Monday, May 27, 2013

ብአዴን ‹‹ሰለሞናዊ›› ስርወ መንግስት!? – (ሊያነቡት የሚገባ የአደባባይ ምስጢር)

የብርሐኔ አበራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ቤተሰብ አባላት አቶ በረከት እና አዲሱ
የብርሐኔ አበራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ቤተሰብ አባላት አቶ በረከት እና አዲሱ
በአንድ ወቅት ዜጋ መጽሔት ላይ ታትሞ የነበረና ለግንዛቤዎ ይጠቅምዎታል ብለን እንደገና ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አቅርበናል።
በአንዳንድ የአገዛዝ ሥርዓቶች በሀብት፣ በመደብ፣ ወይም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ አልያም በዘር የተዋቀረ ሥርዓት ይኖራል፡፡ ለምሳሌ በአፄ ኃይለ ስላሴ ጊዜ የነበረው የስልጣን ፍልስፍና ከሰለሞን ስርዎ መንግስት የሚመዘዝ የዘር ሀረግ ባለቤት መሆንን ይጠይቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው፡፡ ከሰለሞን ስርዎ (Solomon Daynasty) መንግስት ውጭ ላሉና በዚያ የስልጣን ዘር ሀረግ ውስጥ ያሉ ሆነው በጉልበትም ይሁን በብልሃት ስልጣን ላጡት ስልጣን የሚሰጣቸው በጋብቻ ትስስር እንደነበረ ለማስታወስ የአፄ ኃይለስላሴ ልጆች ከማንና የት ተጋብተው እንደነበረ ማስታወሱ በቂ ምሳሌ ነው፡፡

Saturday, May 25, 2013

እጅግ ብልህ መሪና ደጋፊዎቹ

ሚያዚያ 16. 2013
በታክሎ ተሾመ
አገራችን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በድርጅት፤ በቡድን፤ በተናጥል የሚደረጉ የመፈከር እንቅስቃሴ መኖራቸው ያለና የሚጠበቅ ነው።  በሁሉም ዘንድ  የሚደረጉ መፈከሮች  የሩቅና የቅርብ  ዓላማን የሚያመላክት መሪ ቃል ቢሆንም  ፍሬ ቃሉ በሁሉም ዘንድ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የመፈከሮችን ይዘት ድርጅቶችም ሆነ  ደጋፊዎች የሩቁንም  ሆነ የቅርቡን ዓላማ  ሳያሳኩ መንገድ ላይ ወደ ኋላ መመለስ የሚታይበት አጋጣሚ ብዙ ነው። ይህ ደግሞ ከልብ  ሳይታለምበትና ለመሰዕዋትነት ሳይዘጋጁ የሚጀመሩ እንቅስቃሴዎችና ድጋፎች አሻራ  ቢስ  ወይም  እድለቢስ  መሆናቸው  አይቀሬ  ነው።
የተለያዩ  ድርጅቶች፤ ስቪክ ማኅበራት፤ ግለሰቦች በአንድ  አጀንዳ  ዙሪያ  ሊስማሙ  እንደማይችሉ እያወቁ በሥም አንድነት ወይም ውህደት የምትለው ቃል ሽፋኗ ሲያምር ውስጧ ግን ነጣቢ ትሆናለች።  ደጋፊዎችም ለመደገፍ  የተነሳሱትም  ቢሆን  ዓላማውን  በውል  ያልተገነዘቡ  ሰለሚሆን  መጨረሻው  ማጉረምረም   ነው።
በተለያየ ጊዜ  የኢትዮጵያ መንግሥታት  ሥልጣናቸውን  በውርስና  በጠበንጃ  አፈሙዝ  እንደሚይዙ  በተከታታይ  ታይቷል።  የማስመሰያና  ዴሞክራሲን የሚያብረቀርቅ የወረቀት ሕጎችን  መደጋገም  ዋነኛ መለያ ባሕሪያቸው  ነው።  ነገር ግን  በወረቀት ላይ  ያሰፈሩት  የዴሞክራሲው  ይዘት  ምንነቱ  የማይታወቅ  ስለሚሆን ነፃነቴ ተገፈፈ  የሚል ጥያቄ  ሲነሳ ቦግታው  መልኩን ይቀይራል። ሕዝብ  ያልጠመረጣቸው  ባለሥልጣናት (መንግሥታት) ሕልውናቸውን  ለማስቀጠል  ኃይልን በመጠቀም ለነፃነት ትግል የሚነሱትን  ማሰርና  መግደል ይጀምራሉ። ስለሆነም በነፃነትና በባርነት መካከል በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት  አገሪቱ አኬልዳማ  ትሆናለች፤ ሆናለችም።

*ኢትዮጵያዊነት* ሳይኖረን አፍሪካዊነት የናፈቀው መንግስት ነኝ ባይ!

