የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝትን የሚቃወም ሰልፍ ተጠራ:- በሚቀጥለው ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካ ፕሬዘዳንትን ጉዞን በመቃወም የፊታችን አርብ በዚህ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው “ሁዋይት ሀውስ ‘’ የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን አዘጋጆቹ ገለጹ ። በዋሺንግተን ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የወጣቶች ግብረ ሀይል የተዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ፕሬዘዳንት ኦባማ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበትና እንዲሰርዙት የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል። ፕሬዘዳንቱ በቀጣዩ ወር በኢትዮጽያ የሚያደርጉት ጉብኝት ይፋ መደረግን ተከትሎ የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተቃውሞ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል።
Tuesday, June 30, 2015
ሃይ ባይ ያጣው የአለም ህዝቦች ስጋት!
አለም ዝም ያለው, ታላላቅ ሀያላን ሀገራት ሁሉ ፀጥ ብለው ተመልካች የሁኑበት አረመኔያዊው እውነተኛው ትርኢት በጭራሽ አላባራም. እንዲያውም ብሶበታል. ሶሪያ ደበነች, ኢራቅን ፈጁት, ሊቢያ ን አናወዟት, ግብፆችን አረዱ, ኢትዮጵያዊንኑ ወንድሞቻችን ደገሙ. ኮሪያ, አሜሪካ, ኤርትራ ብቻ ያልነካኩት የለም ግን ዝም ተብለዋል. ሀይ ባይ አልተገኘም.
አንድ ቡድን አለምን ሲያስጨነቅ አለም መሪዎች ያጣች ይመስላል. ነገሩ ግራ የገባ ነው. ልምምዳቸው በሜዳ ነው.ይባስ ብለው ለዚሁ ሽብር ተግባር የሚጠቅሙ ህፃናት እያሳደጉ ነው. አልተሸሸጉም. ሆኖም ዝም ተብሏል.
የወያኔ ሰላይ ስደተኞችን መግደሉ ተሰማ
ከሀገር ውጭም በስደት በሕውሓት ሰላዮች ክትትል ይደረግባቸው የነበሩ ኢትዮጵያውያኖች ከሰዳን ወደሊቢያ ገዞ ላይ እንዳሉ የሕውሓት ሰው ከሱዳን አቻው ጋር በመሆን በሱዳን ወታደራዊ ተሽከርካሪ ስደተኞቹ የተሳፈሩበትን ተሽከርካሪ በመግጨት አና እንዲገለበጥ በማድረግ አዳጋ ከደረሰባቸው መካከል የሥርዓቱ ሰው የነበረን ቁስለኛ ከሌሎች ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ፎቶ ከኪሱ በማውጣት ከፎቶው ካስተያየ በኋ በያዘው ሽጉጥ እንደረሸነው የአይን ምስክር ከሞት በተረፉት ሊጋለጥ ችሏል በወቅቱ በሕውሓቱ ሰው በሰሃራ ምድረ በዳ ያለቁት የሁሉም ሰዎች ሥም ያታወቃል ነገር ግር ለሟች ቤተ ሰሰባቸው ሲባል ስማቸውን ለጊዜው በሚዲያ ለማውጣት አልተፈለገም በፎቶ ግራፉ ላይ የምናየውን አሰቃቂ ድርጊት የፈፀመው ኢትዮጵያን የሚገዛው የትግራይ ነፃ አውጭ ሕውሓት ነው ።
— ኢትዮጵያውያን የገጠማቸው ፈተና በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆ በመላው ዓለም ተበትነን በምንገኘው ላይ የዕለት ተዕለት የግል ኑሮአችን ጣልቃ የሚገቡ በሥርዓቱ ቅጥረኞ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ በተገኘው አጋጣሚ ጥቃት እየተደረገብን ይገኛል በግል ሕይወትም ጭምር ።
— ኢትዮጵያውያን የገጠማቸው ፈተና በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆ በመላው ዓለም ተበትነን በምንገኘው ላይ የዕለት ተዕለት የግል ኑሮአችን ጣልቃ የሚገቡ በሥርዓቱ ቅጥረኞ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ በተገኘው አጋጣሚ ጥቃት እየተደረገብን ይገኛል በግል ሕይወትም ጭምር ።
ዳዊት አስራደ በገጠመው ተደጋጋሚ እስርና እንግልት ምክንያት ሀገሩን ትቶ ተሰደደ!!
ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ የሚወዳቸውን ቤተሰቡንና ልጁን ትቶ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል፡፡ ዳዊት ከ13ቱ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚእንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የአንድነትን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድም ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የነደፈ ሙሉ ማንነቱን ለሀገር ትግል የሰጠ ቁርጥ ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም በአማራ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ በመኪና ተገጭቶ ለ6 ወራት ተኝቶ ከሞት ድኗል፡፡
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጡ
የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18/2007 ዓም በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግ/ወያኔን መንግስትን ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘገበ
አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ የምክር እና ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መብትም አላገኙም ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በተደጋጋሚ ለቀረበው ጥያቄ ኢትዮጵያ መልስ መንፈጓ ከፍተኛ ዋጋ በሚሰጠው የእንግሊዝና የኢትዮጵያ ግንኙነት ላይ ጥላ አደጋ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

5 የመኢአድ አባሎች አንዳርጋቸው ፅጌን ይመስክርልን አሉ
በነ ዘመነ ካሴ መዝገብ የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባሎች ናቸው አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብላቸው ነው የጠየቁት የተከሰሱት የግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስልጠና ተሰጥቷችሁ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ላለፉት ሁለት አመታት በእስር የሚገኙት
እነዚህ ተከሳሾች አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ሰው አናውቅም አንዳርጋቸው አሱ አውቃቸዋለሁ አሰልጥኛቸዋለሁ የሚል ከሆነም በናንተ ቁጥጥር ስር ስላለ ችሎቱ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ይዘዝልን እና ይመስክርልን ወይም ይመስክርብን ሲሉ ለፍርድ ቤት አመልክተዋል አቶ አንዳርጋቸው ቀርቦ ምስክርነት ይሰጥ ይሆን ? አቃቤ ህግ በህይወት ይኑር አይኑር የማይታወቅ ሠው ይቅረብልን ማለት አግባብነት የለውም ብሏል ለማንኛው ቀጠሮው ሀምሌ 03/2007 ዓም ስንተኛ ችሎት እንደሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ ፍርድ ቤቱ ግን ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው

እነ ቴዎድሮስ አስፋው ጥፋተኛ ተባሉ
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት ወሬ አውርታችኋል ተብለው የተከሰሱት እነ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሰኔ 22/2007 ዓ.ም አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ጥፋተኛ ከተባሉት መካከል አንደኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ አስፋው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሆን ያሬድ ደመቀ እና አንዋር ከድር የፓርቲው አባል አይደሉም፡፡ እነ ቴዎድሮስ ጥፋተኛ የተባሉት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 486/ለ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ቴዎድሮስ ‹‹የተመሰረተብኝ ክስ የሀሰት ነው፡፡ የተሰማው ምስክርም የሀሰት ነው›› ሲል ውሳኔው ፖለቲካዊ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደዕረቡ መዘዋወሩ ተሰማ በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ እና ውጪ በርካታ የጸጥታ ሃይሎች ነበሩ
ዛሬ በጥዋት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የተቀጠረውን ውሳኔ ተመልክቼ ለመዘገብ ልደታ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርቼ ነበር፡፡ 3፡30 ሰዓት ገደባ በታችኛው መግቢያ በር ጋር ስደርስ፣ ቁጥራቸው በዛ ያሉ፣ የሚሊተሪ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሃይሎች እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች በፍርድ ቤቴ ቅጥር ግቢ በር ላይ ሆነው ሰዎችን በጥብቅ እየተፈሹ ሲያስገቡ አስተዋልኩ፡፡ በአጋጣሚ ከጠበቃ ተማም አባቡልጉ ጋር ተደዋውለን ተገናኝተን ነበር፡፡
እነ ወይንሸት ሞላ ይግባኝ ተጠየቀባቸው
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ሰኔ 16/2007 ዓ.ም ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ዛሬ ሰኔ 22/2007 ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ቀደም ሲል ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል›› በሚል በተከሰሱበትና ከእስር በተለቀቁበት ክስ ላይ ይግባኝ ተጠየቀባቸው፡፡
አቃቤ ህግ እነ ወይንሸት የዋስትና መብታቸውን ተነጥቀው ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ የጠየቀ ቢሆንም ዳኛዋ ‹‹በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ ከእስር የተፈቱ በመሆናቸው ዋስትና ሊከለከሉ አይገባም፡፡›› ብለዋል፡፡ ዳኛዋ እነ ወይንሸት እንደተለቀቁ እንጅ በእስር ላይ መሆናቸውን እንደማያውቁ ገልጸው 3 ወር ተፈርዶበት ቂሊንጦ የሚገኘው ማስተዋል ፈቃዱ ባለመቅረቡ፣ ከእሱ ጋር ረቡዕ ሰኔ 24/2007 ዓ.ም ቀርበው ክርክር እንዲጀምሩ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡ ሰኞ ሰኔ 29/2007 ዓ.ም ውሳኔ እንደሚሰጡም አሳውቀዋል፡፡
የቱርክ መንግስት የግብረሰዶማውያኑን ሰልፍ በውሃ ተኩስ በተነ
በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል የተሰባሰቡ ግብረሰዶማውያን ሊያደርጉት አቅደው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ የአገሪቱ መንግስት ህገወጥ ነው ሲል በውሃ መርጫ ካኖን መበተኑ ተሰምቷል።
ከሰሞኑ በዓለም ላይ እየተከበረ ያለውን የግብረሰዶማውያን ቀን ለማክበር ወጥተው የነበሩት እነዚህ ሰልፈኞች በታቅሲም አደባባይ አቅራቢያ በመሰባሰብ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች እንዲበተኑ መደረጉን በስፍራው የነበረ የሮይተርስ ዘጋቢ ተናግሯል።
ፓሊሶች የሰልፉ መሪዎችን ካሰሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ መመለሷን የዘገበው ይኸው የሮይተርስ ዘጋቢ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖሊሶችን ጣልቃገብነት የሚቆጣጠር አዲስ ረቂቅ አዋጅ እንዲወጣ በመመካከር ላይ እንደሆኑም ጨምሮ ተናግሯል።
ሰበር ዜና፦ ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ለሀሙሱ ESFNA ኮንሰርት ይደርሳሉ!
