Sunday, August 24, 2014

የተስፋኞች ትውልድ በተስፋ ቢስዋ ምድር

“የሶስተኛው አለም የለውጥ ሱናሜው ቀስቃሽ ወጣቱ ነው!” ሀ ሁ ... በል,
እኔም ኤ ቢ ሲ ... ልበል
ሳምሶን ሳህሌ
መንደርደሪያ፡
ይህ አጠር ያለች መጣጥፍ ፡ ቁም ነገር አዘል ስንቅ ባላሰብኩት ሰዓትና ግዜ ያጋጠመኝን የነገር ዱብ እዳ ለናንተ ላካፍላችሁ በማለት እነሆ እንደኔው እያዘናችሁ፤ እየተበሳጫችሁ፤ ውስጣችሁ እየተብሰለሰለ አንብቡት። ካልሆነም እየሳቃችሁ ፤
እየተገረማችሁ ማንበብ ይቻላል። ማልቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
የገጠመኝ ዱብ እዳ እዳለ ለእናንተ ለማካፈል ፈለኩ። በውስጡ ያነሳቸው ነጥቦች ለኔ እንደገባኝ ወጣቱን የሚያብጠለጥልሲሆን ፤ በወጣትኛው ቋንቋ ግን ሊዋጥላቸውና የማይቀበሉት ነጥቦች ተካተዋል። የእንግሊዘኛውን ውይይት ነጥብ በነጥብ ወደ አማርኛው እንዳለ ቀርቧል። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ለቀረበው ጥሬ ነጥቦች ስሜት የሚነካ ቃላቶች/ መልክቶች ካሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ዋናው ነገር አንባቢው በገባው መንገድ መተርጉም ይችላል ። መልካም ንባብ።
፩: አንደተለመደው ከምሳ በኋላ ከመሰሪያ ቤት ወጣ ብዬ ቡና ለመጠጣት ባካባቢው ወደ ሚገኝው ካፊ ገባሁ። ቡናዬን እየጠጣሁ የእለቱን ጋዜጣ አነባለሁ። ወቅቱ የአፍሪቃ fg የሕብረቱ ምስረታ በዓል የተዘከረበት ሳምንት ነበር።
ስለ በዓሉ አከባበር አጠር ባለ መልኩ በዚሁ ድህረ ገፅ ላይ ቀርቧል። ወደ ነገሬ ልመለስ። ሳላስበው ጎርነር ባለድምፅ ከጉኔ ለመቀመጥ ፍቃደኝነቴን ጠየቀኝ። ሳላቅማማ በርግጥ ይቻላል ብዬ ጋዜጣዬን ማንበብ ቀጠልኩ። በርግጥ የኔ ቤት አይደል ወይም ወንበር አላከራይ:: እንደተለመደው ፈገግ ብሎ ተቀመጠ ፡፡ አቀማመጡና አስተያየቱ አስገራሚ ነበር፡፡
በቃ ጉድ ፈላ, አቀማመጡ ለነገር እንደሆነ ተረዳሁ፡፡ ልቤ የነገር መንጠቆዋን ዘረጋች ፡ የማይገባኝ ስሜት ልቤን
ነረተው፡፡ አልፈነዳ ነገር ፡ እሱ ምን አገባው የኔን ደረቅ ስሜት የሚያዳምጥ ፡፡
፪: የረዘመውን ጢሙን እያፍተለተለ በአትኩሮት ተመለከተኝ፡፡ የማይገባ /የማይመች አስተያየት፡፡
“ጄፍሪ እባላለሁ” ኦጁን ዘረጋ፡፡
“ሳም እባላለሁ” ተጨባበጥን፡፡
“ትንሽ ነገር ቀመስ ትመስላለህ፡ ደግሞም ትምህርት የገባህ ጥሩ አመለካከት ያለህ ትውልድ - ግን ከዘመኑ ትውልድ
የምትለይበት ማስረጃ የሌለህ ነህ”፡፡
“አልገባኝም ለምን እንዲህ አልክ፡፡ አንተዋወቅ”፡፡
“ይግባህ - ለምን ይህን የጃጀውን ጢሜን እንደማሳድግ ታውቃለህ?”፡፡
2014
2
“በእርግጥ አላውቅም - ግን አዛውንቶች ስለምትወዱት ፡ ደግሞም ያምርባችዃል”፡፡
“ስላረጀሁ ወይም ሴቶች ስለሚወዱት አይምሰልክ”፡፡ የነገር ቋቱን ዘረገፈው ፡ ዘረገፈብኝ፡፡
“በጣም በዚህ ትውልድ ውስጤ ስለበገነ ብቻ ነው፡፡ ሀገሬ ለምላት ምድር ሊረከብ የሚችል ትውልድ ስላጣሁ :: ቆሻሻ
ትውልድ ፡ ወሽካታ ብቻ፡ ወንጀለኛ ትውልድ፡፡ ይህ ነው ምክንያቴ”፡፡
በውነቱ ነገሩ ትንግርት ሆነብኝ፡፡ አምላኬ ቸር አሰማኝ ብዬ በልቤ ፀሎቴን አደረስኩ፡፡