*ኢትዮጵያዊነት*
:- የነፃነት ቀመር! የማንነት መለያ! ነፃነት አዋጅ!..የሰው ልጅ መገኛ!  አላማ የጥበብ ፏፏቴ!.. ለተሳሳቱት !... ለቸልተኞች ማስጠንቀቂያ!... ለተሠቃዩት እፎይታ!...የባህል አውታር! ለተቸገሩት መፅናኛ!... ተስፋ ለቆረጡት ታላቅ ተስፋ!.. ለሠው ልጅ የተሠጠ ሰላማዊ አየር መተንፈሻ....!!....ለአፍሪካ ህብረት መመስረት ፈር ቀዳጅ! *ኢትዮጵያዊነት*
*ምን የሚሉት ኢትዮዽያዊነት ዛሬስ*
ማንነት ሳይኖረን አፍሪካዊ መሆን
ኢትዮጵያዊነት ሳይኖ አፍሪካዊነት የናፈቀው መንግስት ነኝ ባይ!
 የአፍሪካን ያክል እንኳ ክብር እመራሻለሁ ለሚላትና ብዙ ለሚነገርላት እናት *ኢትዮ* ቅንጣት ታክል የሚዲያ ሽፋን ሰጥቶ በአዝማሪዎቹ ያለፈፈ
ታላላቅ መሪዎቿ በብልህነት የሰሩላትን መልካም ስራ በመተው ሃውልቱ አይገባቸውም በሚል ገድል ለማዳፈን የሚሞክር፣ታላላቅ የነጻነት ፈርጦች ያደነቁትን መሪነት፣ስም ጠርቶ ለመናግር ያልቻለ
ለመሆኑ ይህ መንግስት ኢዮዮያዊ ነው ወይስ አፍሪካዊ ?
 ለአፍሪካ ቀደምት ታሪክ የሰሩ ታላቅ ሚና የነበራቸው እነ ሀይለስላሴ የሰሩት ሚና ሃውልት ሳይሰራላቸው  የጋናው ፕሬዝዳንት ለነበሩት ሙክራባ ሃውልት በመስራት ሟቹ መለስ ለሃይለስላሴ ሃውልት እንዳይሰራላቸው ሲከራከሩ የነበሩ የታሪክ አተላ ሟቹ መለስ ነበሩ !!!

ከሰብኣዊ

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

 (ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. / May 24, 2013)
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተመሠረተ 2007 እ.አ.አ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን የምዕራቡ ድንበራችን እርዝማኔው 1600 ኪ/ሜትር የጎን ስፋቱ ከ30 እስከ 60 ኪ/ሜትር የሚሆነውን ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብትና ልዩ ልዩ ብርቅየ የዱር አራዊትና አውዋፍ የሚገኙበት አንጡራ ለም የድንበር መሬታችንን ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ የገዥ ቡድን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በምስጢር መደራደሩን ፤ ከዚያም በኋላ መስጠቱን ለሕዝብ በማጋለጥ በተከታታይ ሰፊ መግለጫዎች ማውጣቱ፤ ለልዩ ልዩ የዜና አውታሮች ቃለ-ምልልሶች መስጠቱ እና የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በላይ፤ ይኽኑን አሳሳቢ የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ስፋትና ጥልቀት ያለው ታሪካዊ ሠነድ እንደሚያዘጋጅ ቃል መግባቱ የሚታወቅ ነው።
በዚሁ ቃል-ኪዳን መሠረት፣ ከሁለት ዓመት በላይ ሰፊ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ሲያካሂድ ቆይቶ፤ ይህኑን ዓብይ ጉዳይ በተግባር ለማዋል እንዲችል፤ የድንበሩ ኮሚቴ ከፍተኛ አካል የሆነው ምክር ቤት ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ( May 18 and 19, 2013 ) ታላቅ ጉባዔ በሲሊቨር ስፕሪንግ ከተማ፣ ሜሪላንድ፣ አሜሪካ (Silver Spring, Maryland, USA) አካሂዷል።

Friday, May 24, 2013

አንዱን ብሔር ጠልተን ሌላ መውደድ ማላገጥ ነው!



