Sunday, August 25, 2013

“ሥልጣን ለመያዝ ጨዋታው ቀላል አይደለም”

“ሥልጣን ለመያዝ  ጨዋታው ቀላል አይደለም”
 
አብዮቱን ወደ መጠፋፋት ፖለቲካ የወሰደው ኢህአፓ ነው
የብቻ ሩጫ የትም እንደማያደርስ ከነመኢሶን ዘመን ጀምሮ አይተናል
በኢህአፓና በመኢሶን እስረኞች መካከል ልዩነቱ እጅግ በጣም የተካረረ ነበረ
ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የህይወቴ ትዝታዎች” በሚል ሰሞኑን ለንባብ ባበቁት መጽሐፍ ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤት እቁባይ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል፡፡
መጽሐፉን ያዘጋጁበት ዋና አላማ ምንድነው?
የአሁኑ ትውልድ ስለኛ ትውልድ ያልሆኑ ነገሮችን እየሰማ ነው፡፡ በማይሆን መንገድ የሚነገሩና የሚፃፉ ብዙ ነገሮች ስላሉ እነሱን ለማስተካከልና ለማረም ፈልጌ ነው፡፡ የኔ ትውልድ እና የአሁኑ ትውልድ እንዲግባቡ ለማድረግ የተሞከረበት መጽሐፍ ነው፡፡
በመፅሃፍዎ ላይ መኢሶን ለደርግ ያደረገውን ድጋፍ በተመለከተ፤ “ያን ድጋፍ ባያደርግ ኖሮ ደርግ ተጠናክሮ መውጣት አይችልም ነበር” ብለዋል።

የሌላውን ትግል ለማዳፈን መሯሯጥ ለውድቀት!

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ የገባው የሰማያዊ ፓርቲና የ‘33ቱ’ ፓርቲዎች የውዝግብ ዜና የተስፋ ጭላንጭል የተፈጠረለትን የዋህ ህዝብ እጅግ ቅር ያሰኘና ያሳዘነ እንደሆነ ከራሳችን የተጎዳ ስሜት በመነሳት ስለተረዳን፤ ‘የተቃዋሚ ድርጅቶቻችን ይማሩበት ዘንድ’ በሚል የየዋህ መንገድ ይህችን ኣጭር መልዕክት ለማስተላለፍ ተገደድን።
በሃገራችን የፖለቲካ ታሪክ ድርጅቶች በሰለጠነ መንገድ ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት ሲችሉ አልያም በልዩነታቸው ተቻችለው ሲጓዙ ሰምተን አናውቅም። ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን በጋራ ለነፃነት ከመታገል ይልቅ እርስ በእርስ ከመናቆር ጀምሮ እስከመጠላለፍ ሲደርሱ ማየት የተለመደ ሆኗል።

የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ (አቤ ቶኪቻው)

ሰላም ወዳጄ… ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅ….ፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት… እንዴት አሉልኝ.. እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንደዋዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ… ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል… ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ፤ አሯሯጡ ግን ወርቅ በወርቅ እንደሚያንበሻብሽ አትሌት ነው፡፡ ይሁና እኛ እንደሆነ “በርታ ግፋ” እያልን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም… አረ እንደውም ጊዜ ሆይ፤ …ሩጥልኝ ልጄ አምልጠልኝ ልጄ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ለኔውም አልበጄ… ብለን እንደ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ እንቀኛለን፤Meles Zenawi
እናልዎ ወዳጄ ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ ሙት ወቃሽ አታድርገኝም ሳልል የአቶ መለስ መሞት ለሰፊው ህዝብም፣ ሰፊ መሆን ለተሳነው ኢህአዴግም፣ መጠን አልባ ለሆኑት ተቃዋሚዎችም በጣም ስንሳለቅ ደግሞ ለወይዘሮ ሀዜብ ሳይቀር በርካታ ጥቅማጥቅሞች አሉት ብዬ ልሟገትልዎ ነው…!

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ኢየሩሳሌም አርአያ)

ከኢየሩሳሌም አርአያ
ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል።

በሀይማኖት ሽፋን የወያኔ የፖለቲካ አጀንዳን ማራመድ ይቁም!

አምባገነኑ የህውሃት ኢህአዲግ አገዛዝ አገራችን ኢትዮጵያን ላለፉት ሀያ ሁለት አመታት በጎሳ በቋንቋና በሃይማኖት ለመከፋፈል ሆድ አደር ተላላኪዎቹን አስርጎ በማስገባት ዜጎችን እርስ በርስ በመከፋፈል ሰይጣናዊ እኩይ አላማውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ጉዳይ አስፈጻሚው የሆኑትን ሆድ አደር ግለሰቦች በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ሳይቀር አስርጎ በማስገባት ይቅር የማይባል ከፍተኛ በደል በመፈጸም ላይ ይገኛል።
እነዚህን ሆድ አደር ወገኖች የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ጠንቅቆ ሊያውቃቸው ይገባል።

ሰንደቅ አላማውን ያዋረደው ማን ነው?

ጌታቸው ሺፈራው
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ‹‹መንግስት በእምነታችን ጣልቃ እየገባ ነው!›› በሚል ከአንድ አመት በላይ እየተቃወሙ የቀጠሉት የእስልምና እምነት ተከታዮች ሀምሌ 19/2005 ዓ/ም ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ኢህአዴግ ‹‹ሰልፈኞቹ የሰንደቅ አላማውን ክብር አዋርደዋል?›› የሚል ክስ ማቅረቡ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ የተበጣጠሰውን ሰንደቅ አላማው የያዙት ሰልፈኞቹን የሚኮንን መንግስት ቅጥረኞችም ይሁን ሰልፈኞቹ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ምንም እንኳ ህግ የማስከበር ሀላፊነት የነበረበት ቢሆንም ኢህአዴግ ጉዳዩን ያነሳው በእርግጥም በሰንደቅ አላማ ክብር ስለሚያምን አይደለም፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማም ሀምሌ 19/2005 ዓ/ም የተፈጠረው ስህተትን ማስተባበል አሊያም መክሰስ ሳይሆን በተፈጠረው ክስተት ‹‹ሌሎችን›› የሚከሰው ኢህአዴግ ራሱ ሰንደቅ አላማውን እያዋረደ መቀጠሉን  የተለያዩ ክስተቶችንና የራሴን ገጠመኝ በመቃኘት ማሳየት ነው፡፡Ethiopian national flag
ሰንደቅ አላማ የአንድ አገር ዋነኛ ምልክት በመሆን ያገለግላል፡፡ ለቅኝ ግዛት እጇን ያልሰጠችው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ደግሞ ከዚህም በላይ ክብር አግኝቷል፡፡ በተለይ በጸረ ቅኝ ግዛት ዘመን አፍሪካውያንና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ጭቁን ጥቁሮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የነጻነት አርማ አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡

Saturday, August 24, 2013

“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” ዶ/ር ተጋ “ዋስትና የናፈቃቸው ባለስልጣናት አሉ”

የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በዎርልድ ቪዥን፣ በተባበሩት መንግሥታ፣ በዓለምአቀፍ አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ … የሰጡት የዓመታት አገልግሎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ አገራት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ተጋ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዕርቅ፣ የሰላምና የፍትሕ ሒደት ውስጥ የተጫወቱት መጠነኛ ሚና በአገራቸው ተግባራዊ ሆኖ ለማየት የሚመኙና ለዚያም የሚቻላቸውን ጥረት ሁሉ ሲያደርጉ መቆየታቸው እስካሁን የሠሩት ሥራ ምስክር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ የአገር ውስጥና የውጭ ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው፡፡