ምን እንደሆነ ባላውቅም የዛን ትውልድ ታሪክ ለማውቅ በጣም እጓጓለው፡፡ከተፈጥሮአቸው ይሁን ይከተሉት ከነበር ህቡዕ የፖለቲካ አደራጃጀት በማላውቀው መልኩ ስበዙ ሚስጥረኞች ናቸው።
ለምሳሌ ሻብዕያና ወያኔ መንግስትም ሆነው ድብቅ ናቸው፡፡አንድ ጊዜ አቶ በረከት ስምኦን ይንን ድብቅነታቸውን ተናግሮ ነበር።በአንጻራዊነት ወያኔ ሳይሻል አይቀርም የኛ የፖለቲካ አምላክ እያጋጨ ይከፈሉና አንዱ አንዱን ስነካ በመሃል እኛ ወሬ እንቃረማልን።( የወያኔ ሁለት ቦታ መከፈል ልብ ይሏል 1993)።ሻብዕያ እስከ ዛሬ ለዜጎቹም ሆነ ለታሪክ የሚሆን የትግሉን ሚስጢር ያውጣ አይመስለኝም።
በደርግ በኩል ከሞላ ጎደል አያሌ መጻሃፍ ስለ ተጻፉ ችግር የለውም።በኢህአፓ በኩልም ብዙ ተብሏል።
ነገር ግን እንደ ዜጋም እንደ ተከታይ ትውልድም የአባቶቻችንን ታሪክ ማውቅ ነበረብን።እንዳውም ሞተው ከማለቃቸው በፊት ለታሪክ ሰነድ የሚሆን ዳጎስ ያለ መጽሃፍ ቢያሳትሙልን ሌላው ቢቀር "ነፍስ ይማር" እንላለን።
ነገር ግን እንደ ዜጋም እንደ ተከታይ ትውልድም የአባቶቻችንን ታሪክ ማውቅ ነበረብን።እንዳውም ሞተው ከማለቃቸው በፊት ለታሪክ ሰነድ የሚሆን ዳጎስ ያለ መጽሃፍ ቢያሳትሙልን ሌላው ቢቀር "ነፍስ ይማር" እንላለን።
ይህቺን እንደ መግቢያ ከጠቀምኩኝ ወደ አቶ ሌንጮ ለታ የኢሳት ቃለ ምልልስ ላምራና ትኩረቴን የሳቡትን ነጥቦች ላንሳ፥
አቶ ሌንጮ ለታ በአገር ቤት ዩንቨርስቲ ውስጥ( አአ ዩንቨርስቲ) አለመማራቸውንና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአሜሪካ እንደ ወሰዱ ስሰማ ለመጀመሪዪ ነው።በመንግስት ስራም በኩል ጥቂት ዓመታት ብቻ እንደሰሩና ወደ ሜዳ እንደወጡ ተናግረዋል።የሙሉ ዕድሜ ታጋይ ብለን እንለፍ።
ስለ ኦነግ
ጋዜጠኛው ሲሳይ አጌና ያቀረበላቸው ጥያቄ በሁሉም ሰው ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለስ በመሆኑ ተገቢ ጥያቄ ነው።
"ኦነግ ሰፊ ህዝብ ይዞ ሰፊ ክልል ይዞ በትግሉ እንደ ሻብዕያና ወያኔ ለምን አልቀናውም…"የሚል ነው ቃል በቃል ባይሆንም።
አቶ ሌንጮ ለታ "ችግሩ ከእኛም ሊሆን ይችላል…"ብለው ጀምረው፥አሁንም ለኔ አዲስ ታሪክ የሆነብኝን ተናግረዋል።
"ኦነግ በምስራቅ በኩል ከደርግ ብቻ ሳይሆን ከሱማሊያ ሰርጎ ገቦች ጋር ጭምር ስዋጋ እንደ ነበረ፥ደርግ ከገደላቸው ታጋዮች ይልቅ በሱማሊያ የታጠቁ ሰራዊት የተሰው ታጋዮች ይበልጣሉ ብለዋል፡፡
አቶ ሌንጮ ለታ ቀጥለው፥በምዕራብ በኩልም ተመሳሳይ ችግር ነው የገጠመን።በጆን ጋራንግ የሚመራው SPLA የተሰኘው የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ግንባር ከኋላ የደርግ መንግስት ከፊት ሆነው ይውጓቸው ነበር።
በእርግጥ የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ግንባር ጋምቤላ ውስጥ "ቢልፋም" የተባለ የጦር ማስለጠኛ ካምፕ መንግስቱ ሰጥቷቸው የተደራጁ ናቸው፡፡ነጻ ከወጡም በኋላ ለዚህ ቦታ መታሰቢያ ይሁን ዘንድ "ቢልፋም" የተባለ ካምፕ ዋና ከተማቸው ጁባ ላይ እንዳለ አንድ ወዳጄ አጫውቶኛል።
