Sunday, August 24, 2014

በኢትዮጵያ ሕዝብ መራራ ትግል እብሪተኛው የወያኔ መንግስት መውደቁ አይቀርም!!

በኢትዮጵያ ሕዝብ መራራ ትግል እብሪተኛው የወያኔ መንግስት መውደቁ አይቀርም!!

በኢትዮጵያ ሕዝብ መራራ ትግል እብሪተኛው የወያኔ መንግስት መውደቁ አይቀርም!!

Gezahegn Abebe  (ገዛኸኝ አበበ) 
የኢህዲግ ወያኔ መንግስት   የስልጣን ወንበር በትሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአኖኖር ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እያሽቆለቆለ እና እየወረደ በመምጣቱ ከምቼውም ጊዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ኑሮን መቋቋም በማይችልበት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ መኖር ከባድ ፈተና እየሆነባቸው እንደሆነ የችግሩ ሰለባና ተጠቂ የሆኑት ሰዎች በየጊዜው ከሚያሰሙት ሮሮና ጩኸት መረዳት ይቻላል:: በአሁኑ ወቅት ጥቂትየስርአቱ  ደጋፊዎች እና የወያኔ ካድሬዎች ካልሆኑ በስተቀር የኑሮ ውድነቱን መቋቋም በማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል::
  በአሁኑ ሰአት መንግስት የሚያራምደው ፖሊሲ የመላው ኢትዮጵያን ሕዝቡ ፍላጎት እና ጥቅም ማዕከል ያላደረገ ሲሆን የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል :: ሁሉን የኢትዮያ ህዝብ እና ክልል ተጠቃሚ ያላደረገው የመንግስት የልማት ስትራቲጂ ፖሊሲ እና በመላው ሀገሪቱ ላይ በስፋት ተንሰራፍቶ ያለው ሙሰኝነት ከእለት ወደ እለት የሕዝቡ የአኖኖር ሁኔታ  እያሽቆለቆለ እና እየወረደ እንዲመጣ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ ለኑሮ ውድነቱ ግንባር ቀደም ተጠያቂው ሀገሪቱን እየመራው እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት በፍጥነት እያሳደጉኝ ነው የሚለው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ነው::
 ታስታውሱ እንደሆነ የወያኔ ቁንጮ የነበሩት ሞቹ የቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስት መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት  በአሥር አመት ዉስጥ «ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ትችላለች። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርጋለን» ብለው ነበር ነገር ግን ይህ የአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር  የውሃ ላይ ሽታ ሆኖ ቀረ :: በአንጻሩአቶ መለስ  የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሶስቴ እንዲመገብ እናደርገዋለን ያሉለት  ኢህአዲግ  ኢትዮጵያን በብቸኝነት በሀይል መግዛት ከጀመረ  23 አመት እየተጠጋ ሲሆነው በእነዚህ አመታቶች ውስጥ  ምንም የተለወጠ ነገር የለም:: የወያኔ መንግስት በተቆጣጠረው በመገናኛ ብዙሃን እንደሚለፈልፉት የኢትዮጵያ ኢኮነሚው ዕድገቱ በፍጥነት ሽቅብ እየገሰገሰ ሳይሆን ወደታች እያሽቆለቆለ ይገኛል::  ኑሮ እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ የሰዉ የአኖኖር ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ዉስጥ ዉስጡን የሚያልቁት ወገኖቻችን ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።
  በመላው አገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በአገሪቷ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዉጭ ምንዛሪ እጥረት እየታየ ሲሆን  በኢኮኖሚ ችግር  የተነሳ ሕዝቡ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመገገኘቱ በማንኛውም ጊዜና ሰሀት ግባታዊ ሕዝባዊ አመጽ ሊነሳና ትልቅ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸዉ።ደግሞሞ አይቀርም
 በአሁኑ ሰአት እንደሚታየው እና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል ህዝቡ ሀገሪቱን እየመራ ባለው የወያኔ መንግስት ለመመራት ፍቃደኛ አይደለም ከየቦታው የሚሰማው እና የሚታያው የሰበዓዊ መብት ረገጣው አፈናና ግድያው ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ በየቀኑ እየተባባሰ የመጣው የኑሮው ውድነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ  ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆነው እንዲቀጥሉ እያደረጋቸው ነው::ከዚህም የተነሳ መንግስት በየቀበሌው፣በየመስሪያ ቤቱ የሚጠራቸው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ለመገኛት ፍቃደኛ እና ደስተኛ እንዳይደለ ምንጮቻችን ይገልጻሉ:: ነገሮች በዚህ አይነት ሁኔታ ሊቀጥሉ አይችሉም:: የመረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱን ለማስከበር ሆ ብሎ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳቱና አንባገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ገርስሶ መጣሉ አይቀርም:: ስንቶቻችው በእኔ ሀሳብ ትስማማላችው::

   ውድቀት ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት!!!
ገዛኸኝ አበበ ነኝ 

No comments:

Post a Comment