Monday, February 4, 2013

WE NEED PRESS FREEDOM IN ETHIOPIA


Release all JORNALIST AND POLITICAL PRISONERS  including Andualem Aragie, Eskinder Nega, Bekele Gerba, Reeyot Alemu, all Muslim Leaders, et al!
LONG LIVE ETHIOPIA!!!
            FROM SEBIAWI

በኅትመት ነፃነት ላይ የወያኔ አፈና ቀጥሏል


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በድጋሚ ተቀጠረ
በዓዲ ኀትመትና ማስታወቂያ ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስም እየታተመ የሚወጣው “አዲስ ታይምስ” መጽሔት፤ ከብሮድካስት ባለሥልጣን የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እድሳት በመከልከሉ ከኅትመት ውጪ ሆነ፡፡ አሳታሚው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጸው፤ የአገሪቱ የፕሬስ ሕግ በሚያዘው መሠረት የመጽሔቱን ዓመታዊ ፈቃድ ለማሳደስ ከድርጅቱ የሚጠበቁትን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ቢያሟላም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ጥር 2 ቀን 2005 በላከው ደብዳቤ ለመጽሔቱ የሞያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እድሳት እንደማያደርግ አስታውቋል፡፡

Sunday, February 3, 2013

መቆሚያ የሌለው የግብፅ ምስቅልቅል

የግብፅ ህዝብ አምጦ የወለደው የተሂሪር አደባባይ ህዝባዊ አብዮት ውሉ የለየለት አይመስልም። በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች አብዮቱ ጨንግፏል ሲሉ ቀላል የማይባሉት ደግሞ አብዮቱ በሙርሲና በዙሪያቸው ባሉ አክራሪ የእስልምና አማኞች ተነጥቋል ብለው ያምናሉ።
ግብፃውያን ዓመታት በላይ የተጫነባቸውን የሙባረክን አገዛዝ ከጣሉ በኋላ እፎይታን አላገኙም። በህዝቡ ምርጫ አብዛኛውን የፓርላማ መቀመጫ የያዘው የእስልምና ወንድማማቾች ፓርቲ ግብፅን ወደ አክራሪ የእስልምና አገዛዝ ይመልሳታል የሚል ስጋት በመኖሩ በፕሬዝዳንት ሙርሲ ላይ እምነት የሌላቸው በርካታ ግብፃውያን ተቃውሞ ሲያሰሙ ቆይተዋል።
በወናነት በሙርሲ መንግስት ላይ ተቃውሞ የሚያነሱ አክራሪ ያልሆኑ የእስልምና እምነት ተከታይ ግብፃውያንና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አማኝ ግብፃውያን ናቸው። ይሁንእንጂ ሙርሲ የእሳቸውን ስልጣን ከፍርድ ቤቶችና ከህግ በላይ የሚያጎነፅፈውን ፣ ለሴቶች እምብዛም የእኩልነት መብት የማያሰጠውንና በአመዛኙ ወደሸሪያ ህግ የሚያዘነብለው ሕገ-መንግስት ላይ ህዝበ ውሳኔ አሰጥተው ውሳኔው ላይ የተሳተፉ ጥቂት ግብፃውያን ህገ-መንግስቱን መደገፋቸው አይዘነጋም።
ይሁንና የሙርሲ ተቃዋሚዎች ከመጀመሪያው ህዝበ -ውሳኔውን ከመቃወማቸውም ባለፈ በህዝብ ውሳኔውም ላይ ወጥተው ድምፅ የሰቱ ጥቂት ግብፃውያን ናቸው በሚል በድጋሚ የህዝቡ ውሳኔውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ሀገሪቱ የሙባረክ አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በአክራሪና ለዘብተኛ እንዲሁም ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አማኞች የመክፈል አዝማሚያ አሳይታለች። በስልጣን ላይ ያለው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ሀገሪቱ በእስልምና አስተምሮሆቶች መመራት አለባት ወደሚል አቋም ያዘነበለ በመሆኑ በእስራኤል፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት በጥርጣሬ አይን እንዲታይ አድርጎታል። ምዕራባውያን የግብፅ የታሂሪሪ አደባባይ አብዮት በእነ- ኢራንና በሌሎች አክራሪ የእስልምና መንግስታት እንዳይጠለፉም ስጋት አላቸው።

