Friday, February 28, 2014

ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ

(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
hailemedhin

ይድረስ ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፡- በኢትዮጵያ ታሪክ ተወቃሾቹ የኦሮሞ ሕዝብና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ነውን እንዴ?!

በዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን  - nikodimos.wise7@gmail.com
‹‹ዕርቅና ሰላም የሕይወት ቅመም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደውለታ ቢስ ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ የሚሆን መልስ እነሆ!›› በሚል ርእስ የጻፉትን ጦማር እጅግ የማክበርዎና ኢትዮጵያዊው የምሆን ወንድምዎ ደጋግሜ አነብበኩት፡፡ ፕሮፌሰር በትክክል ተረድቼዎት ከሆነ እርስዎ በጽሑፍዎ ለማስተላለፍ የፈለጉት ዋንኛ መልእክትዎ፣ አንድም ‹‹ዕርቅንና ሰላም መስበክ›› ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት ወይም ውለታ ቢስ አድርገው ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ መልስ ይሆናል በሚል እነሆ ያሉት ጦማር እንደሆነ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስናን ለመሸፋፈን የሚደረገው ዘበት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በማዕድኑ ዘርፍ የሚያካሂደውን ሙስና በማደብዘዝ እና በመሸፋፈን ንጹህ መስሎ ለመታየት እና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን ለማግኘት በማሰብ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት(Extractive Industries Transparency Initiative (EITI)) ለተባለው ድርጅት ዕጩ አባል ለመሆን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ይፍጨረጨራል፡፡ የገቢ ምልከታ ተቋም/Revenue Observation Institute የቦርድ ሊቀመንበር እና የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የቦርድ አባል የሆኑት አንቶኒ ሪቸር እንደሚሉት ከሆነ እ.ኤ.አ በ2010 ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ነበር፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ‘የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት አዋጅ (Proclamation on Charities and Societies) የሲቪክ ህዝብ ማህበራት ቡድኖች ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነው እና በሂደቱም ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚከለክል ደንቃራ በመሆኑ ነው የሚል ድምዳሜ ሰጥቷል፡፡

በማተብዋ ልዳኝ – ወድቃ የተነሳችው (ከስንሻው ተገኘ)

ከስንሻው ተገኘ
ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ) ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል።

Wednesday, February 26, 2014

በጭካኔ እየተገዳደልን፣ ወዴት እየሔድን ነው? የአብዱ ሁሴን ይማም ግድያ

abdu hussien

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”

ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!
musevini
ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

Tuesday, February 18, 2014

“ጥቁሩ ሰው” – የጥቁር ሕዝብ አባት

ከስንሻው ተገኝ
አንድ ዘመን ሥርዓተ መንግስቱ በመቆየትም ሆነ አባላቱ የአሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የተረት ዓለም ሰዎች ስለ መሰሉን- ሁሉም ነገር ስለገለማን አዲስ ሥርዓት፣ አዲስ መሪ፣ አዲስ ዘመን መናፈቅ ይዘን ነበር። ሰዓሊ ሁሉ፣ ደራሲ ሁሉ፣ ጸሐፌ -ተውኔት ሁሉ እጁን የሚያሟሸው በቴዎድሮስ ሥዕል፣ ተውኔትና ታሪክ ሆነ። ብርሃኑ ዘሪሁን- የቴዎድሮስ እንባ -(መጽሐፍ) ከዚያ በፊት ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት- ቴዎድሮስ (ተውኔት) አቤ ጉበኛ – አንድ ለእናቱ (ታሪካዊ ልቦለድ) ጸጋዬ ገብረ መድኅን – ቴዎድሮስ (ተውኔት)…ሥዩም ወልዴ -ሥዕል..ታደሰ ወ.አ….ቅርጻቅርጽ እና የሥነ ጥበባት ትምህርት ቤት ሥስት አራተኛ ተማሪዎች..የቴዎድሮስ ሥዕል ግጥም -ቅኔ- ሥዕል አለፈላት።Ethiopian king Atse Menelik
ከአሮጌና ከገለማ ሥርዓት ነፃ የሚያወጣ አመጸኛና አመጻ የሚመራ ጀግና ስንፈልግ ባጀንና ቴዎድሮስን አገኘን። ከመቶ አመት በኋላ ነው ቴዎድሮስ የተፈለገው። በአጤው ሥርዓት በአንዳንድ ደራስያንና የዘመን ታሪክን በውዳሴና በነቀፋ በሚያቀርቡ ግለሰቦች ዘንድ እንደጭራቅ ይቆጠር የነበረው መይሳው ካሣ በለውጥ መሪነት የተፈለገበት መሪ ነበር። አብዮታዊው መሪ ጓድ መንግሥቱ እንኳ፥ “ቴዎድሮስ” (ምናልባትም ዳግማዊ ቴዎድሮስ) እኔ ነኝ። የዚህን ሕዝብ አብዮት እንድመራም ከሙታን የተጠራሁ ነኝ” እስከ ማለት ደርሰው ነበር። በቴዎድሮስ መንገድ አልተጓዘም እንጂ። በተረተኞች፣ በተረበኞችና በዋልጌዎች፣ በጐታቾችና በክፍፍል በኖሩ ዘንድ ተወዳጅ ያልሆነው ሕልመኛው ቴዎድሮስ በእርግጥ ከዘመኑ አርቆና አልቆ የሚያይ ስለሆነ ከወቅቱ ደባትርና ከመሳሰሉት ጋር ስምምነት አልነበረውም።