Sunday, June 2, 2013

“አንለያይም አንለያይም… መቼም አንለያይም አንለያይም!”ሰላማዊ ሰልፉን በርካቶች እየተቀላቀሉት ጉዞው ቀጥሏል፡፡


መንግስታችን ይህንን ሰልፍ ዕውቅና የሰጠው ሰማያዊዎቹ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ እንደዛቱት ያደርጉትና አልተኩስ ነገር እንግዳ አለ አላስር ነገር ስንቱን አስሬ ብሎ ሰግቶ መሆኑ ይጠረጠራል፡፡
የሆነ ሆኖ ዛሬ በመንግስት ዕውቅና ያገኘ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡ ከቀበና አራትኪሎ ከአራት ኪሎ ደግሞ ፒያሳ የተሰላፊው ቁጥር እየጨመረ ወደ ኩባ አደባባይ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡
አንድ ወዳጄ እንዳወጋኝ መንግስት እስከዛሬ ድረስ በሚያደርጋቸው ሰልፎች ላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ወደ ሰልፉ ያሰማራቸው ነበር፡፡ እንዳይቀሩም የስም ጥሪ እና ቁጥጥር ይደረጋል የቀረ ተማሪም ማርክ ይቀነስበታል፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በተለምዶሜካፕ ክላስእንደሚባለው በሰንበቱ ለትምህርት ጠርተዋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንዳቀሩም ሃምሳ ማርክ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል፡፡
አንድ ጊዜ መንግስት የሆነ ሰልፍ ጠርቶ እኔም ስታድም ተገንቼ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይ አንዲት ሴትዮን እናቴ የዚህ ሰልፍ አላማ ምንድነው ስላቸውእንጃ ልጄ አበሏ ትጠቅመኛለች ብዬ ነው ወጣሁት ስምጠሪው አንዴ ቢየኝ ወደቤቴ እመለስ ነበር ብለውኛል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ አበልም የለም ማርክም የለም፡፡ ሰዉ ግን አሁንም እየጎረፈ ነው፡፡
በዚህ ሰልፍ ላይ ጎልቶ ከወጣው ዜማ መካከል ሙስሊሙ ህብረተሰብ እና ሌላው በአንድ ድምፅአንለያይም አንለያይምመቼም አንለያይም አንለያይም!” እያሉ ያዜሙበት ይገኛል፡፡


Saturday, June 1, 2013

ትግሉ ጥራት እንዲኖረው አቅጣጫንና ግብን አለማወቅ ልዩነትን፡ መከፋፈልን ፡ አለመተማመንንይፈጥራል:: እርስዎስ የትነው ያሉት ?


እንደ አንድ ዜጋ በሃገራችን ጉዳይ ላይ በሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች ላይ ነገሮችን በችላ ባይነት ለማለፍ ብዙ ጊዜ አልሞክርም ያም በመሆኑ ያቅሜን ያህል የማበረክተው ድርሻ ካለ ቀዳዳዋን ለመጠቀም እሞክራለሁ። በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ጉዳይ ላይ በርካታምሁራንበየቀኑ የመያወጡአቸውን የተለያዩ ጽሁፎች አነብና በየቀኑ የሃገሬ ልጆች በየፓልቶኮቹ የሚያደርጉትን ውይይት ክርክር ስድብ እሰማና ማታ ጋደም ብዬ ሳብሰለስለው አንዱም ነገር ውስጤ ሳይቀር ሲሰማኝ በመብሰልሰል ብቻ እኖራለሁ።
ዛሬ በሃገራችን ያለውን ችግር የምንገዘብበት የግንዛበቤ መነጽራችን እጅግ የተለያየ ከመሆኑም በላይ ለመፍትሄውም ዝብርቅርነት ዋነኛውን አስተዋጽኦ አድርጎኦል ብዬ ስለምገምት እነሆ ወገኞቼ በተለይም በሃገራችን ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ቀጥዬ በማቀርበው መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በሚኖረን አቅዋም ልዩነቶቻችን ሊጠቡ ወይም ሊሰፉ ልንግባባ ወይም ላንግባባ በጋራ ለሃገር እንድንቆም ወይም ያለመፍትሄ ስንረጋገም እድሜያችንን እንድንፈጅ እንገደዳለን ብዬ አምናለሁ።
በወያኔ/ ኢህአዴግ ላይ በሚኖር አመለካከት ላይ ያለ ልዩነት/ተቃዋሚዎች
የአመለካከት አንድ ስብስቦች
ወያኔ/ኢሃዴግ ፋሸስታዊ መንግስት ነው
ወያኔ/ኢሃዴግ ኢትዮጰያን በኮሎኒ የያዘ መንግስት ነው
ወያኔ አፓርታይድ መንግስት ነው
ወያኔ የሽፍቶች ቡድን እንጂ መንግስት አይደለም
ወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ መንግስት ነው አላማውም ኢትዮጵያን ማፈራረስ ነው።
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የአንድ ዘር የትግሬን በላይነት የሚጠብቅ መንግስት ነው
ወያኔ ሁሉም ነው