32ኛው በሰሜን አሜሪካ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው የኢትዮጲያዊያን የሰፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ ከተዘጋጁት ዝግጅቶች መሀከል በጉጉት የሚጠበቁት የሃሙስ እና የዓርብ የሙዚቃ ዝግጅቶች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት እንደሚደረጉ ተረጋገጠ።
ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ተስፋዬ ቪዛቸውን ለማግኘት የአሜሪካ ኤምባሲ የሲስተም መበላሸት ያዘገየው ቢሆንም አሁን ከደቂቃዎች በፊት ኤንባሲው ችግሩን እንዳስተካከለ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።
U.S. Embassy Addis Ababa
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ባለፉት ሳምንታት የተፈጠረው የሲስተም ችግር መፈታቱን በደስታ እየገለጠ፡ ቪዛችሁ የተፈቀደላችሁ አመልካቾች ፓስፖርቶቻችሁን መረከብ እንደምትችሉ እናስታውቃለን፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ011-558-2424 ይደውሉ፡፡

ፖሊስና አቃቤ ህግ በኢህአዴግ ላይ ሰልፍ መውጣታቸውን ቀጥለዋል!
አይ ኤስን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ በኋላ ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ ኢህአዴግ ላይ ሰልፍ በመጥራት ስድብ እያዘነቡበት ነው፡፡ በሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ላይ በቦታው ያልነበሩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የቀድሞው መኢአድ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችን ያስሩና እነዚህ ወጣቶች ያላሉትን ክስ ብለው ያቀርባሉ፡፡ ይህ ክስ ደግሞ ለእነሱ የሰልፍ መፈክር መሆኑ ነው፡፡ የስድብ ውርጅብኝ፡፡ በቃ ችሎት የቁጭት መውጫቸው ሆኗል ማለት ይቻላል!
ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ (ሰልፍ እንበለው) ከሚያሰሟቸው መፈክሮች መካከል፡-
• ኢህአዴግ ሌባ ነው!
• ጠንካራ እንጅ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም
• ቴዎድሮስ ለህዝብ ሞተ፣ መለስ ደንግጦ ሞተ፣ ሀይለማሪያም በቁሙ ሞተ!
• እያዋረደን ያለው ወያኔ ነው!
• ወያኔ አሳረደን!
• ኢህአዴግ ቡሽቲ መንግስት ነው! (አሁን ይህም ክስ ላይ ይቀርባል! ዳንኤል ብርሃኔን መሰሉኝኮ)
• የወያኔ 24 አመት አገዛዝ ይበቃናል!
• የሀገር አበሳ የውጭ ሬሳ
• ኢህአዴግ….
• ኢህአዴግ….እና የመሳሰሉት ስድቦች (ማለቴ መፈክሮች) ይገኙበታል!

“መንግስታዊ ቅሌት !”
“መንግስታዊ ቅሌት !”
ህውሓት/ኢህአዴግ በአገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች በአደባባይ ወጥተው መንግስትን የመቃወም እና የመተቸት አለም አቀፍ እንዲሁም ህገ-መንግስታዊ መብት ጨፍልቆ፣የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ማሰር፣መግደል እና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ ዋና ዋና የመንግስት ስራ ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯአል፡፡
ህውሓት/ኢህአዴግ በአገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች በአደባባይ ወጥተው መንግስትን የመቃወም እና የመተቸት አለም አቀፍ እንዲሁም ህገ-መንግስታዊ መብት ጨፍልቆ፣የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ማሰር፣መግደል እና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ ዋና ዋና የመንግስት ስራ ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯአል፡፡
በኢትዮጵያ የሚኖሩ “ኤርትራዊያን” የአገራቸውን መንግስት እንዲቃወሙ የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ በመፍቀድ ፣ ሃሳብ ማመንጨት እና ማስተባበር እንዲሁም ቦታን መፍቀደ የህውሓት/ኢህአዴግ ጭንቀት ከሆነ ቆየ !
ቆራጡ የዲሞክራሲ ታጋይ ዳዊት አስራደ ከሀገር ተሰደደ!!
