቀመጫ እያሳጡት ነው የሚለውን ዜና እንሰማለን።
ማንም ታጋይ መኖሪያውን በረሃ ላይ እንዲሆን የሚፈልግ የለም፡ ማንም ታጋይ ከሚወደው ቤተሰቡ እና ህዝቡ ተነጥሎ በበረሃ ላይ ከባዱን ኑሮ የሚፈቅድ ያለ አይመስለንም ፡ ማንም ታጋይ በአገሩና በህዝቡ ላይ ጥፋትና ጥቃት ሲፈጸም እያየ ዝም የሚል የለም በረሃ ወርደው አገርን ነጻ ለማውጣት የህብንም ጭቆናና መከራ ደምሦሶ ለማጥፋት ብረት ያነሱት አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ አንድ የሆኑበትን የጋራ መግለጫ አውጥቶተው እንደሚቀሳቅሱ ተስፋ አደርጋለሁ።
ህዝብን ነጻ ለማውጣት ለህዝብ እኩልነት ለማምጣት ለሚያስቡ እና የሚታገል ታጋይ ከዚህ የበለጠ ትልቅ አጋጣሚ ከወድየትም አይገኝም ።
እናም ታጋዮቻችን አንዱን ጥለን ሌላ ችግር ሊፈጥር የሚችረስ ውጭ እታገልለታለው ለሚለው ህዝብ ደግሞ የበለጠ መከራና ስቃይን እንዲገፋ የማድረግ መብት ለበዳዩ ወያኔ መፍቀድ እንዳይሆንብን አሁን ሰዓት ላይ ነንና በዜና አውታር በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ነጻ ለማውጣት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር የጋራ ጥምረት ፈጥረው በወያኔ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም እና ወያኔን ህዝባችን ላይ የበለጠ ጥፋትና ጥቃት ሳያደርስ ለምንወደውና ለምንታገልለት ህዝባችን ለመድረስ ደቂቃዋና ሰዓቷ አሁን ነውና ጥምረታችሁን በይፋ ለህዝብ ንገሩና ወያኔን መግቢያና መውጫ ምድረ ካድሬን ደግሞ የሚናገረውን እንዲያጣ በማድረግ ህዝባችንን እየገደለ እና ንብረታቸውን እያቃጠለ አማራውን ይሄንን ያደረገብህ ኦነግ ነው ብለው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የኦሮሞ ህዝብ እየገደለ እና ንብረቱንም እያቃጠለ ያለውን አማራ ነው ብለው የኦሮሞን ህዝብ አማራው ላይ እያነሳሳ የከሰረ 25 ዓመት ሲሰራበት የነበረውን ህዝብን ከህዝብ እያጣሉና እያፋጀ ስልጣኑን የማራዘም ስራ ሁሉም ህብረተሰብ በይፋ እንዲያውቀው ፖለቲካውን በበላይ የሚመሩት አካሎች ትልቅ ድርሻ አላቸው በተለይም ደግሞ ብረት አንስተው ስለህዝባቸው እና ስለ ሃገራቸው የሚታገሉት የፖለቲካ አመራሮች ለህዝቡ ነጻነት የናንተንም የበረሃ ላይ ትግል በአጭር ግዜ ወደ አሸናፊነት የሚያመጣችሁ አንድነት ሲኖራቸው ነውና የአንድነት ዜናዎችን በቅርቡ እንደምታሰሙን ተስፋ አለኝ።
ወያኔ አሁን እየተንቀሳቀሰ ያለው በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያሉትን በተለይ ሁለቱን ብሄሮች የማጣላት ስራን ለመስራት ማንንም ሳያሳትፉ የሕወአት ሰዎች ብቻ ተሰብስበው መመሪያ አስተላልፈዋል። ከተላለፉት መመሪያ ውስጥ አደገኛውና በህዝባችን ጥፋት ላይ ያነጣጠረው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አማራ ያልሆኑ፡ ነገር ግን አማርኛ ተናጋሪዎችን በማስፈራራት አማረነታቸውን እየገለጹ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥላቻ እንዳላቸው እየተናገሩ ህዝቡን እንዲገሉ በማድረግ እና የኦሮሞ ህዝብ በአማራው ላይ እንዲነሳ ..በአማራው ክልል ውስጥ የኦሮሞኛ ቃንቃ የሚናገሩ ነገር ግን ኦሮሞ ያልሆኑትን የመከላከያ ሰራዊት በማሰለፍ የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ አማራን እንደሚጠሉ በመንገር በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሱ የማድረግ ስራ ሰርተው ህዝባችንን ለመጨፍጨፍ ወያኔ የመጨረሻውን የመፍጨርጨር የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ቆርጦ ተነስታል።
እዚህ ላይ ወያኔ እኔ ህዝብን በህዝብ የኦሮሞ ህዝብ እና የአማራን ህዝብ አጣልቶ እርስ በርስ ሲጨፋጨፉ ያኔ የኔ ስልጣን ለሁል ግዜ ይጸናል ሁለቱ ካልተጣሉ ግና ስልጣኔ ያበቃል ብሎ ከመነሻው ሲሰራ የነበረው የወያኔ ሴራ በመጨረሻዋ ህዝባችንን አጣልቶ እና አፋጅቶ አላማው እንዳይሳካለት የፖለቲካ አመራሮች በዚህ ሰዓት ግልጽ መልዕክት መግለጫ ማውጣት አለባቸው ኦነግና አርበኞች ግንቦት 7 ተዋህደው ወያኔን ለመደምሰስ አንድነታቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አስታውቁ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁሉም አንድ በመሆን ገዢው ፓርቲ በህዝብ መግለጫ ሰው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ መሆናችን ማንኛውም ህዝብ የትኛውም ህዝብ ጠላት ሳይሆን ጠላታቸው ወያኔ ስለሆነ ሁሉም በህብረት ወያኔን ለእታገል በህብረት እንነሳ የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ህዝባችንን የትግል ችቦ በመለኮስ ሁሉም ጋር እንዲዳረስ ማድረግ በፖለቲካው አመራር ላይ ያሉት ሰዎች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ ይሄ ሲሆን ወያኔ ሊሰራ ያቀዳቸውን እቅዶች ሁሉ በህዝባችን መሃል ለስልጣን ብሎ የመጠፋፋት ስራን ሊሰራ ያሰበውን ዜሮ በማስገባት ሁሉም ህዝብ ሃሳቡን ወደ አንድ አቅጣጫ በማድረግ ወያኔን በአጭር ግዜ ውስት ሆ ብሎ በመነሳት ድል ማምጣት ይቻላል።