Ethiopia holds reporter covering evictions in dam region

New York, May 30, 2012--Ethiopian authorities have detained since Friday a reporter who sought to interview people evicted from their homes in a region where the government is building a contentious hydro-electric dam on the Blue Nile, according to a news report and the reporter's editor. The Committee to Protect Journalists said today that the case highlights authorities' disregard for the rule of law and its systematic efforts to suppress news critical of government officials.

Muluken Tesfaw, a reporter for the private weekly Ethio-Mihdar, is being held in a prison in the town of Asosa, capital of the Benishangul-Gumuz region, Getachew Worku, the paper's editor-in-chief, told CPJ. Muluken has not been formally charged or presented in court, Getachew said. The detention appears to run counter to constitutional guarantees that a person be brought to court within 48 hours of arrest.
"By arresting journalist Muluken Tesfaw for gathering information from the victims of forced relocation, Ethiopia is once again criminalizing independent journalism," said CPJ Africa Advocacy Coordinator Mohamed Keita. "Ethiopia should make good on its obligation as a member of the U.N. Human Rights Council to uphold citizens' rights by releasing Muluken immediately."

ኑሮዬን ለማሻሻል ወደ ጉምሩክ...


ጊዜው በጃንሆይ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ አንድ ሰውዬ ነበረ፡፡ ፈጥኖ ደራሽ (ፖሊስ?) ነው፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ማለት ያው ጦር ሠራዊት ማለት ነው፡፡ ግንኙነታቸው ከጀርመን ጋር ስለሆነ ጠመንጃቸው ማስ MASS ነው፡፡ የጦሩ ግን የአሜሪካ ኤም ዋን M-1- ነው ይባላል፡፡ በተረፈ ባብዛኛው ነገራቸው ፈጥኖ ደራሾች ልክ እንደጦር ሠራዊት ናቸው፡፡ ወጥቶ አደር በጠረፍ አካባቢ መዘዋወርና ወንበዴና ወመኔን መመንጠር ከፊናንስ ፖሊሶች ጋር በመተባበር ኮንትሮባንዲስቶችን ማሳደድና ህገ-ወጥ ንብረቶች መውረስ የአገሪቱን የንግድ አመራር ሥርዓት የማስያዝና የየበረሃውን ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ነው፡፡ ዛሬም በረሃ፣ ነገም በረሃ ሁሌም በረሃ ነው፡፡ ቤተሰቡ አዲስ አበባ ነው፡፡ ደመወዙን በሙሉ ለቤተሰቡ ተቆራጭ ያደርግና ይሄዳል፡፡ እሱ የሚኖረው በበረሃ ቀለቡና ለሥጋ ተብላ በወር የምትሰጠው ሦስት ብር ብቻ ነው፡፡ ለወር የሥጋ መሸመቻ ሦስት ብር መንግሥት ይሰጠዋል፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይበቃ ነበር፡፡ አሳምሮ፡፡ ዛሬ ሌላው ቀርቶ የኛ ሰፈር እንኳ ባቅሙ አንድ ኪሎ ሥጋ 140 ብር ይሸጣል፡፡ እና ፈጥኖ እረፍት የለውም፡፡ ደንቡ የአመት ፈቃድ ያገኛል ቢልም እሱ ግን በተግባር የሚያገኘው ፈቃድ በሁለትና በሦስት ዓመት አንዴ አሥር ቀን ለማትሞላ ጊዜ ያህል ነው፡፡ እሷኑ ከሚስቱ ተቀራርቦ ዘር ይተውና ይሄዳል፡ ልጁ ሲወለድ ክርስትና ሲነሳ፣ ሲገረዝ... ምናምን ሲል አባትየው የመገኘት እድል የለውም፡፡ ፎቶግራፍ ትልክለታለች በቃ ይሄው ነው፡፡ በመጣ ጊዜ ሁሉ ወሬው የበረሃ ብቻ ነው፡፡ አንዴ መጣና ለሚስቱ ስለበረሃ ኑሮው ያወራላታል፡ ምን ሆነ መሰለሽ ይላታል፡፡ ለግዳጅ ስዘዋወር ኢሚ፣ ኢልካሬ፣ ፊቅ፣ ጭናክስን፣ ቶጐጫሌ፣ ፌርፌር፣ ዶሎ... ወዘተ እያለ የበረሃውን ነጥብ ጣቢያ እየጠቃቀሰ ያወራላታል፡ በጥሞና አዳምጣው አውርቶ ሲጨርስ ሚስት ቀጠለች ባለቤቴ ሆይ አለችው፡፡

