Tuesday, October 1, 2013

Democracy, Tolerance, and G7’s position towards Eritrea

by Kirubeal Bekele
On Sunday September 22, 2013, the Ginbot 7 leadership had a very revealing and open discussion in Washington DC meeting like it has never had before. As you know, the issue of working with Eritrea has been a bone in the throat for G7 as well as for its supporters around the world. Many have argued against using Eritrea as a spring board to wage an armed struggle against TPLF.Ginbot 7 leadership had a very revealing and open discussion in Washington DC
Opponents claim that Eritrea cannot be trusted based on their experience with Isayas Afeworki so far and his public rhetoric as it relates to Ethiopia. They may have a point. But the problem is that they don’t practice the position they defend or argue for. They don’t provide an alternative and actually implement that alternative.

ሸረኛ ጥጃ ቢያርዷትም አትተኛ!!፡ የፖለቲካው ጀዋሪ የሚለው

በለው!~ 
“አማራ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት አይደለም፤ …ይሄ ፖለቲካ ለካ ላይ ላዩን እንጂ ውስጡ ጥሬ ነው”
>>>እጅግ የተለጠጠ፣ ግን የዘቀጠና የወረደ ጥያቄና መልስ! ለነገሩ ግለሰቡን እንደገና ለዝና ለማምጣት የተፈተለች የሥራ አጦች ሸማ ናት በለው! ግን በሀሳብም በባሕርይም ቁጭ መለስ ዜናዊ! ዘይገርም ነገር አለ…አንዳንድ ሰወች ያሳዝኑኛል ዕውቀት ሲቸግራቸው ምሁር ማንቆለባባስ ይጅምራሉ ልክ እነደ ኢህአዴግ ማለት ነው። ” እኔ ጃዋርን በጣም ማከብረው አድናቂው የምከታተለው የምደግፈው የማፈቅረው የሚቀጥለው ጠ/ሚ አድርጌ የምመርጠው ወጣት የፖለቲካ ተንታኝ (በታኝ) የአ እንግዲህ ታንክ ተደግፈው መፅሀፍ ካነበቡት ኢኮኖሚስት ምሁር ፌዘራሊዝም በፌኢዘ ቡክ የምትነፋ ቱልቱላ አንዳንዴም የሚሽነሪስት ሹንባሽ፣ የወተትና ፋፋ ዲቄት በአፍ ሲበን ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

እኔና አፄ ምኒሊክ (አብርሃም ደስታ – ከመቀሌ)

7c196-1001168_485348238212789_1719160956_n
አብርሃም ደስታ
ቆይ ግን እኔ የምኒሊክ ‘አድናቂ’ ነኝ እንዴ? ባጋጣሚ ስለ አፄ ምኒሊክ ጥሩም መጥፎም ፅፌ አላውቅም። ግን ብዙ የህወሓት ደጋፊዎች የምኒሊክ አገዛዝ እንደምደግፍ አድርገው ለህዝብ ይነግራሉ። የፌስቡክ ጓደኛዬ ዳንኤል ብርሃነም “የምኒሊክ ቲፈዞነትህ ለማስቀጠል ከፈለክ የሱ ወራሾች የሆኑ ‘አንድነቶች’ (ፓርቲው መሆኑ ነው) አሉልህ፤ ከነሱ ጋር ተቀላቀል” የሚል መልእክት ያለው አስተያየት ሰጠኝ።
የህወሓት ደጋፊዎች ከምኒሊክ ጋር የሚያገናኙኝ ምናልባት ህወሓት ስለምቃወም ይሆን? ወይስ እንደነሱ ‘ሸዋ አማራ ጠላታችን ነው’ ብዬ አለመፃፌን ነው? ህወሓትን መቃወም ከምኒሊክ አገዛዝ… ጋር ምን ያገናኘዋል? ግን’ኮ ህወሓቶች በስልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙት ስትራተጂ ‘ከፋፍለህ ግዛ’ ነው።

ከሰማይ የወረደው መስቀል ጉዳይ..በሶርያ ሰሞኑን የተሰራው ተአምር... (የቪድዮ ትምህርት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

መስከረም 18/2006 ዓም የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሰማይ ወረደ ተብሎ ስለተነገረው መስቀል መሰረት አድርጎ እንዲህ ዘግቦ ነበር-
''በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ከሰማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል፣ ቅዱስ ሲኖዶስ መርምሮ ውሳኔ  እንደሚያስተላልፍ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳትና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አስታወቁ፤ ሕዝቡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ በትዕግሥት እንዲጠባበቅ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል....''
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሰማይ የወረደው መስቀል ጋር በተያያዘ  ስለታምራት እና በሶርያ የተደረገው ተአምራት ጋር አያይዞ በአዲስ ዓለም ማርያም  ሰሞኑን ያስተማረው ትምህርት ወቅታዊ ግንዛቤ ይሰጣል።ይመልከቱት።

9.5 ሚልዮን የባለ አንድ እና የባለ አምስት ብሮች የአገልግሎት ጊዜያቸው ከመጠናቀቁ በፊት ከገበያ ውጭ ሆኑ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም በአውሮፓውያኑ በ2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው ፣ በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው።
ብሮችን የሚቀብሩ እና አሽገው የሚያስቀምጡ እንዳሉ የገለጹት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባንኩ የህዝብ ግንኝነት ሰራተኛ፣  በየጊዜው የብር ዋጋ የመግዛት አቅም እየተዳከመ በመሄዱ ህብረተሰቡ ተጎጅ እየሆነ መምጣቱን ይገልፃሉ፡፡

ግንቦት7 በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መስመሩን እየዘረጋ መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ

መስከረም ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ይህንን የተናገሩት በኖርዌይ ከተካሄደው ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሁዋላ ነው።
የግንቦት7 ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው  የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ላይ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ የተጣለብን ህዝባዊ አደራ ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል።
በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው የሄዱት ሰዎች በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ አንዳርጋቸው ፣ በመከላከያ ሰራዊት በእግረና፣ በአየር ሃይልና በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሊደርሱበት በማይችሉበት መንገድ መስመር እየዘረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በውጭ አገራት ተመሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለማድረግ እቅድ አላችሁ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ ህዝባዊ ሀይሉ ከተግባር ጋር በተዛመደ መልኩ የገቢ መሰባሰብ ዝግጅት መርሀ ግብሩን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በህዝባዊ ሀይሉ ወይም በግለሰቦች ስም ምንም አይነት የገቢ መሰባሰቢያ ዝግጅት መደረግ እንደሌለበት ገልጸዋል።

መሬት የማን ነው? አንድ (ፕ/መስፍን ወልደ ማርያም)

አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው።የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤ይህ በአጥንትና በደም የታጠረ መሬት የማን ነው? በመሬቱ ላይ የባለቤትነት መብትን ለማስከበር ከውጭ ኃይሎች ጋር የተጋደሉት ጥንታውያን ነፍጠኞች ቅድሚያን የሚያገኙ ይመስለኛል፤ እነዚህ ጥንታውያን ነፍጠኞች ብቻቸውን አልነበሩም፤ ለምግብ የሚሆናቸውን ሁሉ የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፤ ለልብስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚፈትሉና የሚሸምኑ ባለሙያዎች ነበሩ፤