እንግዲህ እነሱ የመንግስቱ ሃይለማርያምን ውለታ ለመመለስ ኦነግን ቢወጉ አይገረምም።የሱማሌ መንግስት ግን ይገረማል።ከመንግስቱ ጋር ባለ አንጣም ሆኖ እነሱን ከወጋ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
ለነገሩ አቶ ሌንጮ እዛው ላይ መለስውታል።የዚያድባሬን ቅዥት።
ስለዚህ ኦነግ ከአገር ውስጥ ገዢ መንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከጎሮቤት አገሮችም ጭምር ስዋጋ የተፈለገውን ያህል መራመድ ሳይችል ቀርቷል።
ወያኔና ሻብዕያን እንዲህ ዓይነት ቻሌንጅ እንዳልገጠማቸውም ጠቅመዋል።እንዳውም "ደርግን ያሽነፈ ደርግ ነው" ስሉም ደርግ አገሪቷ አላት የሚባሉትን ጄኔራሎች በመረሽን የሰራዊቱን ሞራል ገድሏል።በዚህ ጊዜ ወያኔና ሻብዕያ ደርግን ገፋት እንጂ አላሽነፋትም አስቀድሞ እራሱን በራሱ ገድሏል።
ኦነግ ከወታደራዊ ባሽገር በዲፕሎማሲም እንቅስቃሴ ያደርግ እንደ ነበር።ተናግረዋል ኦቦ ሌንጮ፡፡ጋዜጠኛው ሲሳይ አጌና ያቀረበላቸው ሌላውና ዋነኛ ጥያቄ የመገንጠል ጥያቄ ነው።
ወደ ቀጣዪ ክፍል ከመሄደ በፊት ስለ ደርግ ምን አሉ? ጋዜጠኛው ስለ ድርድር ስጠይቃቸው እንዲህ አሉ
"አንድ ግዜ አንድ ደብዳቤ ተልኮልን ነበር፥እንዴት እንደ መጣችም አናውቅም፥እኛ ግን ጊዜ አለነበረንም" ፈገግ አሰኙኝ፡፡
"አንድ ግዜ አንድ ደብዳቤ ተልኮልን ነበር፥እንዴት እንደ መጣችም አናውቅም፥እኛ ግን ጊዜ አለነበረንም" ፈገግ አሰኙኝ፡፡
በተያያዘ ጉዳይ አንድ ግዜ በ1977 ረሃብ ለትግራይ ህዝብ የተላከውን እርዳታ ወያኔ ለግል ጥቅሙ አውሎታል ተብሎ በቢቢሲ ሳይቀር ስያጋልጡ ሟቹ ጠ/ር እንዲህ ብለው ነበር።
"እኛ በትግላችን ታሪክ ከደርግ ጋር የተደራደርንበት ነጥብ ቢኖር፥ ለህዝቡ የመጣው እርዳታ እንዲያልፍ የተኩስ አቁምና መንገድ እንዲከፈት ብቻ ነው" ብለዋል።
የአንድ አገር ልጆች ተመሳሳይ ትውልድ!
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለአቶ ሌንጮ ለታ ያቀረበላቸው ጥያቄ አሁንም የብዙሃን ጥያቄ ነው።በነገራችን ላይ ሲሳይ አጌና "ኢትዮጵ" የተስኘች ዝነኛ ጋዜጣ ባለቤት የነበረ ነበር፡፡
እንዲህ አለ በአጭሩ ኦነግ ለምንድነው የመገንጠል ዓላማ ይዞ ተነሳ የሚል ነው(ቃል በቃል አይደለም)
ኦቦ ሌንጮ በወቅቱ ስንነሳ ለትግል ወደ ሜዳ ስንገባ ይህ ጥያቄ ፍትሃዊ ጥያቄ ነበር አሉ።
ኦቦ ሌንጮ በወቅቱ ስንነሳ ለትግል ወደ ሜዳ ስንገባ ይህ ጥያቄ ፍትሃዊ ጥያቄ ነበር አሉ።
ትክክል ናቸው፡፡የነበሩበት ሁኔታ የሚከተሉት ረእውተ ዓለም ያስገድዳቸዋል ተግቢ ነበር።
ለምን ቢባል ኦሮሞ እና ኦሮሚያ የምትባል የማትታውቅበት ጊዜ ይህን ህዝብ ማሳወቅና መብቱን መጠየቅ ትክክል ነበር፡፡
"ይህ ዕሳቤ እስከ 1991 ትክክል ነበር" ብለዋል እሳቸው፡፡እሳቸው ያሉትም እኔም በግሌ የምጋራው ሃሳብ ቀጥሎ ያለው ነው።
እኔ ለአቅመ ፖለቲካ ደረሼ እስከ ዛሬ ድረስ የኦሮሚያን መገንጠል ከማይደግፉ አንዱ ነኝ።ምክንያቴን በምሳሌ ላስረዳ?