ትግሉ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ ወደ አንድነት መጥቶ ወያኔን መቆሚያ እና መቀመጫ ማሳጣት ያለብን ግዜ ላይ ነን። ትላንትና ከፋፍዬአቸዋለው በትኛቸዋለው የቤት ስራዬንም በደንብ ሰርቼአለው ብሎ ሲኩራራ የነበረው ከእንግዲህ ወዲያ ሁሉም ስለተከፋፈሉ እየነጣጠልክ ማጥፋት ስለምችል ስልጣኔን ማስቀጠል እችላለው በማለት ሰይጣናዊ ስራን እየሰራን የነበረው ወያኔ ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ አልተለያየንም ሁላችንም አንድ ነን በማለት አንድነትን እየፈጠሩ ሲመጡ ሲያያቸው ግራ በመጋባት ከላይ እስከ ታች በወያኔ መንደር ትርምስ ተፈጥሯል። የሞት ሽረት ትግልም እያደረጉ ይገኛሉ በየግዜው ሕወአት ለብቻቸው በድብቅ እየተሰባሰቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ቢሰበሰቡም ያለ ምንም ውጤት ይለያያሉ። ከሌላውም ግዜ በከፋ እንደውም እስከ መጠፋፋት የሚያደርሳቸው መከፋፈል በመካከላቸው እንደተከሰተ ከውስጣቸው ባሉት አካላት በሰፊው እየተነገረ ነው።
ብረት ሳያነሱ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ትግሉን በከፍተኛ ሁኔታ ወያኔን በመታገል ላይ ያሉት ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ ወያኔ እየሰራ ያለውን መከፋፈል ሰብረውት ከአሁን በኋላ በኢትዮጵያ ጉዳይ ተነጣጥሎ ለወያኔ መመቸት የለም ሁላችን አንድ ነን ስለ አንድ ኢትዮጵያ በአንድነት ሆነን ለመታገል ከመቼውም ግዜ በላይ ተቀናጅተን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍና በደል እየሰራ ያለውን ወያኔን ለመታገል ውህደት መፍጠራቸው ብራቮ ኢንጅነር ይላቃል ጌትነት ብራቮ ዶክተር መራራ ጉዲና ብራቮ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በማለት በዚህ ወሳኝ ሰአት ወያኔ ኢትዮጵያን ሊያጠፋት የመጣ ኃይል መሆኑን አውቀው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአንድነቱን ድምጽ በመስማት በአንድነት ህዝባችን ጫንቃ ላይ ያለውን ወያኔ ላይ የምንነሳበት ሰዓት አሁን መሆኑን አሳይተውናል።
ሌላው የቀድሞ የኦነግ መስራች የሁኑት አሁን ደግሞ የኦዴግ አመራር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ በኢሳት ቴሌቭዝን ቀርበው ያቀረቡት ንግግር ሳዳምጣቸው ነበር። ፖለቲካ ማለት ከግዜው ጋር የሚቀያየር እንደሆነ እና የህዝብን ፍላጎት ያካተተ ትግል ወደ አሸናፊነት ብሎም ወደ ፍጹም ነጻነት የሚያስጉዝ መሆኑን ተረድተው ትግላችን ኢትዮጵያ በአንድነት የሚያስጉዝ ህዝቡንም ለኢትዮጵያ ሰላም እና ነጻነት በአንድነት የሚያስነሳ አላማ ያዘለ በመሆኑ ፖለቲካውን በአግባቡ የተረዱት አቶ ሌንጮ ለታ ትክክለኛ የፖለቲካ ሰው እንደሆኑ አስመስክረዋል። ትግሉ የዘር ጉዳይ አይደለም ትግሉ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ትግሉ የኢትዮጵያን የማዳን ትግል ነው። ለኢትዮጵያ በጋራ ስንታገል ዘር ሃይማኖት ባህል የመሳሰሉት በመሉ በአንድነት ይከበራሉ። አንድነት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ወደ አሸናፊነት እና ዲሞክራሳዊ መንግስት መመስረት ነው።
በመጨረሻም በረሃ ወርዳችሁ በድልና በክብር ወደምትወዱት ህዝብ በአጭር ግዜ በመምጣት የሚቻለው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነት ድምጻችሁን አሰምታችሁ ለህዝባችን አሳውቁን በውጭ እና በአገር ቤት የምትኖሩ ሙሁራኑ እና የፖለቲካ ሰዎች እናንተንም በአንድነት የሚያስተሳስራችሁን አዋጅ አውጃችሁ ለህዝባችን ንገሩት ያኔ ወያኔ ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ ይሆናል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች !!
መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)
No comments:
Post a Comment