Tuesday, December 31, 2013

የከተማ አብዮት!


(ተመስገን ደሳለኝ)
ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ አብዮቶች (የተሳኩትም ሆነ የከሸፉት) ሰላማዊውንና ህጋዊውን መንገድ የተከተሉ ባለመሆናቸው ዛሬም ይዘገንናሉ፤ ለወደፊቱም ባልተደገሙ ያሰኛሉ፡፡ ስለምን ቢሉ? ግድግዳው ላይ የተቸከቸከው ፅሁፍ እንዲህ የሚል ምላሽ ያስነብባልና፡- በጭቁን ሕዝብ ስም የብዙሀኑን ቤት አፍርሰዋል፤ ሀገርና ታሪክ ለመቀየር የማይሳናቸው አፍላ ወጣቶችን እርስ በእርስ አጫርሰዋል፤ ‹አንቱ› ሊባሉ የሚችሉ ምሁራንን በአንድ ጀንበር ወደ ትንታግ ነፍሰ-ገዳይነት ቀይረዋል፤ ክስረቱም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳ ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሷል…

የማለዳ ወግ ! አይ የእኛ ነገር :( የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው ነቢዩ ሲራክ

ሰሞኑን ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ፣ ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ ፕሮፊሰር ይስሐቅ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በየአይነቱ ሰማን ። ይህ ሁሉ ታዲያ በፈረንጆች አመት በዋዜማው ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?

የማለዳ ወግ ! አይ የእኛ ነገር :( የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው ነቢዩ ሲራክ

ሰሞኑን ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ፣ ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ ፕሮፊሰር ይስሐቅ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በየአይነቱ ሰማን ። ይህ ሁሉ ታዲያ በፈረንጆች አመት በዋዜማው ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?

የጃዋር መሀመድና የአንዳንድ አጨብጫቢዎች አደገኛ መንገድ በአጭሩ

ዋቅጅራ ሶሪ
jawar mohamed
“በእናቴ መንዜና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነኝ፤ በአባቴ የአርሲ ኦሮሞ እና ሙስሊም ነኝ፤ ከኔ ወዲያ ለኢትዮጵያዊነት ምልክት ሊሆን የሚችል የለም” ጃዋር ይህን ያለው ከዓመት በፊት ወጣቱ ተንታኝ እየተባለ በኢሳት በተደጋጋሚ ይቀርብ የነበረ ሰሞን ነው።Jawar Mohamed Muslim fundamentalist
የተመቼው እና ፖለቲካዊ ንግዱ የደራለት ሲመስለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ተመሣስሎና አድፍጦ የቆየው ጃዋር መሀመድ ፤በግብጽ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ የሙርሲ ባለስልጣናት በአባይ ግድብ ያደረባቸውን ንዴት በግልጽ በቴሌቪዥን ተሰባስበው እየፎከሩ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲዝ ቱ ሰማ። የሙርሲ ባለስልጣናት ከሰነዘሯቸው አማራጮች አንዱ፦” የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን የሙስሊም ክንፍ ወይም ኦብነግን ማስታጠቅና መርዳት” የሚል መሆኑን የሰማው ጃዋር ሳይውል ሳያድር በአልጀዚራ ላይ ቀርቦ በግልጽ “ኦሮሞ ፈርስት” በማለት የኢትዮጵያዊነት ቆቡን አሽቀንጥሮ ጣለ። ሜንጫው ተከተለ፤የሙስሊሞችን የመብት ትግል ከኦነግ ጋር እያገናኘ ተናገረ፣ ኢትዮጵያውያን ከኦሮሚያ ይውጡ! እያለ መፈክር ሲያሰማ ተደመጠ…

Thursday, December 26, 2013

ለኢትዮጵያ ሰማያዊ ፓርቲ ምስክርነት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ሰማያዊ ፓርቲን እንደፖለቲካ ድርጅት/ፓርቲ ለምን እንደምደግፈው፣
እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013 ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው አርሊንግተን ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ  ንግግር እስካደረግሁባት ዕለት ድረስ በበርካታ ጥያቄዎች እወጠር ነበር፡፡ አንደኛው ተደጋግሞ የሚጠየቀው ጥያቄ ለበርካታ ዓመታት ገለልተኛ ሆኘ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን ጋር ሳልወግን ከቆየሁ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ለሰማያዊ ፓርቲ ለምን ያልተቋረጠ ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደምገኝ በሚቀርብ ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