እየጎመዘዘኝ የሰማሁት ዜና ነው!!
ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ የሚወዳቸውን ቤተሰቡንና ልጁን ትቶ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል፡፡ ዳዊት ከ13ቱ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የአንድነትን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድም ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የነደፈ ሙሉ ማንነቱን ለሀገር ትግል የሰጠ ቁርጥ ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም በአማራ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ በመኪና ተገጭቶ ለ6 ወራት ተኝቶ ከሞት ድኗል፡፡
በ97 ዓ.ም በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን የጀመረው ዳዊት አስራደ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች አባልም ነበር፡፡ ዳዊት በፓርቲው የተለያዩ ሓላፊነቶች ላይ የሰራ ሲሆን ለአብነትም
- በወጣቶች የትምህርትና ስልጠና ዘረፍ
- የብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ አባል
- የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ዋና ጸሀፊ
- የኢኪኖሚ ጉዳዮች ሃላፊና በተለያዩ የአድሆክ ኮሚቴዎች ውስጥ በሀላፊነትና በአባልነት ሰርቷል፡፡
Wednesday, June 17, 2015
ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣ ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ (ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ)
አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር
ANDENET NORTH AMERICA ASSOCIATION OF SUPPORT ORGANIZATION
8121 Georgia Avenue, Silver Spring, MD 20910 ste 10, Tell: (301) 585-7700
ሰኔ ፲, 2007 ዓ/ም (June 12, 2015)
የደርግ ስርዓት ሲገረሰስ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የዲሞክራሲ ስርዓት እንደሚገነባ ቃል ገብቶ ነበር። ሆኖም፣ ይኸው ሃያ አራት አመታት አለፈ፤ ኢትዮጵያዉያን የግፍ ቀንበር በላያቸው ላይ ተጭኖ፣ መብታቸዉንና ነጻነታቸውን ተገፈው፣ በአገራቸው በፍርሃትና በሰቀቀን እየኖሩ ነው። ምንም እንኳን እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ የስርአቱ ተጠቃሚዎች ቢከብሩም፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የኑሮ ዉድነት፣ ዜጎችን ከቅያቸው የማፈናቀል ተግባራት፣ አድልዎና ዘረኝነት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢትዮጵያን ለብዙዎች ሲኦል እያደረጋት ነው።
የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle) (በሥዩም ወርቅነህ)
ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን
ቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ ከሃገራችን ባህልና ወግ በእጅጉ የሚፃረርና የወደፊት ተተኪውን ትውልድን ወደ አልባሌ ድርጊት የሚገፋፋ ነውረኛ ተግባር ነው።
Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን
የህብር ሬዲዮ ሰኔ 7 ቀን 2007 ፕሮግራም
<…በቀጥታ አይከል ከተማ ከላይ አርማጭሆ የመጡ ሶስት ወጣቶች ሻይ ቤት ተቀምጠው እያለ ታጣቂዎቹና ፖሊሶች በአንድነት መጥተው ወጣቶቹ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ሰው ግልብጥ ብሎ አትነኳቸውም ልጆቻችንን አለ በዚህ ጊዜ ወደ ሕዝቡ ተኮሰው አምስት ገለው ስድስት ቆስለዋል..እንዴት ሰላማዊ ሰው ላይ በመሳሪያ ጭፍጨፋ ይደረጋል?..> በሰሜን ጎንደር የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…ሁበር ኤክስ ለቬጋስ አያዋጣም የሚያዋጣው ብላኩ ነው እሱ እንዲፈቀድ መታገል ጥሩ ነው ካልሆነ የቲፕ ነገር የግድ በስብሰባ መነሳት አለበት…>
አሌክስ አበራ ከሳን ፍራሲስኮ ስለ ሁበር የግል ልምዱን መሰረት አድርጎ ከሰጠው ማብራሪያ (ውይይቱን ያዳምጡት)
ከኒዮርኩን እስር ቤት ያመለጡት መጨረሻ ያለመታወቅ የፈጠረው ጭንቀት እና ያልተሳካው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች አሰሳ( ልዩ ዘገባ)
በውጭ የሚኖረው ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ በጭብጨባ ተገቢውን ትኩረት አግኝቷል? (ምልከታ)
ሌሎችም
እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ” ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል
እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ” ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው ኤርትራ የሚገኘውንና በተወካዮች ም/ቤት በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ በጸጥታ ኃይሎች ማይካድራ ላይ በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አስገቡ፡፡
ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ማለትም፣ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ በጋራ ያዘጋጁትን የክስ መቃወሚያ አስገብተዋል፡፡
የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ» ትላንት ምሸት በድብቅ ጅዳ ገቡ
ሰኔ 8 ቀን 2007 ምሸት ሳውዲ አረቢያ የገቡት የኢትዮጵያው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስተር ጉብኘት ያለተጠበቀና እንግዳ መሆኑን የሚናገሩ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ምንጮች በዲፕሎማቱ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፤ ሚንስትሩ ከሳውዲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ቢሄዱም የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ጉብኝት ኦፊሴላዊ ይሁን በድብቅ እስካሁን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ጅዳና ሪያድ ያሉት የመንግስት ዲፕሎማቶች ምንም አይነት ነገር እንደማያውቁ ከቆንስላው ጽ/ቤትና ከሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ
የትህዴን ድምጽ እንደዘገበው ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርጫፍ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ ተብሎው በኢህአዴግ ባለስልጣናት መነገራቸው ተገለጸ። ለዜና ምንጩ በደረሰው መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣን በሆነው በአዲሱ ለገሰ በተደረገው የስብሰባ መሪነት አብዛኛው የአቢሲያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ፤ ከመንግስት ጋር ያላችሁን ችግር በውይይት እንፋታው ብሎ በከፈተው ስብሰባ ላይ የባንኩ ሰራተኞች እኛን የቀጠረን ባንክ የግል ተቋም ነው።
አቶ አላሙዲንን እንደ በጎ አድራጊ፣ ቸር እና ደግ ሰው የምትቆጥሩ ሰዎች በጣም አስቂኝ ናችሁ
ዓበጋዝ ዤዓንግት አላሙዲ ሞራል እና ስነምግባር የጎደለው ሰው ነው፣ አላሙዲ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ትዳር አፍርሷል፣ አላሙዲ ወርቅን ያክል የኢትዮጵያ ሀብት በብቸኝነት ያለ ማንም ከልካይ እየዘረፈ ያለ ሰው ነው። ብዙዎች አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያንቀሳቅሰው ንግድ ትርፍ እንደሌለው እና ይልቁንም በተለያየ ጊዜ ለግለሰቦች በሚያደርገው የገንዘብ ዳረጎት ብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚከስር ግለሰብ አድርገው ማየታቸው አንድም ካለማወቅ ነው በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ሰውየው በተደራጀ መልኩ በጎ ነገሮች በሚያወሩ እና በሚያስወሩ ሰወች ተሸውደው ነው ብለን እናስባለን። ቢሆንም ግን አላሙዲ ህወሀት/ወያኔወች በራሱ ምንም ሊያደርጉት የማይችል ግለሰብ ነው፤ ምክንያቱም እሱ የአይነኬወቹ ሰይጣን አምላኪ ኢሉምናቲወች አባል ነው (ይህን አላምንም የሚል ሞባይል እና ለፕቶፕ ላይ አፍጥጦ ፎቶ ላይክ ከማድረግ ይመርምር)፤ እስከዛሬ ህወሀት/ወያኔወች በእሱ ምክንያት አይናቸው እየቀላ ምንም ሊያዳርጉት ያልቻሉት ሰው ነው፤ ስለዚህ ምርጫቸው እና የሚያዋጣቸው አብረው ተሞዳሙደው መዝረፍ ነው። በአጠቃላይ አቶ አላሙዲ (ሼኽ የማልለው ሙስሊም ስላልሆነ ነው) መታየት ካለበት እንደ በጎ አድራጊ ሳይሆን እንደ ሞራል እና ምግባር የሌለው ዘራፊ ሰው ነው፤ ሊመሰገን አይገባውም።
Samuel is not just some unknown Ethiopian
I am shocked to hear of the death of our leader Samuel Awoke, a brilliant young man, visionary leader and human dignity defender. His young precious life was cut too soon last night by soulless and immoral thugs of the TPLF/EPRDF.
Our brother Samuel is not just some unknown Ethiopian; he is one of us. He is the son, brother, uncle, best friend, valued colleague and extraordinary leader of all of us. Ethiopia has lost an amazing leader and freedom fighter.
የስደቱን መከራ ወደ ምፍትሔ መፈለጊያ እድልነት መቀየር ይቻላል? የመነሻ ሀሳቦች (ፈቃደ ሸዋቀና)
ማስታወሻ ፥ (የዚህን ጽሁፍ መሰረታዊ ይዘት በቅርቡ በተካሔደው ኢሳት ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ አቅርቤው ነበር። የኢትዮጵያን ሁኔታዎች አዘውትሮ እንደሚከታተል ኢትዮጵያዊ በሀገራችን የሰፈነው ዘግናኝ ድህነት የፈጠረውን አሳዛኝና አዋራጅ ስደትና ወደፊትም መፍትሔ ካልተበጀ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ገምቼ የባሰ ድህነት ውስጥም ሳንዘፈቅ ችግሩን ምን ብናደርግ ነው መቋቋም የሚቻለው በሚለው ጥያቄ ላይ ሳሰላስል የመጣልኝ ሀሳብ ነው። የሰጠሁት የመፍትሄ ሃሳብ በጉባዔው ላይ ትንሽ አቧራ አስነስቶ ነበር። አንዳንዶችም የየዋህ ሀሳብ አድርገው ወስደውታል። እኔ ችግር ማውራትና ማማረር የሰለቸኝ ሰው ነኝ። ብሶት በባዶ ከማውራት ብዬ የመሰለኝንና ብዙ ዋጋ ሳያስከፍል የችግራችን መፍትሄ ይሆናል ያልኩትን ሀሳብ ነው አቅርቤ ውይይት መቀስቀስ የሞከርኩት። የሌሎችን ሀሳብ ማየትና መከራከር እፈልጋለሁ። ሀሳቤን በተሻለ ሀሳብ ለመለወጥ ዝግጁ ነኝ። የማነሳው ሀሳብ ስራ ላይ የሚውል አለመምሰሉ ይገባኛል።
አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ… ክንፉ አሰፋ
የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ።
“ሃሎ?”
“ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?”
“ነኝ፣ ምን ፈለግክ?”
“ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።”
“ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?”
“99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!”
“0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?”
“አዎን ጌታዬ። ሌላ ምን እንታዘዝ?”
“99.8% ህዝብ የስም ዝርዝሩን አንብብልኝ።” አሉ አቦይ ስብሃት እየተባለ ይወራል።

አንድ ወዳጄ ስለ አቦይ ስብሃት የነገረኝ ታወሰኝ። ሰውዬው ከግመል እንኳን የማይሻል እንስሳ ብጤ ነው። ግመል ሳትጠጣ ለቀናት ትሰራለች አቦይ ስብሃት ደግሞ ሳይሰራ ቀኑን ሙሉ ይጠጣል። አብዛኞቹ የህወሃት አባላት እድሜያቸው እንደ አስተሳሰባቸው ስላረጀ ጨዋታቸው ከውሃ ጋር ነው። ከውድ ውሃ ጋር! ድንጋይን ውሀ ያስጮኸዋል!
ሜዳው የኢህአዴግ፣ ዳኛው ኢህአዴግ፣ ታዛቢው ኢህአዴግ፣ ድምጽ ቆጣሪው ኢህአዴግ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀው “ምርጫ” እነሆ ተጠናቀቀ።
ሜዳው የኢህአዴግ፣ ዳኛው ኢህአዴግ፣ ታዛቢው ኢህአዴግ፣ ድምጽ ቆጣሪው ኢህአዴግ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀው “ምርጫ” እነሆ ተጠናቀቀ።
የስደቱን መከራ ወደ ምፍትሔ መፈለጊያ እድልነት መቀየር ይቻላል? የመነሻ ሀሳቦች (ፈቃደ ሸዋቀና)
ማስታወሻ ፥ (የዚህን ጽሁፍ መሰረታዊ ይዘት በቅርቡ በተካሔደው ኢሳት ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ አቅርቤው ነበር። የኢትዮጵያን ሁኔታዎች አዘውትሮ እንደሚከታተል ኢትዮጵያዊ በሀገራችን የሰፈነው ዘግናኝ ድህነት የፈጠረውን አሳዛኝና አዋራጅ ስደትና ወደፊትም መፍትሔ ካልተበጀ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ገምቼ የባሰ ድህነት ውስጥም ሳንዘፈቅ ችግሩን ምን ብናደርግ ነው መቋቋም የሚቻለው በሚለው ጥያቄ ላይ ሳሰላስል የመጣልኝ ሀሳብ ነው። የሰጠሁት የመፍትሄ ሃሳብ በጉባዔው ላይ ትንሽ አቧራ አስነስቶ ነበር። አንዳንዶችም የየዋህ ሀሳብ አድርገው ወስደውታል። እኔ ችግር ማውራትና ማማረር የሰለቸኝ ሰው ነኝ። ብሶት በባዶ ከማውራት ብዬ የመሰለኝንና ብዙ ዋጋ ሳያስከፍል የችግራችን መፍትሄ ይሆናል ያልኩትን ሀሳብ ነው አቅርቤ ውይይት መቀስቀስ የሞከርኩት። የሌሎችን ሀሳብ ማየትና መከራከር እፈልጋለሁ። ሀሳቤን በተሻለ ሀሳብ ለመለወጥ ዝግጁ ነኝ። የማነሳው ሀሳብ ስራ ላይ የሚውል አለመምሰሉ ይገባኛል።
Andy Tsege: Fears grow over state of mind of British activist who languishes in Ethiopian jail
Exclusive: 60-year-old reportedly said he sees no reason to stay alive
Exclusive: 60-year-old reportedly said he sees no reason to stay alive
Fears are growing for the state of mind of a British father of three who has languished in a secret jail in Ethiopia for almost a year.
Andargachew “Andy” Tsege, who has been sentenced to death, reportedly told the British ambassador during a rare visit: “Seriously, I am happy to go – it would be preferable and more humane.”
Next week marks the first anniversary of Mr Tsege, a leading opponent of the Ethiopian regime, being imprisoned during a trip to Africa.
