ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የኦሮሞን ህዝብ የነፃነት ትግል(The oromo movement as a Nomadic,Destructive, and Purposeless) በማለት በመጤነት ፥በዓላማቢስነት፥ በወራሪነት፥ በአውዳሚነት፥ በጎርፍነት ይመድቡና "አማሮች በጎጃምና በደንብያ ሁነው ትግሮችም በግምባራቸው ጠንክረው ባያግዱት እንደፈሳሽ ውኃ እስከ ምስር( ግብፅ) ይፈስባት ነበር።
ይህን ታላቅ ጎርፍ አማሮች ከሀበሻ እንዳያልፍ አቆሙ።" ይላሉ።( መስፍን ወልደ ማርያም 1972፡ 16/17)እዚህ ላይ ኦሮሞዎች ሀበሻ ያለመሆናቸውን ፕሮፌሰር መስፍን የተቀበሉ ይመስላሉ ምክንያቱም ጎርፉ ከሀበሻ እንዳያልፍ ከተባለ ጎርፉ ሀበሻ አይደለም ማለት ነው።
በሌላም በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ብሄሮች ከመጡበት ግንድ ሲመድቡ
"1 ሰመቲክ( ሀበሻ)፡- አማራ፥ ትግሬ ፥ጉራጌ፥ ሀረሪ
2 ኩሽ፡- ገዴኦ፥ ኦሮሞ ፥አገው፥ ሶማሌ ፥አፋር ፥ሲዳማ፥ ቤጃ ፥ሳሆ ፥ኩናማና ሌሎችም
3 ናይሎቲኮች በሱዳን ወሰን የሚኖሩ" ይላሉ (መስፍን ወልደማርያም 1972፡17-18)
No comments:
Post a Comment