በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል የተሰባሰቡ ግብረሰዶማውያን ሊያደርጉት አቅደው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ የአገሪቱ መንግስት ህገወጥ ነው ሲል በውሃ መርጫ ካኖን መበተኑ ተሰምቷል።
ከሰሞኑ በዓለም ላይ እየተከበረ ያለውን የግብረሰዶማውያን ቀን ለማክበር ወጥተው የነበሩት እነዚህ ሰልፈኞች በታቅሲም አደባባይ አቅራቢያ በመሰባሰብ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች እንዲበተኑ መደረጉን በስፍራው የነበረ የሮይተርስ ዘጋቢ ተናግሯል።
ፓሊሶች የሰልፉ መሪዎችን ካሰሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ መመለሷን የዘገበው ይኸው የሮይተርስ ዘጋቢ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖሊሶችን ጣልቃገብነት የሚቆጣጠር አዲስ ረቂቅ አዋጅ እንዲወጣ በመመካከር ላይ እንደሆኑም ጨምሮ ተናግሯል።
የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት (AFP) እንደዘገበው ደግሞ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የወሰዱት እርምጃ በተለያዩ የግብረሰዶም መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ዘንድ “ፋሽስት” የሚል ቅፅል አሰጥቶቷቸዋል።
ግብረሰዶማውያኑ ከዚህ በፊት ለ13 ዓመታት ያለምንም የመንግስት ጣልቃገብነት ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጉ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ኤርዶጋን በዚህ ዓመት የመጀመሪያውን እቀባ ማድረጋቸው ነው የተነገረው።
(ዜናው የአል-አረቢያ ቴቪ ነው)
No comments:
Post a Comment