እስራኤል ለኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች አስገዳጅ የወሊድ መቆጣጠሪያ መስጠቷን አመነች


ከአምስት ዓመታት በፊት ጥርጣሬ ፈጥሮ የነበረውና የእስራኤል መንግስት በአስገዳጅ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት እንዲወጉ አድርጓቸዋል የሚለው ወሬ እውነት መሆኑን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሆኑት ፕሮፌሰር ሮን ጋምዙ፤ እስራኤል ውስጥ ለሚገኘው የሲቪል መብቶች ተሟጋች ማህበር በፃፉት ደብዳቤ አመኑ።
ኢትዮጵያውያኑ እናቶች “ዴፖ-ፕሮቬራ” የተሰኘውን የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት መወጋታቸውን የሚያትት ወሬ ከዚህ ቀደም ወጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ በእስራኤል ባለስልጣናት እውቅና ባለመስጠታቸው ምክንያት ባለፉት አምስት አመታት ተሸፋፍኖ ቆይቷል ይላል ዘገባው። የጤናጥበቃ ሚኒስትሩ አክለውም ባስተላለፉት ትዕዛዝ በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ላይ የተፈፀመው አስገድዶ መድሃኒት የመስጠት ጉዳይ በአፋጣኝ እንዲቆም ብለዋል።

የፖለቲካ “ ለውጥ” ቢገኝማ ሽረት ነበር !! ግን ፖለቲካችን “ከርሞ ጥጃ”፣ “ታጥቦ ጭቃ”


አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቃላችሁ? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ፍፁም ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ አዲስ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግኝት የሚፈጥርልን ብናገኝ (ቻይናን ምን ይሳናታል?) በገንዘብ ባንችል እንኳን በ”ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ” ስም እንማጠናቸው ነበር… (ቻይና ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ስታውቅ አይደል?)
ወዳጆቼ፤ የጥምቀት በዓል እንዴት አለፈ እባካችሁ? በሸጋ ያለፈ ይመስለኛል (እኔ ከናንተ ባላውቅም) ከሁሉም ያስደመመኝ ግን ምን መሰላችሁ? በጥምቀት ይወረወር የነበረው ሎሚ ተረት ሆኖ (እንደ ድህነት? ማለት ነው) ዘንድሮ በፕሪም ተተክቷል የሚባል ነገር ሰምቻለሁ፡፡ “ወጭ ለምኔ” ያሉ የዘመኑ ወጣቶች ደግሞ (በሬ ለምኔ እንደሚባለው) የሞባይል ነምበራቸውን ቆነጃጅቱ ደረት ላይ ሲወረውሩ እንደዋሉም የአውዳመት የወሬ ምንጮቼ ሹክ ብለውኛል፡፡ በደቡብ አፍሪካው የባለፈው ሰኞ የብሄራዊ ቡድናችን ግጥምያ እለት የተባለውን ሰምታችሁልኛል? “ውበት ሲለካ የኢትዮጵያ ሴቶች ናቸው ለካ!” የሚለውን ማለቴ ነው፡፡ (ለነገሩ ሲያንሳቸው እኮ ነው!!) ነገርዬውን ዝም ብዬ ሳስበው ግን የኢትዮጵያን እንስቶች ውበት ድንገት ያጐሉት ያለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ከሆነችው ዛምቢያ ጋር ገጥመው (ያውም በጐደሎ ተጫዋቾች) ድንቅ የኳስ ጥበብ ያሳዩት የብሄራዊ ቡድናችን አባላት ይመስሉኛል - (ያዳኑን እነ አዳነን ማለቴ ነው!) የሴቶቻችን ውበትማ አዲስ ክስተት አይደለማ!! እኔ የምለው ግን… በኢቴቪ ቀርቦ አስተያየቱን የሰጠ አንድ ሰው

የመለስ ራዕይ በ‹‹አዲስ ታይምስ›› መፅሄት ተተገበረ!!!


