ክንፉ አሰፋ
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። … የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን አያውቁትም። የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ። እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣ የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም። “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል። ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል። እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም። እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ። የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው። ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው። “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።
አጼ ምኒሊክ አምስት ሚሊዮን ጡት ቆርጠዋል ሲሉን ግን፤ ስሌቱ ላይ የቤት ስራቸውን በደንብ የሰሩት አይመስልም። በአጼ ምኒሊክ ዘመን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ቁጥሩ ስምንት ሚሊዮን ነበር። የአምስቱ ሚሊየን ህዝብ ጡት ከተቆረጠ፣ በዘመኑ ወንዶቹም ጡት እንደነበራቸው ያመላክታል። ግን ያንን ሁሉ ጡት እንዴት ሊቆርጡት እንደቻሉ ተናጋሪው አላብራሩም። ስልጣኔን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት አጼ ምኒሊክ በመጀመሪያ ያደረጉት የጡት መቁረጫ ማሽን ማስገባት መሆኑን ከጉግል ላይ በቅርቡ ሊገኝ ይችላል።
ጉግል፣ ጉግል፣ጉግል፣ጉግል፣…… እያለ መነጋገርያውን ለቆ ወረደ - የምኒሊክን አዲስ ታሪክ የሚያስተምረው።
“ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል።… ይህንንም በቅርቡ ይፋ በሚሆነው ጥናት ታገኙታላችሁ… ።” የሚል ሌላ ተናጋሪ መድረኩን ይዞ ሲናገር ከማርስ የመጣ ፍጡር ነበር የመሰለን።
ጨርቁን ጥሎ እርቃኑን መንገድ ለመንገድ የሚሄድ፤ ወይንም ደግሞ እጅና እግሩ በሰንሰለት የታሰሩ ሰው ስናይ፤ በተለምዶ ይህ ሰው አብዷል እንላለን – ውጭውን ብቻ አይተን። ጥሩ ልብስ ለብሰው በስነልቦና እና በአእምሮ መታወክ የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ እብዶች እንዳሉ ብዙውን ግዜ እንዘነጋለን። እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች በቀን ቅዠት የሚሰቃዩ፣ የስነምግባርና የሞራል እስረኞች በመሆናቸው አእምሯቸው ይታወካል። በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የአጼ ምኒሊክ ጣእረ ሞት እየመጣ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነው።
ፓልቶክን ከሰባት አመታት በኋላ መስማቴ ነው። ይህን ትልቅ መድረክ፣ አንዳንዶች ታሪክ ሰርተውበታል። ሌሎች ታሪክ ሲያወሩበት ሰንብተዋል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ታሪክ የሚያጎድፉ ጉዶች ይዘውታል። ከሰባት አመታት በኋላ የኛ ፓልቶክ ሽቅብ ሳይሆን ቁልቁል አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ቢገርመኝም፤ በአንጻሩ ግን እንደ አዝናኝም እየሆነ መምጣቱን አልጠላሁትም።
እንደሰማነው የፓልቶክ ርእሱ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አልተቀየረም። የዛሬውም መነጋገርያ ርእስ ዳግማዊ ምኒሊክ ናቸው። እኚህ መሪ ካለፉ እነሆ መቶ አመት ሆናቸው። “የሞኝ ለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ!” እንዲሉ አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ስለ አጼ ምኒሊክ አውርተው ሌሊቱንም ይመለሱበታል። ዛሬ ግን ወሬውም፣ ስድቡም ያለቀባቸው ይመስላል። ዛሬ ስለጀኖሳይድ እያወሩ አይደለም። ይልቁንም ጀኖሳይድ እያወሩ ነበር። ወንጀሉን ራሳቸው በቃል እየፈጸሙት…።
ሌላኛው ተናጋሪ ተራውን ጠብቆ መነጋገርያውን ያዘ። የተለመደውን የአጼ ምኒሊክን አጽም ከመቃብር እየጠራ ካወገዘ በኋላ፤ እንዲህ ሲል ተናገረ። “…አበበ ቢቂላን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ አድርገው ታላቅ በደል ፈጽመውበታል።”
መቼም ወደው አይስቁ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች እንኳ አይፈረድባቸውም። ገና ሃገር ሲለቅቁ የለቀቁ ስለሆኑ ለክርክርም አይመቹም። ”አበበ ቢቂላ በሮም እና በቶክዮ ላይ የሮጠው በአጼ ምኒሊክ ዘመን ነው።” ብሎ ከሚከራከር ሰው ጋር ሙግት መግጠም እብደት ይሆናል።
“የቁቤ ትውልድ ነን።” የሚል ሌላ ታናጋሪ ደግሞ መጣ። ይሄኛው ደግሞ የቆሪጥ መንፈስ የሰፈረበት ሳይሆን አይቀርም። የሚያወራው ሁሉ ስለ መቁረጥ ብቻ ነው። ሚኒሊክ ጡት፣ እጅ፣ ቆለጥ፣ እግር፣ ጥፍር… ቆርጠዋል አለን። እንደታናጋሪው ከሆነ እኚህ መሪ ያልቆረጡት ብልት የለም። ሃገር ማስተዳደሩን ትተው አስራ ሁለቱንም የሰውነት አካል ሲበልቱ ኖሯል!
አርፍደው የሚገቡት ተሳዳቢዎች ከአፋቸው የሚወጣውን ጸያፍ ስድብ ለመድገም ይዘገንናል። በ”ምሁሮቻቸው” ገለጻ መሃል እንደ አዝማች ጣልቃ እየገቡ በአማራው ህዝብ ላይ ይወርዱበታል። በዚህ ሁሉ መሃል ትንሽ የገረመኝ አንድ ክስተት ነበር። የክፍሉ መሪ በስድድቡ መሃል ገብቶ በኦሮምኛ እንዲህ ሲል ተናገረ።
“ጀሪን ወል አኛተኑ። ማይኪ ኢቲ ኬኒ። ኑ ሂንደጌኛ”።
ወደ አማርኛው በግርድፉ ሲመለስ፣ ”ማይኩን ስጣቸው። እነሱ እርስበርስ ይባሉ። እኛ እንሰማለን።” እንደማለት ነው። ዋናው ጨዋታ እዚህ ላይ ኖሯል። ምክንያቱም ይህንን ውግዘት እና ውርጅብኝ ሜንጫዎቹ ያለምክንያት በዚህ ሰዓት አላነሱትም። ነብሳቸውን ይማርና አፄ ምኒሊክ ካረፉ 100 አመት አለፈ። የሙት አመታቸው መከበር ከጀመረ ደግሞ 70 አመት ሆነው። ይህንን ወቅት ጠብቆ በአማራ እና በክርስትና እምነት ላይ ለመዝመት የሚደረገው ሙከራ፣ ግብታዊ ሳይሆን በጥናት የተደረገ ስለመሆኑ ያመላክተናል። ግርግር በመፍጠር እና ዜጎችን እርስበርስ በማባላት፣ ትንሽ የፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚፈጸም የፖለቲካ ዝሙት መሆኑ ነው።
ልብ በሉ! የዚህ የሜንጫ ዘመቻ መሪዎች ኦሮሞዎች አይደሉም። አብዛኞቹ በግማሽ ከሌላ ዘር የሚወለዱ ናቸው። በእምነታቸውም ሆነ በዘራቸው የተቀላቀሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ።
ስድስት ሚሊየን አይሁዶችን የፈጀው አዶልፍ ሂትለር ግማሽ አይሁድ እንደነበር አንዘንጋ።
No comments:
Post a Comment