ዩንቨርስቲ በነበርኩበት ወቅት የህግ መምህር የነበረውን አስታወሰኝ ፡፡ አንድ አይነት ባህሪ፡፡ ይህ የህግ መምህር
ካልጠጣ የልቡን: የችሎታውን ማስተማር አይችልም፡፡ ቡናውን ሁለቴ ተጋተው፡፡ ጋሽ ስብሃት ነብሳቸውን ይማረውና
፡ የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ በሚሰሩበት ወቅት ጠዋት አረቄ ካልጠጡ እንደማይጽፍ ይነገር ነበር፡፡ የነፃው ፕሪስ
ውልደት ስሞን ከጋሽ ስብሃት ጋር መገናኝት ጀመርኩ፡፡ አንድ ውቅት ቤተ መፃህፍት ውስጥ ተገናኝን፡፡
ጋሽ ስብሃት በማንኛውም ቀን ከሚለብሱት ልብስ መሀከል ሹራብ መልበስ ይወዳሉ፡ ጢማቸውም ረዘም ብሎ
የማሻሸት ልምድ አላቸው፡፡ አንድ ወቅት ለምን ሹራብ መልበስ እንደሚያዘወትሩ ጠየኳቸው፡፡ መልሳቸው እንዲህ
ነበር፡፡
“ሹራብ በጣም ይሞቃል ... በቃ: ሙቀቱን ላንተው ብቻ ይሰጥሃል፡፡ እንደሴት፡፡ ሴት ስታቅፋት ሙቀቷ አይጠገብም
አይደል ... ገላህን የሚያግል ሙቀት ... በቃ መጋጋል: ለነገሩ አንተ አይገባህም ገና ወጣት ነህ ... መንገደኛ ልብና ገላ
ይዘህ የሹራብ ጥቅሙ አይገባህም .. በቃ ይህ ነው ምስጢሩ”፡፡ ሰውየው እንደ ጋሽ ስብሃት ተመሳሳይ ባህሪ አለው፡፡
ወደ ነገሬ ልመለስ፡፡
“ይህ ትውልድ መናጢ ነው ብልህ ቅር ይልካል?፧ ስለማንነት ሊገባው የማይችል ልቡ የደነደነ ማንነቱ ያልገባው የጭቃ
ትውልድ - ጭቃ በትክክል አትቆምበትም - ያሟልጭሃል : እንደዛው ናቸው, የዘመኑ ትውልድ, በትውልድ ዘመኑ
ማድረግ የሚገባውን ማድረግ የግድ የማይለው/ የማይላት- ወሽካታ ትውልድ::
“ይቅርታ አፍሪቃዊ ነኝ, የአፍሪቃን አየር, አፈር, ውሃ የቀመስኩ በኦሪት ዘመን ከተፈጠረ ትውልድ የመጣሁ ማንነት
የሚያንገበግበኝ ግለሰብ” ::
፫ ፡ “ከየት ነህ?”
“ከኢትዮጵያ?”
“ኦ -- ከታላቋ ምድር, ባህል ጠባቂ, የቋንቋ የእምነት መገኛ ምድር, ግን ስንቱ በቡዳ በላችሁ: በተለይ እንደኔ የጥቁር
ክልስ መልክ ያለው ነቀርሳ”፡፡
ትንፋሹን ዋጥ አደረገ: አንገቱ አቀረቀረ፡፡ በጣም ግራ የሚያጋባ ንግግር ለምን እንዲህ ሊል እንደቻለ ግራ የሚያጋባ፡፡
ይህ ሰው መልኩ የጥቁር ክልስ አነጋገሩ ቀልቡ ሁሉ አፍሪካዊ፡፡
2014
3
“እኔም ከታላቋ ደቡብ አፍሪቃ ነኝ”
“ኢትዮጵያ በሐይማነቷ የኮራች, የተባረከች: ሀገረ እግዚሃብሄር:: ትውልዷ ግን የማይታዘዟት, የማይከተሏት, ከልቡ
አውጥቶ የጣላት ነው ያላት:: እዚህ የምታየው ወጣት ሆዱን ገልብጦ የሚሄድ, ገላውን, ፊቱ በምናምንቴ የተበሳ
በማይገባው ቋንቋ ገላው የተበጣ, ሰለ እምነቱ በድንቁርና የሚጠበስ ታዲያ እንዴት ፈጣሪ እጁን የሚዘረጋው፡፡ አንተና
አንተን መሰሎችህ ብዙ ስራ ይጠብቃችኋል፡፡ ወጣቱን መልሱት፡ የፈረኝጅኛው እምነት, ባህል, ቋንቋ አይሰልቅጠው::
አስተምሩት, ስለሃገሩ አሳቢ, ስለእምነቱ አስተዋይ እንዲሆን ጠግኑት፡፡
በውነት ንግግሩ አሰገራሚ ነው፡፡ የነገር ቋቱ ገና አላለቀም፡፡ እኔም ንግግሩ ስለገረመኝ ቡና ደገምኩ፡፡ እሱም ደገመ፡፡
በነገር ለመጫጫስ፡ አስገራሚ ቀን፡፡
፬፥ “በርግጥ ኤትዮጵያ የራሷ ፊደልና ቁጥር ያላት ሀገር ፡ አይደል?”