ምንም ጥርጥር የለውም መለስ ዜናዊ ፍፁም አምባገነን ነበር፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ከአንድ ክፍለ ጦር በላይ የተለየ ሀሳብን እና ነፃ ሚዲያን ይፈራል፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ወራሾቹም ሀሳቡን በነፃነት የሚገልፅን ከመለስ በባሰ መልኩ ይፈራሉ፡፡ ይህ ፍራቻቸው ወደ ጭፍን አምባገነንነት ስለቀየራቸው መላ ሀገሪቷን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየገፏት ነው፡፡ 
የሆነ ሆኖ መለስ ከአደባባይ ከራቀ በኋላ በፍትህ ቤተሰቦች የሚመራ ትልቅ ሚዲያ ሲዘጋ ‹‹አዲስ ታይምስ›› ሁለተኛዋ ናት፡፡ 
ለ‹‹አዲስ ታይምስ›› መዘጋት መንግስት የሰጠው ሶስት ምክንያት፡-
1. የባለቤትነት ድርሻ ከአንዱ ወደ ሌላው ሲዞር በ15 ቀን ውስጥ አላሳወቃችሁም፣
2. ህትመቱ ሲወጣ ለቤተ-መዛግብት ሁለት ሁለት ኮፒ በነፃ አልሰጣችሁም እና
3. የገንዘብ ምንጫችሁ አይታወቅም የሚሉ ናቸው፡፡
በቃ፡፡ ህዝብን መናቅ ሙያ ብሎ የያዘው ገዥው ፓርቲ መፅሄታችንን ለመዝጋት የሰጠው ምክንያት እነዚህ ናቸው፡፡ አስገራሚው ጉዳይ የባለቤትነት ድርሻ ሲዞር በጊዜው ማስታወቃችን፣ ለቤተ-መዛግብትም ህትመታችን ሲወጣ ሁለት ሁለት ሳይሆን አምስት አምስት ኮፒ በነፃ የሰጠንበትን ማስረጃ ማቅረባችን እና ምንጩ አይታወቅም ለሚለው ደግሞ የመፅሄቱ ኮፒ 35 ሺህ በመሆኑ ምንጩ ህዝባችን (አንባቢያን) መሆናቸውን ብሮድ ካስት አብጠርጥሮ ማወቁ ነው፡፡
ይሁንና እነዚህ የተጠቀሱት ምክንያቶችስ ተፈፅመው ቢሆን እንኳ አዋጁ የሚለው አስራ አምስት ሺህ ብር ያስቀጣል ነው፡፡ ታዲያ መዝጋትን ከየት ያመጡት ህግ ነው? ማንአለብኝነት እና ጉልበተኝነት ካልሆነ በቀር፡፡
በነገራችን ላይ ‹‹ብሮድ ካስት›› በሚል ስያሜ የተመሰረተ ተቋም ከቴሌቪዥንና ራዲዮን ውጭ ያልተፈቀደለትን የ‹‹ህትመት ሚዲያ››ንም ጨምሮ መቆጣጠሩ ከበረከት ስምዖን ውጪ ለማንም ግልፅ አይደለም፡፡ ለቤተ-መፅሀፍት መፅሄት ማስገባትን እና አለማስገባትንም እንዲሁ ከሙያ ብቃት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በረከት ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡
… አሁን የመለስ ራዕይ ግልፅ ነው፤ አፈናውን አጠናክሮ ማስቀጠል፡፡ 

እውን ይህቺ አገር የማን ናት ?



በአገራችን ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው በተራቸው ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የሚገደዱ ሃይሎችን በየቀኑ እየፈለፈለ መሆኑ በተግባር እየታየ ነው።
ወያኔ የድጋፍ መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ውስጥ የወጣው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ወይም ዴሚት በሚል ምህጻረ ቃል ከሚጠራውና በርካታ የትግራይ ወጣቶችን ማሰባሰብ ከቻለ ድርጅት ጀምሮ “በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የብሄር እኩልነት ካባ አከናንቤያችኃለሁ” ብሎ ወያኔ ከሚመጻደቅባቸው ህዝቦች አብራክ የወጡ የኦሮሞ፣ የኦጋዴን፣የቤነሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአፋርና የደቡብ ህዝቦች የዚህን ዘረኛ ሥርዓት እብሪትና ጥጋብ አስተንፍሰው የተዋረደውን ክብራቸውን ለማስመለስ  መሳሪያ አንስተው መፋለም ከጀመሩ ውለው አድረዋል።