ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ በባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ በማስፈራራት ጀምሮአል። በምርጫ ቅስቀሳ የፈራው የወያኔ መንግስት ፓርቲዎችን በክርክሩ መርታት ሲሳነው በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አይተናል በክርክሩ የህዝብ አመኔታን ያጣው ገዢው ወያኔ የሚጨብጠው ቢያጣ ንቢቱን ተመስሎ በተሰራ ባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ ላይ ይደነፋ ጀምሮአል ድሮም ኮሮጆ በመስረቅ ነው 25 ዓመት በሃይል የገዛው ።
ገዥው የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አምስተኛው የኢትዬጲያ ብሄራዊ ምርጫ ግይካሄዳል ፡፡ ሶስተኛውና ተስፋ የፈነጠቀው አገራዊ ምርጫ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የፓለቲካ ምህዳር መዘጋት ከተጠናቀቀ በኋላ የተካሄደውን አራተኛው ምርጫ ኢህአዴግ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫ “በማሸነፍ” ተቆጣጥሮታል፡፡
ከቀናት በኋላ የሚካሄደው አምስተኛ አገራዊ ምርጫ የፓለቲካ ምህዳሩን ለማሻሻል የሚረዳና መጠነኛ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እያዳከመ ተቺዎችን እና ሌሎች ነጻ ድምጾችን ለእስር ዳርጎ በከፍተኛ ጫና ታጅቦ ይካሄዳል፡።
የወያኔ መንግስት ህዝብን ማስተዳደር የማይችል አሸባሪና ዘረኛ ፓርቲ ነው። የኢትዮዽያ ህዝብም አንቅሮ ከተፋው ቆይቷል ወያኔም የተረዳው መሆኑን በሰሞነኛ ድርጊቱ እየታየ ነው። አንዳንድ የአፍሪካ አንባገነን መንግስታት ሽንፈታቸውን በሃይል ለምቀበል የሚደረገው ሙከራ ወያኔ ከምርጫው ቀድሞ ወታደሩን እና ታንኩን በአደባባይ ኮልኩሎ ህዝብን ማሸበር የተሸናፊነት ምልክት መሆኑን አውቀናል።
ወያኔ ተንቦጫብጯል ወያኔ ፈርቷል እንደለመደው የህዝብን ድምጽ ሊሰርቅ አሰፍስፋል ለተከታይ ፭ አመት የህዝብን በዘረኛ እና በግፍ አገዛዝ ሊገዛ አሰፍስፎ በማስፈራራት ታንክ ጭምር ከተማ ላይ በማሰማራት የህዝብን ድምጽ ለመገደብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለዚ የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃ በቃ በቃ በቃ በማለት ይህን የዘረኛ መንግስት በአንድነት ልናስወግድ ይገባል።
ሞት ለወያኔ
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር
No comments:
Post a Comment