Sunday, June 14, 2015
ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣ ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ (ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ)
አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር ANDENET NORTH AMERICA ASSOCIATION OF SUPPORT ORGANIZATION 8121 Georgia Avenue, Silver Spring, MD 20910 ste 10, Tell: (301) 585-7700 ሰኔ ፲, 2007 ዓ/ም (June 12, 2015) የደርግ ስርዓት ሲገረሰስ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የዲሞክራሲ ስርዓት እንደሚገነባ ቃል ገብቶ ነበር። ሆኖም፣ ይኸው ሃያ አራት አመታት አለፈ፤ ኢትዮጵያዉያን የግፍ ቀንበር በላያቸው ላይ ተጭኖ፣ መብታቸዉንና ነጻነታቸውን ተገፈው፣ በአገራቸው በፍርሃትና በሰቀቀን እየኖሩ ነው። ምንም እንኳን እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ የስርአቱ ተጠቃሚዎች ቢከብሩም፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የኑሮ ዉድነት፣ ዜጎችን ከቅያቸው የማፈናቀል ተግባራት፣ አድልዎና ዘረኝነት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢትዮጵያን ለብዙዎች ሲኦል እያደረጋት ነው።
የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ጭልጋ ላይ ገበያ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ገደሉ * በርካቶች ቆስለዋል
ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ዛሬ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ። ከስፍራው የሚወጡት ዜናዎች እንደሚያረጋግጡት በአይከል ከተማ መሀል ገበያ ህዝብ ላይ ተኩስ የከፈቱት የህወሀት ወታደሮች በርካታ ሰዎችንም ማቁሰላቸው ተገልጿል። ከሶስቱ ሟቾች የሁለቱ ስም የታወቀ ሲሆን የአስር አለቃ ውቤ እና አቶ ብርሌ በህወሀት ወታደሮች ዛሬ ተገድለዋል። የአይከል ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ሙስሊምም መገደላቸው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አስታውቀዋልል:: እንደ ዘገባው ከሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እየተነገረ ነው።
Sunday, June 7, 2015
አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ለስልጣኑ መጠበቂያ ያቋቋመው መከላከያ ሠራዊት እየፈረሰ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ነው፡፡
የህዝብ ጠላት የሆነው ህወሓት ከህዝብ አብራክ የተከፈለውን መከላከያ ሠራዊት በፀረ-ህዝብነት ሙሉ ለሙሉ የማሰለፉ ዓላማው ሲከሽፍ በዓይኖቹ በብረቱ በመመልከት ላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰሞኑን በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው በመኮብለል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡ ህዝብን ለማጥፋት የቆመውን ህወሓትን ከድተው ለህዝብ ከቆመው አርበኞች ግንቦትት 7 ጎን ከተሰለፉት ከእነዚህ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የአግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አባላት ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡
በቴፒ አቅራቢያ ከፍተኛ ውጊያ ተካሄደ- ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል
ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና ደቡብ ክልል አዋሳኝ ከተማ በሆነቸው ቴፔ ትናንት ሌሊት 11 ሰአት ላይ ለተሻለ ፍትህና ነጻናት እንታገላለን የሚሉ ታጣቂዎች በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ በወሰዱት እርምጃ 3 የሌሊት ተረኛ ፖሊሶች ሲገደሉ በርካታ እስረኞችንም አስፈትተዋል።ቁጥራቸው ከ100 እስከ 150 የሚሆኑ በቴፒና አካባቢው የሚታየውን ዘረኝነትና የአስተዳደር በደል እንዋጋለን በማለት ራሳቸውን አደራጅተው ጫካ የገቡ ወጣቶች ባለፉት 9 ወራት ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ቢቆዩም ትናንት ሌሊት የፈጸሙት ጥቃት ከእስካሁኑ የተለየ ነው ተብሎአል።
የፖሊስ ጣቢያው በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን በአካባቢውም የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰፍረው በአካባቢው ተደጋጋሚ ቅኝት ያደርጋሉ። ታጣቂዎቹ ከአንድ ቀን በፊት ለፖሊስ አባላት ጥቃት እንደሚፈጽሙ ማስጠንቀቂያ የላኩ ሲሆን፣ በቃላቸው መሰረት ሌሊት ላይ ፖሊስ ጣቢያውን ሰብረው በመግባት በጣቢያው ውስጥ ተከማችተው የሚገኙትን የጦር መሳሪያዎች እስከ እነ ጥይቶቻቸው እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶችን ሰብስበው ወስደዋል። በሶስት ክፍል ታስረው የነበሩ እስረኞችን ሲለቁ፣ የራሳቸውን አባላት ይዘው ጠፍተዋል።ተረኛ ፖሊሶች ተኩስ የከፈቱ ቢሆንም ታጣዊዎች በወሰዱት እርምጃ አንድ መቶ አለቃ ማእረግ ያለው ፖሊስና ሁለት ተራ ፖሊሶች ተገድለዋል።
