Wednesday, June 17, 2015

ወንድሜን ሳሙኤል አወቀ ገደሉት


የሰማያዊ ፓርቲ አባል በደብረማርቆስ እጩ ተወዳዳሪ ነበረው ወንድሜን ሳሙኤል አወቀ በዚህ መልኩ ነበር ከወራት በፊት የደበደብት ይሄው ዛሬ ህይወቱ ማለፉን ሰምቻለሁ በጣም አዝንኩ እጅግ በጣም ግፍቸው ጽዋው ሞልቶ ፈሰሰ ያለከልካይ፡፡
ይህ ወጣት የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነው በደብረማርቆስ እጩ ተወዳዳሪ ሆኖ እንደሚወዳደርና ለምርጫ ቅስቀሳ በወጣበት ሲመለስ ቤቱ አከባቢ ሲደርስ በርካታ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ደብድበውታል ጉዳት አድርሰውበታል፡፡

እስቲ ስለልጁ የምታውቁት ነገር ካለ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ የተዘገበው ይሄን ወንድማችንን ያካትታል፡፡‹‹‹‹ደህንነቶችና የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የሚያደርጉት ጫና ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ትናንት ሚያዝያ 21/ 2007 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ የሆነው አቶ ሳሙኤል አወቀ እንዲሁም ሚያዚያ 20/2007 ዓ.ም የደ/ጎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢና የፎገራ ወረዳ የተወካዮች ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ አቶ አለማየሁ አደመ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል›››፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ
ወንድሜ ፈጣሪ ጉዳትህን ይጠግን
ለግፈኞችም ፍርድ ይስጥ
ከ 2 ሳምንት በፊት (ግንቦት 26 2007 ዓም ወይም በፈረንጆቹ June 03 2015) ነበር ሳሙኤል አወቀ ገዳዮቹ ሊገድሉት እንዳሰቡ እና ከሞተም እነማን እንደሚገድሉት ሕዝብ እንዲያውቅ ከዚሁ ፌስ ቡክ ላይ የፃፈው ይሄው ዛሬ ሞቱን ሰማን:: እንዲህ ነበር የፃፈው
“በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!!!" በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል!!!!! ተገደልሁም ታሠርሁም ፤ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ !!!!" አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው::”
ማን እንደገደለው አናውቅም ለምትሉን የሽፍታው መንግስት ጠበቆች አሁንስ ማን እንደገደለው አወቃችሁ ?
ነብስህን በገነት ያኑር !

No comments:

Post a Comment