Sunday, September 29, 2013

ሐረግነት፣ አውራነት እና ውራነት!? (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና)

“ትግል እና ዕውቀት ከያ ትውልድ ጋር አላከተመም” እስክንድር ነጋ
እንደ መነሻ፡-
ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ በነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትሟ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነሐሴ 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሠማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተጋብዘው “ኢህአዴግ በፖለቲካ ፍልስፍና አይን ሲዳሳስ” በሚል ርዕስ ያቀረቡትን ህዝባዊ ውይይት ለአንባቢያን በሚያመች መልኩ አስተናግዳ ነበር፡፡
እንደተገነዘብኩት፣ ዶ/ር ዳኛቸው መግለጽ የፈለጉትን ፍሬ-ሃሳብ በቀላሉ፣ በምሳሌ አዋዝተው፣ በአመክንዮ እና በተነፃፃሪነት የምሑራንን እና የፈላስፎችን ዕይታ ከነባራዊ የኢትዮጵያ ፓለተካ ጋር ቃኝቶ ለሁሉም በሚገባ መልኩ ማቅረብ አንዱ ተሰጥዎአቸው ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
ዶ/ሩ በዚህ የመወያያ ርዕስ፣ ካነሷቸው አንኳር ጉዳዮች መካከል አንዲቷ ሃሳብ ይበልጥ ቀልቤን ገዛችው፤ ደጋግሜም አሰላሰልኳት፡፡ በማስለሰልም ብቻ አልተገታችም- ሃሳቧ፡፡ ከቅርብ ጓደኛዬ ጋር ስንወያይባት ነበር፡፡

ሰበር ዜና፣ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

ዛሬ ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። ሙሉ ዘገባውን በቅርብ ይዘን እንቀርባለን ።

የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?

ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።
በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።

የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!

ሞረሽ ወገኔ (ብሪታኒያ)
Moresh Wogenie (UK)
Moresh ኤምባሲ በልማት ስም አባሎቹን ስበሰባ መጥራቱን ደርሰንበታል።
ይህ በብሪታኒያ በበጎ አድራጎት ድርጅትነት ተመዝግቤያለሁ የሚል “የአማራ ልማት
ማህበር” ወያኔ በአምሳሉ ቀርፆ ከፈጠራቸው ተለጣፊዎችና በኢሕአዴግ ስም
ከሚጫወትባቸው አሻንጉሊት ድርጅቶች አንዱ አካል መሆኑን ከመግለጫው ማወቅ
ችለናል።
ማሳወቅ የምንፈልገው ገዥው ፓረቲ ኢሕአዴግ ዛሬ በኢትዮጵያ የአማራውን ዘር
ለማጥፋት በሥውርም ሀነ በግልፅ ቀን ተሌት እየጣረ ባለበት በዚህ ወቅት የአማራ
ልማት ብሎ ተሰብስቦ ቡና መጠጣት ለአማራው ምንም ፋይዳ ያለው ውጤት
እንደማይኖረውና ይልቁንም የዲያስፖራው አማራ ወገኑ ላይ የተጋረጠውን እጅግ
አሳሳቢ ችግር እንዳይገነዘብ የማዘናጋት ሥራ ሆን ተብሎ እየተሠራ መሆኑን ነው።

Friday, September 27, 2013

ሰበር ዜና – አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ታሰሩ !

09
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንትና የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ 26 የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ለአምስት ሰአታት ከታሰሩ ቦሃላ ተለቀዋል። የፓርቲው አመራር አባላት የታሰሩት በአዲስ አበባ ከተማ ቅስቀሳ በተሰማሩበት ውቅት ነው። በጉዳዩ ላይ ያነጋግርናቸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙንት ሃላፊ አቶ ዳንዔል ተፈራ ይህ ሁሉ ከፍረህት የመነጨ መፈራገጥ እንደሆነ ገልጸው ከህዝቡ ጋር በመሆን እስከመጨረሻው ስረአቱን እንደሚታገሉ ግልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ነጋሶ መሪ ሆኑ – ከአበበ ገላው (ጋዜጠኛ)

“ካሁን በኋላ አባሎቻችን ሳይሆኑ መታሰር ያለብን እኛ ነን…” ዶ/ር ነጋሶ ለዘ-ሐበሻ የሰጡት ትኩስ ቃለ ምልልስ
ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ትናንት ለዘ-ሐበሻ ከሰጡት አጭር ቃለ ምልልስ በኋላ በፌስ ቡክ ገጹ ያሰፈራት አጭር ግን ብዙ የምትናገር መልዕክት፦
መሪ ማለት ሌሎችን አጋፍጦ ዘወር የሚል ሳይሆን ከፊት ቀድሞ የመጣውን ሁሉ የሚጋፈጥ ማለት ነው። በትናትናው እለት የአንድነት አባላት በሰላማዊ መንገድ ስራቸውን በመስራታቸው ሲታሰሩ አብሬ እታሰራለሁ በማለት መደ ቤት ሳይሆን ወደ እስር ቤት ገብተዋል። በዚህም የታሰሩትን አስፈትተው መሪ መሆናቸውን አስመስክረዋል። ከዚህ በሁዋላ መታሰር የሚገባን እኛ እንጂ አባላቶቻችን አይደሉም ማለታቸው ቁርጠኝነታቸውን ያሳያል። ነጋሶ ወያኔን በቃኝ ብለው ህዝቡን በመቀላቀል ክብራቸውን አስመልሰዋል።

No Human Rights = No Development

Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network Submit Human Rights Report on Ethiopia to the United Nations

OAKLAND CA- In a report submitted to the UN Human Rights Council’s Universal Periodic Review (UPR) on September 15, 2013, the Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network outlined the human rights and international law violations perpetrated by the government of Ethiopia in the name of country’s development strategy.