“ በርግጥ አዎ, የራሳችን አለን”
“አየህ አንተ ሳትወለድ ወይም ትንሽ በነበርከበት ዕድሜ ወደ አንተ ሀገር መጥቼ ነበር:: ያኔ ደቡብ አፍሪቃ በአጣብቄኝ
ውስጥ በነበረችበት ወቅት ለጦር ልምምድ ሻሸመኔ ነበርኩ:: ለስልጠና ከዚያም ከአመታት በሆላ ወደ ትግል ሜዳ
ከትግል ጏዶቼ ጋር አመራሁ:: የዛን ግዜ ነበር የእናንተን ቋንቋ, ባህል, እምነት ለማወቅ አጋጣሚ ያገኝሁት:: አንተ ሀ ሁ
ስትል እኔ ኤ ቢ ሲ እላለሁ... ይህ ነው ስለ አንተ ቋንቋ የማውቀው, ከዛ ሀ ሁን ለመድኩ። ዛሬ ደግሞ ከነፃነት
ማግስት ይኸው አዚህ እገኛለሁ፡፡ ግን ባህሌን, እምነቴን ጠባቂ ለዚህም ማረጋገጫ ባይገኝም ቃሌ -አነጋገሬ
ይመስክር”፡፡
“ለመሆኑ ይህ ትውልድ ቋንቋ ባህል እምነት ጠባቂ ይመስልሀል? በተለይ ወጣቱ ወደ ነጭ ምድር ሲመጣ አባዜው
ይነሳበትና የሚያረገውን ያሳጣዋል፡፡ እብደት ይጀምራል፡፡ አተንም ከሆንክ የራስክ ጉዳይ፡፡ ልጅ ስትወልድ ገና ከእናቱ
ሆድ እያለ ቃል አስገባው፡ አንተን እንዲመስል”፡፡
፭፡ “ኤትዮጵያ ለጠላት የማትንበረከክ, ለኛ አፍሪቃውያን ምሳሌ የምትሆን ሀገር: የምስራች የምትባል ምድር:: ጏድ ማንዴላ
በሮቢን አይላንድ እስር ቤት እያሉና ከውጡም በኋላ ከወጡም በዃላ ስለ ኤትዮጵያ ይመሰክሩ ነበር፡፡ታዴያ ዛሬ ምን
ነካቹህ? በራሳቹህ ሰው የምትበሉት? እርስ በእርስ መባላት:: አንተና ወጣቱ ምነው ወኔያቹህ ጠፋ? ይህን ትውልድ
ይዘህ ነው ኤትዮጵያዊ ነኝ የምትለው? ሀ ሁ ብለህ ፊደልህን እንደቆጠርክ ወጣቱን ከሀ እስከ ፐ አስቆጥረው፡፡ ከገባው
፥ ከዛ በሆላ ፖለቲከኛ ብሎም ለሀገር ታጋይ ይሆናል፡፡ ይህ ነው የምልህ ከልብህ ካመንከኝ”፡፡
፮፥ “ለምንወደዚህ ሀገር: ኒውዝላንድ መጣህ?” የማያገባው ጥያቄ::
“ አንተ ለምን መጣህ?”