ኣንድ ሰው ኣማራን ጠልቶ ትግራይን ሊወድ ኣይችልም፤ጉራጌን ጠልቶ አፋርን ሊወድ አይችልም ትግራይ ጠልቶ ኦሮሞ ወይ ሌላ ህዝብ ሊወድ ኣይችልም።
ንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰው የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት በተለያየ ስም ሊያደራጅ ይችላል ችግር የለውም ግን በብሔር ተደራጅቶ ብሔሬን ነፃ ላውጣ ሲል ብሔር ከኢትዮጵያ የተመሰረተ ነው እኮ እረስተውት አይመስለኝም ማላገጥ ካልሆነ በስተቀር!  የፖለቲካ ideology ላይቀበለው ይችላል ግን ለብሔሬ ፣ለሕብረተሰ  ሲል ግን ለትልቋ ኢትዮጵያ አይመስልም ! ከኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ የሚወደው ህዝብ ሊኖረው ኣይችልም።

ህዝብን መውደድ የኣስተሳሰብ ዉጤት ነው፣ ህዝብ መጥላትም እንዲሁ። ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ መውደድ ካልቻልን የዘር ሓረጉ ማጣቀስ የመውደዳችን ምንጭ ሊሆን ኣይችልም። ምክንያቱም እኛ (ሁላችን) በወላጆቻችን በኩል ስንወለድ በፍቃዳችን ወይ ያለፍቃዳችን ኣይደለም። ከሆኑ ሰዎች ከሆነ ቦታ በሆነ ግዜ ተወለድን ወደዚች ዓለም ተቀላቀልን። ከዛም መወለዳችን መምጣታችን ወደድነው፤ ምክንያቱም የኛ መወለድ የተፈጥሮ እንጂ የምርጫ ጉዳይ ኣይደልም።

Thursday, May 23, 2013

Annual Report 2013 on Ethiopia


Freedom of expression

A number of journalists and political opposition members were sentenced to lengthy prison terms on terrorism charges for calling for reform, criticizing the government, or for links with peaceful protest movements. Much of the evidence used against these individuals consisted of examples of them exercising their rights to freedom of expression and association.
The trials were marred by serious irregularities, including a failure to investigate allegations of torture; denial of, or restrictions on, access to legal counsel; and use of confessions extracted under coercion as admissible evidence.

ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!! ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ
ሕገ ወጥነት ከዓላማችን አይገታንም!!!
ሕግ ምን ይላል?
አዋጅ ቁጥር ፫/፲፱፻፹፫ ዓ.ም
ስለ ሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የወጣ አዋጅ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው አካል ስላለበት ግዴታ በአንቀጽ ፬ ላይ እንዲህ ይላል

አንቀጽ ፬፤የማሳወቅ ግዴታ፤
፩/ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ህዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የሚያዘጋጀው ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከሚካሄድበት ጊዜ ቢያንስ ከ፵፰ ሰዓታት በፊት በጽሑፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
፪/ የማሳወቂያው ጽሑፍ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በከተማ ከሆነ የሚደረገው ለከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት፤ ከከተማ ውጭ ከሆነ ለአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
መልስ ሰጪው አካል የከተማ ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ያለበትን ግዴታና ኃላፊነት አንቀጽ ፮ ላይ እንዲህ ብሎ ደነግጋል፡፡
አንቀጽ ፮፤ የከተማው ወይም አውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊነት፣
፩/ ከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ጥያቄ በጽሑፍ ሲቀርብለት ሰላምን ከማስፈን ጸጥታን ከማስጠበቅና የሕዝቡን ዕለታዊ ኑሮ እንዳይሰናከል ከማድረግ አንጻር አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
፪/ ከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ሥፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለው ምክንያቱን በመግለጽ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ፲፪ ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለአዘጋጁ ማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው ወይም አውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፉ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ጊዜም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም፡፡