የኢትዮጵያ ግድብ የጦርነት አዋጅ ነው አል-ጋማ አል-ኢስላሚያ የግብፅ ሚኒስትሮች ካቢኔ ረቡዕ በአስቸኳይ ተሰበሰበ...

 የኢትዮጵያ ግድብ  የጦርነት አዋጅ ነው  አል-ጋማ አል-ኢስላሚያ   የግብፅ ሚኒስትሮች ካቢኔ ረቡዕ በአስቸኳይ ተሰበሰበ...
የኢትዮጵያ የሕዳሴው ግድብ ግንባታና የጥቁር አባይ ወንዝ ውሃን አቅጣጫ የማስቀየር ተግባር ‹‹በግብፅ ላይ ጦርነት እንደማወጅ ነው›› ሲሉ ሼክ እብዱል አክሀር ሙሐመድ ተናገሩ፡፡ የአል-ጋማ አል-ኢስላሚያ አመራር ‹‹አል-አረቢያ›› ከተሰኘው የሳተላይት ቴሌቪዥን ጋር ቃለ- ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ይህን ያሉት ኢትዮጵያ ባለፈው ማክሰኞ ግንቦት 20 ቀን 2005 የግድቡ ስራ አካል የሆነውን የወንዙን ፍሰት አቅጣጫ ማስቀየር ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡ ሼህ ሙሐመድ ድርጊቱ ‹‹የግብፅን የውሃ አቅርቦት የሚቀንስና በብሔራዊ ደህንነቱን የሚያበላሽ ነው›› ብለውታል፡፡ ጨምረውም ‹‹በእኛ ላይ ጦርነት የሚያንዣብብ ከሆነ ለመዋጋት ዝግጁ ነን፡፡ ሁሉንም ጥንካሬያችንን ተጠቅመን ክብራችንን እናስጠብቃለን›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከዚህ በፊት ዲፕሎማሲያዊ ስምምነቶች ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡
አሕራም የተሰኘው የግብፅ ጋዜጣ በኦን ላይን ዕትሙ ከሰሞኑ ባሠፈረው አዲስ መረጃ መሠረት፣ ግብፅ ከአባይ ወንዝ አሁን ከምታገኘው የበለጠ የውሃ ኮታ እንዲኖራት ትፈልጋለች፡፡ ጋዜጣው የአገሪቱን ብሔራዊ የፕላኒንግ ኢኒስቲትዮት ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ በአሁኑ ወቅት ግብፅ ከአባይ ወንዝ በዓመት እያገኘችው ያለው ውሃ 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ቢሆንም (እ.ኤ.አ) በ2050 ግን ተጨማሪ 21 ቢሊዮን ኪዩብክ ሜትር ማግኘት ይኖርባታል፡ ፡ ምክንያቱም በተጠቀሰው ዓመት የግብፅ ሕዝብ ብዛት 150 ሚሊዮን እንደሚደርስ ስለሚገመት 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትሩ ብቻ እንደማይበቃው በጋዜጣው ተመልክቷል፡፡