ኢትዮጵያ የጋራችን ኤርትራ የግላችን! “ከ 40 ግድብ አንድ የአሰብ ወደብ

ኤርትራዉያኖች ተበልጠዉ በኢትዮጵያ ተንደላቅቀዉ የሚኖሩበትን ሁኔታ ከተነጠቁ በሗላ እንደገና እጃቸዉ ለማስገባት በተለያየ ዘዴ ቢጠቀሙም ህዋአት እና ሻቢያ “እባብ ለባብ ይተያያል ካብ ለካብ” አይነት ሆነና ኤርትራዉያን የፈለጉትን ያህል ሳይሆንላቸዉ ቀርቶ እዚሀ ላይ ተደረሷል። የጸሀየ ግብአተ መሬት ፉከራ ከከሸፈ በሗላ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያን ሊበትንልን ይችላል የሚሉትን ሀይል እና ዘዴ ቢበደሩም መላ ቢመቱም ቢያሰባስቡ እና ቢያሰለጥኑም፤ የኢትዮጵያ አንድነት ፍንክች ሳይል ቀርቶ እዚህ ላይ ይገኛል። የኤርትራ ምሁራን ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸዉ ተራ ወርደዉ የሚያስገምት ጽሁፍ ቢጽፉም፤ በቀይ ባህር ማተሚያ ቤት የእዉሸት ፋብሪካቸዉ ተረት መሰል የኢትዮጵያ ታሪክ ቢያሳትሙም፤ ቅጥፈት የተሞላዉ ወረቀት ቢጽፉም ድካማቸዉ ሁሉ ያለምንም ፍሬ ልፋት ብቻ ሁኖ ቀርቷል
ታድያ ለሁሉም ብልሀት አለዉ እንዲሉ ይህ ዘዴ ያለመስራቱን የተረዱ ኤርትራዉያን አቶ መለስንና ለኤርትራ ስስ ልብ ያላቸዉን የህወአት ባለስልጣኖች በመጠቀም ዛሬም ከዜጋዉ በላይ የኢትዮጵያን በረከት እየተጎናጸፉ ይገኛሉ። በተለይ ከአቦይ ስብሀት አለንላችሁ መግለጫ በሗላ ብዙ ኤርትራዉያን ባላቸዉ ንክኪ አማካኝነት በብዛት ወደ ሀገር ጎርፈዋል ከኢትዮጵያ ሳይባረሩ የቀሩትን ወገኖቻቸዉንና በዉጭ ሀገር በሚኖሩ ኤርትራዉያን አማካይነት የዉስጥ ለዉስጥ ግንኙነታቸዉን በማጠናከር ኢትዮጵያ ዉስጥ የቀድሞ ቦታቸዉን ይዘዋል።

ሕይወትም የሚጀምረው ራስን ከመሆን ነው – ሰው ራሱን ሲያክል ሌላ ብዙ ነገር ማድረግ ይቻለዋል” ቴዎድሮስ ካሣሁንን

“ሕይወትም የሚጀምረው ራስን ከመሆን ነው – ሰው ራሱን ሲያክል ሌላ ብዙ ነገር ማድረግ ይቻለዋል” ቴዎድሮስ ካሣሁንን


” ቅንነት ከሌለ ጥሩ ነገር ማየት እንደማይቻል አውቆ። ታሪኩንም በቅንነት ስሜት መመርመር ይኖርበታል። የባለታሪክ ሰዎችን ጥሩ ነገር መውሰድና ጥሩ ያልሆነ ነገራቸውን ደግሞ እንዳይደገም ለማረም መትጋት ከኛ ከወጣቱች ይጠበቃል። ትልቁና ቁልፍ ነገር የማንነትን መ...ሠረታዊ ጥያቄ ከመገንዘብ ይመነጫል። ሕይወትም የሚጀምረው ራስን ከመሆን ነው። ሰው ራሱን ሲያክል ሌላ ብዙ ነገር ማድረግ ይቻለዋል።… ስለዚህ የነገር ሁ ምንጭ ፍቅር ስለሆነ ከፍቅር የሚጀምረውን ህይወት በፍቅር ለመጨረስ ቅንነት ያስፈልጋል። አመጣጡን ያዬ አካሄዱን ያዉቃልው ምክኒያቱም ታሪኩን እየዞረ የማያይ ተጋዥ የኋላ መመልከቻ መስታወት የሌለው መኪናን ይመስላልና “