የእዉቅና መረጃ . .
የብሐራዊ መረጃዉ ዳይሬክተር ጌታቸዉ አሰፋ በጥቂቱ...
የብሐራዊ መረጃዉ ዳይሬክተር ጌታቸዉ አሰፋ በጥቂቱ...
ወያኔ ሀገራችንን እንደወረረ በመጀመሪያ የተቆጣጠረዉ ባዶ ስድስትን ነበር ባዶ ስድስት የእስር ቤት መገለጫ ሲሆን በእነርሱ አጠራር የኮድ ስም መሆኑ ነበር ወያኔያዊያን የማረሚያ ቤቶችን በቁጥጥራቸዉ ስር እንዳደረጉ ቀድሞ ሲያገለግሉ የነበሩት የማረሚያ ቤቶች አባላት በሙሉ በመሰወራቸዉ ምክንያት እስረኞችን በአግባቡ መያዝ ተሳናቸዉ። ስለዚህም የማረሚያ ቤቶች ሰራቶኞችን በአዋጅ መጥራቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ።
ሰራተኞቹ በአዋጅ ተጠርተዉ እንደመጡ የማረሚያ ቤቱን ሰነዶችና መረጃዎችን እንዲሁም በሰራተኖች ዙሪያ ላይ ግምገማ ለማካሄድ በማስፈለጉ ምክንያት ህወሃት አሉኝ ከሚላቸዉ ግለሰቦች መካከል ከማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የምርመራ ቡድን ሐላፊ የሆነዉን በሻለቃነት ማእረግ የሚያገለግል ግለሰብ ወደ ማረሚያ ቤቶች ላከዉ! ሰዉየዉ በማረሚያ ቤቶች ዉስጥ ለአንድ ወራት ያህል ሰነዶች ሲያገላብጥ ቆይቶ አጠቃላይ አባላትን በመሰብሰብ ግምገማዉን ጀመረ።
ሰራተኞቹ በአዋጅ ተጠርተዉ እንደመጡ የማረሚያ ቤቱን ሰነዶችና መረጃዎችን እንዲሁም በሰራተኖች ዙሪያ ላይ ግምገማ ለማካሄድ በማስፈለጉ ምክንያት ህወሃት አሉኝ ከሚላቸዉ ግለሰቦች መካከል ከማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የምርመራ ቡድን ሐላፊ የሆነዉን በሻለቃነት ማእረግ የሚያገለግል ግለሰብ ወደ ማረሚያ ቤቶች ላከዉ! ሰዉየዉ በማረሚያ ቤቶች ዉስጥ ለአንድ ወራት ያህል ሰነዶች ሲያገላብጥ ቆይቶ አጠቃላይ አባላትን በመሰብሰብ ግምገማዉን ጀመረ።
በግምገማዉ ላይ ሂሳብ ያላወራረዱ ሁሉ ስማቸዉ እየተጠራ ተብጠለጠሉ ሻለቃዉ አልጋ እና ብርድ ልብስ እንኳ ሳያስረኩ የተሰወሩ የማረሚያ ቤቱ ጥበቃዎችን በያሉበት አስፈልጎ እንዲከፍሉ በማድረግ ለህወሃት ታማኝነቱን አሳየ! አዎ የአድዋ ተወላጁ አጭርና ወፈር ያለ አካል ያለዉ ጠይሙ ባለ ሰፊ ፊት ሻለቃ የዛሬዉ የብሔራዊ ደህንነት የበላይ ጠባቂ ጌታቸዉ አሰፋ።
ጌታቸዉ አሰፋን ከኢትዮጵያ ዉጭ በመላክ የስለላና የመረጃ ትምህርቶችን ተምሮ እንዲመጣ በማድረግ በኩል የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስቴር ለገሰ ዜናዊ ፣ የማረሚያ በቶች አስተዳደር ሐሰን ሽፋና የብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር ሟቹ ክንፈ ሚና የተጫወቱ ሲሆን ዛሬ በመላዉ ሐገራችን ላይ በግፍ የሰለጠነ በደም የተጨማልቁ እጆቹ የሚይዙት የሚጨብጡት ማጣታቸዉን ምንጮች ይናገራሉ።
ሻለቃ ጌታቸው የተለያዩ አይነት የአይን መነጽሮችን በመጠቀም እራሱን ለመቀያየር ይሞክራል፣ አንዳንዴ እረዘም ያሉ ካፖርቶችን በመልበስ እራሱን እረጂም ሰዉ ለማስመሰል ይሞክራል፣ በፊቱ ገጽ ላይ የበቀሉ ጾሞቹን በተለያየ አይነት ሁኔታ ቢቆረጥም ሰፊዉን የጌታቸዉ አሰፋን መልክ ለመለውጥ ግን አይችሉም፣ አሁን አሁን በሚያነብበት ወቅት የንባብ መነጽር መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ ያለልምዱ ባርኔጣዎችንም መቀያየር ስራዉ አድርጎታል፣ የጌታቸዉ የጥበቃ ሰራተኞች እርሱን የሚጠብቁት አይመስሉም ብዙዉን ግዜ ወደ ቢሮ በምን ሰአት እንደሚገባና እንደሚወጣም ለማወቅ አስቸጋሪ ነዉ እኔ ግን በተደጋጋሚ አያዋለዉ በዚያ ቦታ ላይ እረዘም ላለ አመታት በመስራቴ ማንም ሰዉ አይጠረጥረኝም ነገር ግን በእርግጥኝነት ለመናገር ጌታቸዉ ማንንም የሚያምን አይነት ግለሰብ አይደለም በመስሪያ ቤት ዉስጥ አይቆርስም አይቀምስም፣ አንዳንድ የመስሪያ በት ሰራተኞች እርሱ ጌታቸዉ መሆኑን አያዉቁም ጌታቸዉ ባለበት አካባቢ ፎቶ ማንሳትም ሆነ ለመነሳት መሞከር አይቻልም ኑሮዉ ሁሉ በጭንቅ የተወጠረ ይመስላል ኋላዉንም ሆነ ፊቱን አያምንም ብዙን ግዜ አንዲት ቀጭን በመካከለኛ ቁመት ደረጃ ያለች ከእጆቿ ባይንደር የማይነጠል ቀይ ዳማ ሴት አትለየዉም የተለያየ አይነት መኪናዎች እየመጡ ይወስዱታል አብዛኛዉን ግዜ የግል ወይም የቤት መኪና ታርጋ ያለቸዉ ተሽከርካሪዎችን ያዘወትራል ።
will be continued
No comments:
Post a Comment