Friday, November 21, 2014

ጀግናችን ምን አስባ ይሆን?

የተወለደችው በአዲስ አበባ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በእቴጌ መነን (ያሁኑ የካቲት 12) 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ለጥቃም የከፍተኛ ተቋም ትምህርቷን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ሙያን በመማር የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያዘች። ከዚያም በተመረቀችበት ሙያ በዳኝነት ያገለገለች ሲሆን በ1997ቱ ምርጫ ወቅት ቀስተዳመና ፓርቲን በመቀላቀል ወደ ቅንጅት ከተዋሃደ በኋላ ምርጫውን ማሸነፍ በመቻላቸው ምርጫው እንዳለቀ የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆና ተሾማለች።
                                                 birtukan 1
ነገር ግን በወቅቱ በነበረው የምርጫ ድምፅ መጭበርበርና ከወያኔ ጋር በተፈጠረው ውዝግብ አምባገነኑ ወያኔ ጀግናዋ እህታችንን ጨምሮ ሁሉንም አመራሮች አስሮ ነበር። ከ18 ወራት እስራትና ስቃይ በኋላ የወያኔ ምስ በሆነው ይቅርታ በሉኝ ፈሊጥ ይቅርታ ጠይቀዋል በማለት ሊለቀቁ ቻሉ።
ቅንጅትም ከተበታተነ በኋላ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን በመመስረት በሊቀመንበርነት  አገልግላለች። ሆኖም ወያኔ በድጋሚ ይችው ጀግናችንን ይቅርታ የጠየቀችውን ባደባባይ አልጠየኩም ብላለች በማለት ታህሳስ 28/2008 እ.ኤ.አ የእድሜ ልክ እስራት ፈረደባት። በእስር ቤትም እንግልትና ስቃይም ደረሰባት። ወያኔም ምሴን ካላገኘሁ አለቅም አስመስሎበት ይቅርታ (ምሳችንን ሰጥታን ቢሉ ይሻል ነበር) ጠይቃን ለቀቅናት በማለት ጥቅምት 6/2010 እ.ኤ.አ ከእስር በድጋሚ ተፈታች።
ሁሉን ነገር ለርሷ ልተውና ከተፈታች በኋላ ወደ ፖለቲካው ምህዳር ተመልሳ ማቅናት አልፈለገችም። በ2011 እ.ኤ.አReagan-Fascell Democracy Fellowship የ 5 ወር የትምህርት እድል ሰጥቷት በዋሽንግተን ዲሲ “study the principles of democracy” አጥንታለች። በመቀጠልም በዛው በዩናይትድ ስቴትስ በ2013 በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ስኮላርሺፕ ስላገኘች በታፈነ ማህበረሰብ ውስጥ የዳኝነት ነጻነት ምን እንደሚመስል /independence of the judiciary in closed societies/  የሁለት ዓመት ጥናት በመከታተል ሁለተኛ ዲግሪዋን አገኘች፡፡
                                                        birtukan
እንደው ለማስታወስ ያህል ሞነጫጨርኩ እንጂ ድፍን ኢትዮጵያዊ በታላቅ ጀግንነቷ የሚያውቃት፣ በጨካኙና በአምባገነኑ የወያኔ ስርአት ስር ያደረውን የፍትህ ሜዳ የታገለችና አቋሟን ያሳየች (የስዬ አብርሃ የዋስ መብት ተጠብቆ እንዲለቀቅ ማድረጓ)፣ በተቃዋሚነት የአመራሩን ስፍራ የደፈረች ታላቅ  ሴት፣ ሴትነቷ ሳይበግራት በጭራቁ የወያኔ መንግስት እስራት፣ ግፍና ስቃይን የተጎነጨች፣ ወዘተ። ታዲያ ይህች ታላቅና ቆራጥ ሴት በቀላሉ ከፖለቲካው ምህዳር ትርቃለች ብዬ አላስብም። ሆኖም ግን ይህ እሷና እርሷ ብቻ የሚያውቁት ነገር ነው። ምንም እንኳን ወያኔ የፖለቲካ መጫወቻ ሜዳውን ከጊዜ ወደ ጊዜ አጥብቦ አጥብቦ ሊደፍነው ቢቃረብም ጀግና የጀመረውን ሳይጨርስ ወይም ሳይሰዋ ከሜዳው ለቆ አይወጣምና በቅርቡ እናይሻለን ብዬ አስባለሁ።
ስላንቺ ወሬ ቢጠፋ እንደው ምን ላይ ትሆን ብዬ ነው። አለሁ እንደምትይን ተስፋ አለኝ።
ዴሞክራሲንና ፍትህን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማጎናፀፍ ከሚታገሉት ጀግኖች አንዷ ነሽና ሁሌም እንኮራብሻለን።
“ሰው ያለ ነጻነቱ ምንድን ነው ?” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ።
መልካም ጊዜ ይሁንልሽ
 አሜጋ ነኝ ከኖርዌይ

No comments:

Post a Comment