Tuesday, July 2, 2013

የህወሓት/ ኢሕአዴግ ሰወች ለምን ለጃዋር ጥብቅና ቆሙ ?

ከማሰተዋል

የሰሞኑን የአልጀዚራን ፕሮግራም ተከትሎ ስለፕሮግራሙ እና ስለጃዋር የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ሰንብተዋል:: ከነዚህ አስተያየት ሰጭወች መካከል በአፍቃሪ ህወሓት/ኢሕአዴግ የሚታወቁ ሰወች የሰጧቸአው አስተያየቶች ትንሽ ግራ የሚያጋቡ ናቸው :: እነዚህ ሰወች በመጀመሪያ ራሱን የአልጀዚራን ፕሮግራም የሰላ ትችት ሲሰነዝሩበት የሰነበቱ ሲሆን ከመሀከላቸው በፕሮግራሙ ላይ መንግስትን ወክለው ለመሳተፍ አልጀዚራን ጠይቀው ከአልጀዚራ ፍቃድ ሲከለከሉ ሃሳባቸዉን በኢሜል ለአልጀዚራ እንደላኩ በሁአላም አልጀዚራ መልዕክቴን አዛብቶ አቀረበብኝ እያሉ በማማረር በፌስ ቡክ ገፃቸው ሲያስነበቡን የሰነበቱ ይገኙበታል :: በተጨማሪም የፕሮግራሙን ተሳታፊወች በተለይም ጃዋርን የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ ሲወነጅሉ ከሰነበቱ በሁአላ ሰሞኑን እንደገና ጃዋር ትክክል ነው እያሉ የጃዋር ጠበቃ መስለው ለመታየት ሙከራ እያደረጉ ነው :: እነዚህ ሰወች ለምን እንደዚህ ያደርጋሉ?

Monday, July 1, 2013

***በታሪክ አንቀልባ ታዝሎ መኖር ለማንም አልጠቀመም***

***በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የትምህርት ተቋም የሚመረቅ ወጣት ሀገርህ የት ነው ተብሎ ቢጠየቅኦሮምያ፣ ትግራይ፣ደቡብ፣ ሶማሌ፣አፋር…› ከማለት ውጪኢትዮጵያ ናትየሚል ለማግኘት በጣም የምንቸገርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡***
መብላት መጠጣት፣ መልበስና ማማር ሊቀር የሚችል ተራ ነገር ነው፡፡ ማጣትና ማግኘት ተፈራራቂ በመሆናቸው ዛሬን ያጣ ነገ ያገኛል ተብሎ ይገመታልና ይህም ምንም ማለት አይደለም፡፡ አሁን እያስፈራኝ የሚገኘው ትልቁ መርዶ ግን አንድ ሕዝብ በዜግነት ማንነቱ፣ በባህሉ፣ በሃይማኖቱ፣ በትምህርት አቋሙ፣ በማኅበራዊ ሥነ ልቦናው፣ በአጠቃላይ የግንዛቤና ዓለምን የመረዳት የአስተሳሰብና የአመለካከት አድማሱበነዚህና በመሳሰለው አእምሮኣዊና መንፈሣዊ ኅልውናው ላይ አሁን የተጋረጠበት አደጋ ሊያስከትለው የሚችለው የትውልድ ምክነትና የኅልውና ቀጣይነት ችግር ነው፡፡ ይህ ዓይቱ ችግር ነው ብዙዎቻችንን እንቅልፍ እየነሳን የሚገኘው፡፡ ይህ ዓይነቱ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስ ሞራለቢስና በሀገሩ ላይ ሀገር አልባ የሆነ ትውልድ በብዛት የሚያመርት ሀገራዊ ችግር ነው ጥቂት የማንባል የቀደመው ትውልድ አባላትን የኅሊና ዕረፍት እያሳጣን የሚገኘው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሀገር ያለች እየመሰለች ነገር ግን ሁለመናዋ የጠፋና እንደፀጉራም ውሻ አለች ሲሏት የሞተች ሀገር ውስጥ የመኖር አደጋ ነው እየተንሰራፋ ያለው፡፡ 
ከቁሣዊው ሕይወት አንጻር ዛሬ ቢርበንና ቢጠማን ምንም አይደለም፡፡

" ዘረኝነት "

ዘረያቆብ

" ዘረኝነት "
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ,....logical or racism ?!?! 
ዘረኝነት ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሰዉ ልጆችን የሚያሰቃይ {ቫይረስ} ነዉ
ዘረኝነት በሁለት ይከፈላል
1. በተፈጥሮ ዘረኛ የሆኑ ሰዎች አሉ ሌላዉን የሰዉ ልጅ የሚንቁ የሚያቋሽሹ እንዲሁም የሚያገሉ እራሳቸዉን ልዩ ዘር አርገዉ የሚያዩ {እነዚህን የያዘዉ የዘረኝነት ቫይረስ በቀላሉ የሚፈወስ አይደለም}

2.
ሌላዉ ደግሞ በተለያየ ምክኒያ ዘረኛ ለመሆን የተገደዱ ሰዎች ናቸዉ እነዚህ ለዘረኝነታቸዉ ምክኒያት ነዉ ብለዉ የሚያነሱት ከሌላዉ ዘር በደረሰባቸዉ ግፍ በደለ የዘር አድሎ ጭቆና እና ማጥላላት ዋነኛ ምክኒያት ነዉ