አንድ አባ ወራ ብዙ ልጆች ያሉት ሚስቴና ልጆቼ አስቸገሩኝ ብሎ ቤቱን ትዳሩን በትኜ ከለውጣው ብሎ ቤቱን ቢቀውጠው…አስቡት ሚስቱን ልጆቹ የሚሆኑትን ስያጡ? ያለ አባውራ ቤቱ ምን ይሆናል?
የዛን ግዜ በቃ እኛ ከአሁን በኋላ አናስቸገረህም ብቻ አትሂድብን ብሎ ቤተሰቡ መለማመጥ ይጀምራሉ፡፡ያኔ አባውራው ተገቢውን ክብር ከአገኘ ጨክኖ ቤተሰቡን አይበትንም።እንዳውም እምቢ ካሉ አንድ በአንድ ማባረር ይችላል።
ኦሮሞ የኢትዪጵያ አባውራ ነው።ካልተገነጥልኩ ብሎ በኦነግ በኩል ስያስቦካ የሚንጫጩት ሌሎች ብሄር ብሄርሰብ ናቸው።እውነት አላቸው ያለ ኦሮሚያ ኢትዮጵያ ኦና ነች።ኦሮሞ እንደ ስፋቱና ብዛቱ እንደ ሃብት መጠኑ የሚገባውን ካገኘ እውነተኛ የሃብት ክፍፍል ከተደረገ ወዴትም መገንጠል አይችልም።ግን የአባውራነቱን ስፍራ ሊያገኝ ግድ ይላል።
እንግዲ የኔ እሳቤ ተንጽባርቆ ያገኘሁት በአቶ ሌንጮ ንግግር ውስጥ ነው። "የመገንጠል ጥያቄ እስክ 1991 ትክክል ነበር"፥ከዛ በኋላ ግን መከለስ ነበረበት ይሄንን ጉዳይ ለማሳመን ከሃያ ዓመት በላይ እንደ ፈጀባቸውና ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ስቀር የራሳቸውን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ እንደ መሰረቱ ተናግረዋል።
በአቶ ሌንጮ የሚመራው አዲሱ ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ ጥላ ስር የኦሮሞ ችግር መፍታት ይቻላል ብለው በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚፈልግና መንግስትም ይሁንታ ሰጥቷቸው ሽገር ከደረሱ በኋላ ወያኔ ፈርታ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ አገሪቷን ጥለው እንዲወጡ ማድረጓ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።
እንደ መውጫ የአስመራው ኢሳያስ አፍወርቂ ኢትዮጵያ መበታተን የለባትም የሚል የጸና አቋም እንዳለው ከአንደበቱ በተደጋጋሚ ሰምተናል።ወያኔ ስነሳ የመገንጠልን ዓለማ ይዞ እንደተነሳ እና የሻብዕያ መሪው እንደከለከሏቸው ከዚህ በፊትም ሰምቻለው አቶ ሌንጮም ይህንኑ አረጋግጠውልናል፡፡ ኢሳያስ የሚፈልገው ሁለት አገር ብቻ ነው ኢትዩጵያና ኤርትራን ብቻ ብለዋል።
ይህንን ሃሳብ በነባራዊ ሁኔታ ጋር ስናስተያየው አንድ ሃቅ እናገኛለን።ወያኔና ሻብዕያ በአውዳሚ ጦርነት ከተለያዩ በኋላ መጀመሪያ አስመራ ላይ ቢሮውን የከፈተው ኦነግ ነበር፡፡ይሄው ብብቱ ስር ከቶ ወይ አይለቅ ወይ አያዋጋ ያሻቸዋል።ቀጥሎ አርበኞች ግንባር የሚባል ቡድን ነው።እሱንም ከስሙ በስተቀር የቀረ ነገር አልነበረም።በነገራችን ላይ ስለ አርበኞች ግንባር ሚስጢር ማን ጫካ የሚባል ሰው በተከታታይ ኢትዩ ሚዲያ የተባለ ዌብ ሳይት ላይ በተከታታይ ይጽፍ ነበር።
እናም አሁን ደግሞ ግንቦት ሰባት ስሙን ከነባሩ ጋር አጣምሮ እንደ ጄት ተውረውሮ ነበር አስመራ የገባው ግን ወፍ የለም።
ለምን ኢሳያስ አይውድማ! ግን ወያኔን ያስፈራራበታል በእነዚህ ድርጅቶች፡፡ውስጠ ሚስጢሩን እንግዲህ ሴይጣን ብቻ ነው የሚያውቀው።
አበቃው!Q
No comments:
Post a Comment