2014
4
ይህ ሁሉ ድንፋታ በውነት ምን ያህል ሀገሬንና ታሪኬን ቢያውቅ ነው:: በመሀከላችን ፀጥ እረጭ አለ። ደማሚት
ቢፈነዳ የማንሰማ ሀውልት መሰልን።
፯፡ “ደግሞ ስማ, አፍሪቃ ተዋርዳለች: የበለፀገው ሀገር ባህልና ቋንቋ ሲውጣት, የራሷ ደግሞ ወደ ከርሰ ምድር ሲጣል ምንኛ
ያንገበግባል። ስለ አፍሪካ ስናወራ ስለኤትዮጵያ አይቀሬ ነው። እኔ እንደምታዬኝ ሰው አይደለሁ?፣ በጣም አፍሪቃዊነት
የገባኝና የማምን ነኝ። አፍሪቃን ከውርደት የምታድኑአት እናንተ ወጣቶች ናችሁ ግን ወኔ የሌለው በተለይ የሀገርክ
ወጣት ሀገራችሁን ከሲኦል ፈተና አውጧት። አፍሪቃ ብዙ ፈተና አላት።
፰፤ መደምደሚያ
“በጣም በገነፈለ ስሜት ጎዳሁክ መቼም ይገባሀል አይደል?”
“እረ ምንም አይደል, ደግሞም ስለወቅቱ የፖለቲካ ጡዘት ነው የተወያየነው”።
“ እምነትክ ኦርቶዶክስ ነው ያልከኝ?”
“አዎ ኦርቶዶክስ ነኝ”
“ ጠዋት በማለዳ ፀሎት አድርገህ ከሆነ መሰናክሎችህና አጋጣሚዎችህ በሙሉ ጉድ ይፈላባቸዋል። ግን እንደዚህ መናኛ
ትውልድ ከሆንክ እምነት፣ ፀሎት የማይገባህ ከሆነ ጉድ ይፈላብህል። አይንህ ካልታወረና ካልታወረባቸው: የአረቡ
ወጣት ምሳሌ ይሆናችዃል። የሶስተኛው አለም የለውጥ ሱናሜው ቀስቃሽ ወጣቱ ነው። የመጀመሪያም የመጨረሻም
እነሱ ናቸው።
፱፡ “ይህ ትውልድ እንደ ክርስትና አባቱ/ አባቷ በአንገቱ/ በአንገቷ ላይ ሰይጣንን የሚዋጋበት ማተብ ካላሰረ ወይም እንደ
መነኩሴ በየሰዓቱ ካላደረሰ ይቅር የሚለው አይኖርም፡፡ ይህ ትውልድ የቴክኖሎጂ ዲቃላ ነው ብልህ ከእውነት የራቀ
ይመስልኸል?፡፡ በጣም የጏጏኹት ሞቴን ነው, በቃ - መሞት ከዛም ይህ ጭራ ቀረሽ ትውልድ ምን እንደሚገጥመው
በሰማይ ቤት ሆኖ መሰማት: ያም ገነት ከገባሁ ፡፡ በጣም መተንፈስ ያለብኝን ዘረገፍኩልህ፡፡ የውስጥ እፎይታ በቃ -
የሰላም ጉዞ”፡፡
“አይኑን አፈጠጠብኝ፡፡ መልካም ሰው - የሰው ስሜት የሜገባህ ጥሩ አዳማጭ”፡፡
“ማ! እኔ እረ: አይገባኝም”::
“ምነው, ሹመት ሳይሆን ማንነትክን ስለነገኩህ ነው?”
“ሳይሆን - ብዙ አንተዋወቅም”
“አፍሪቃዊ ብቻ መሆን አይበቃም? ደግሞም የምትኮራበት ኤትዮጵያዊነትክ: እኔም በጥሞና አውቃለሁ የምትናገረውንም
ቋንቋ መናገር እችላለሁ”፡፡ ፈገግ ብሎ ፈርጠም ባለ አጨባበጥ ጨበጠኝ፡፡
“አየህ እኔ እብድ አይደለሁም:: እንደው ጨዋታ ስለጀመርን:: አፍሪቃዊ ደግሞም - ኤትዮጵያዊ - የያኔው ቡዳ ሳይበላቹህ
- ሌላ ግዜ እንገናኝ”፡፡
2014
5
በድጋሚ ተጨባበጥን:: ስልክ ተላዋውጠን, በቀጠሮ ተለያየን፡፡ በቃ አስገራሜ ቀንና ገጠመኝ፣ እውነት ነው ያጫወተኝ,
ቁም ነገር ሁሉ, የዘመኑን ትውልድ ጉድ የሚዳስ ነው፡፡ ቀሪውን ለአንባቢ አተወዋሁ፡፡ በተመቻቹህ መንገድ
በሚሰማችሁ ስሜት መተርጎም ይቻላል፡፡ እኔም ጨረስኩ፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡
ፀሐፊውን ለማግኝት ይህን ኤሜል ይጠቀሙ፡ ethiofreemedia@hotmail.com

No comments:

Post a Comment