ሻለቃ ፅጌ ትባላለች፤ (አሁን ኰሎኔል) ..የጄ/ል ሰዓረ መኮንን ባለቤት ናት። ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 1997ዓ.ም ምሽት ኢህአዴግ ምርጫውን አስመልክቶ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ጠርቶ ነበር። ሻለቃ ፅጌ ከጠባቂዋ ደህንነት ጋር በስፍራው ተገኝታ ሻማዋን እያበራች በጦር ሃይሎች ሆ/ል በር በኩል ታልፋለች። በሆስፒታሉ በር ከቆመው ጠባቂ ዘብ ጋር አብራ የምታወራ የሆ/ ሉ ሜንስ ቤት ሰራተኛ እያፌዘች «ስሚ አንቺ የያዝሽው ሻማ የኢህአዴግ ንብ እሁድ ይቃጠልበታል..በቅንጅት» ትላታለች። ሻለቃ ፅጌ ተንደርድራ በመሄድ በጥፊ ስትማታ ልጅቷም አንገቷን በማነቅ ሻለቃዋን መሬት ላይ ጥላ ስትረግጣት የሻለቃዋ ደህንነት ሽጉጡን መዞ ሲጠጋ የበሩ ዘብ ክላሹን ወድሮ ይተናነቃሉ። ሻለቃዋን አላውቋትም ነበር።
በዚህ መሃከል ጥይቶች ይባርቃሉ። ወዲያው አንድ መኮንን ከውስጥ ይመጣል። ሁለቱንም እጅ ወደላይ ብሎ መሳሪያ እንዲፈቱ ያደርጋል። ሻለቃ ፅጌን ያውቃት ስለነበረ ይርበተበታል። ክፉኛ የተደበደበችው ሻለቃ ለባልዋ ስልክ ትመታለች። አሁን እስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ የግቢውን ጠባቂና አሰለፍ የተባለችውን የሜንስ ቤት ሰራተኛ አሳፍኖ አስወሰደ። አሰለፍ 4ኛ ክ/ጦር በሚባለው ግቢ ለ3 ወር ተደብድባ ህይወቷ ሲያልፍ፤ ወታደሩ ወደ ታጠቅ ተወሰደ። የደረሰበት ግን አልታወቀም። በነገራችን ላይ አሰለፍ በድብደባ መሞቷን ሻለቃ ፅጌ ስትሰማ ለብዙ ቀናት ክፉኛ ደንግጣ ነበር።
No comments:
Post a Comment