‹‹አማራ በመሆኔ ዘሬን እንዳልተካ ተደርጌያለሁ›› 1ኛ ተከሳሽ ጌታቸው መኮንን (መቶ አለቃ)
[በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር]
ከወራት በፊት በሽብር ተጠርጥረው ከአማራ ክልል ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ የዞን አመራሮች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ በ13/07/07 በተጻፈና ዛሬ ግንቦት 28/007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በንባብ በተሰማው የአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው በአንደኛ ተከሳሽ ጌታቸው መኮንን መዝገብ 16 ሰዎች የሽብር ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ከተከሳሾቹ መካከል የመኢአድ፣ የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት የተካተቱበት ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በ2001
ውዝግብን ያስተናገደው የዛሬው የጦማሪያኑ እና የጋዜጠኞቹ የፍርድ ቤት ዝርዝር ዘገባ (ኤልያስ ገብሩ)
በትናንቱ የቪኦኤ ዘገባ ላይ አቃቤ ሕግ ቅሬታ አቀረበ
ጦማሪ አቤል ዋበላ ችሎት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ
‹‹ሥነ-ሥርዓት ያዝ!›› ዳኞች
‹‹እናንተ ራሳችሁ ሥነ-ሥርዓት ያዙ! ይህ ችሎት ነው፡፡ ግልጽ ነው›› አቤል ዋበላ
‹‹ውሳኔው ለሁሉም ከሆነ፣ ለአቃቤ ህጉም ሆነ ለአለቃው ጠ/ሚኒስቴርም መሆን አለበት፡፡››
‹‹ጓደኛዬ (አቤል) የሚቀጣ ከሆነ ውሳኔው እኔም ላይ ይታዘዝ››
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

ትናንት ምሽት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ (VoA)ን ሳዳምጥ ነበር፡፡ ከዘገባዎቹ መካከል ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ላይ ስለሚገኙት ስድስቱ የዞን 9 ጦማሪያንና ሶስት ጋዜጠኞች በትናንትናው ዕለት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የነበራቸውን የፍርድ ቤት ውሎ ይገኝበታል፡፡
86 ኤርትራውያን በISIS መታገታቸው ተነገረ
86 ኤርትራውያን ስደተኞች በአይሲስ ታጣቂዎች ተጠልፈው ከትሪፖሊ ውጭ መወሰዳቸው ተሰማ።
እስካሁን ግን አይሲስ ሀላፊነት መውሰዱን አልገለፀም።
አንድ በእንጊሊዝ የሚታተም ጋዜጣ እንደጠቀሰው በምህራብ ሊቢያ ነው 86 ኤርትራውያን በISIS የተጠለፉት
Militants from Islamic State of Iraq and the Levant (Isil) are believed to have kidnapped 86 Eritrean refugees from a smugglers’ caravan in westernLibya.
የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።
ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?
ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ ብቻ እንደሚሄዱ እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከአምስቱ አንዱ እንደሆኑ ይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)
አዲስ አበባ ብቻ ዛሬ ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ መግብያ ያጡ ”ጎዳና ቤቴ” ብለው አንቅልፍ በጣላቸው ቦታ ክልውስ ብለው የሚተኙ ሕፃናት ይኖሩባታል።ይህ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ግዴለሽነት የመነጨ እንጂ ከድህነታችን ብቻ የሚመስለው ካለ ለመሳሳቱ እማኝ ላቅርብ። ሕፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው።ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ሕፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን?

ህወሀት ወያኔ ለአማራው ህዝብ ያለው ጥላቻ ከየት መነጨ? ታሪካዊ ዳሰሳ
ህወሀት ወያኔ በግልጽ በሚያወጣቸው ጽሁፎች አንዳንድ ግዜ ‘የገዢ መደብ’ የሚል ተውላጠ-ስም ቢታከልበትም ባካሄዳቸው እንቅስቃሴዎች አማራን እንደ ህዝብ የሚያጥላሉ መጣጥፎች፣ መዝሙሮች፣ ሽለላዎችና ድራማዎችን ይጠቀም እንደነበረ ቀደምት አባላቶቹ ሳይሸሽጉ የሚናገሩት ሃቅ ነው። ነገሩን በጥልቀት ለተመለከተ፤ ድርጅቱ ይህንን ተግባር የሚፈጽመው በስህተት ወይንም አባላቱ በሚፈጽሙት የዲሲፕሊን ግድፈት ሳይሆን፣ እንዳውም የአማራውን ህዝብ በስትራቴጂክ እና ታሪካዊ ጠላትነት ፈርጆ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ስለመሆኑ ብዙ ብዙ ማስረጃዎችን ለማቅረብ መድከም አያሻም። ድርጅቱ ትግሉን ገና ‘ሀ’ ብሎ ሲጀምር “አማራና ኢምፔሪያሊስምን”በትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላትነት ፈርጆ እንደሆነ በወቅቱ የነበሩ ሁሉ የሚያስታውሱት ነው።
ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)