ከወደ ብሩንዲ ሕዝብ ነቅሎ ተነስቷል። በአገሪቱ ሊካሄድ ጥቂት ጊዜያት በቀሩት አገራዊ ምራጫ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ራሱን በእጩነት ያቀረቡት አንባገነኑ ፔሬ ኑኩሩንዚዛን ሕዝብ በቃህ በማለት ተናንቋቸዋል። ጭንቅ ውስጥ የገባው የፔሬ አገዛዝ ከሕዝባዊ ማዕበሉ ለመትረፍ እየተወራጩና አንዳንድ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ቢሆንም ሕዝቡ እርምጃዎችን ሳይገቱት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ጉዞውን ወደ ቤተ መንግስቱ አድርጓል።
ከጥቂት አመታት በፊት የሰሜን አፍሪካ አምባገነን ገዥዎችን ያንኮታኮተው ሕዝባዊ አመጽ በመቀጠል ባሳለፍነው አመት የምዕራፍ አፍሪካዋን ቡርኪናፋሶ አምባገነን ገዥ ብለስ ኮምፓወሬን ከስልጣን መመንገሉ የሚታወስ ሲሆን በዚህ በያዝነው አመት ደግሞ ሕዝባዊ ማዕበሉ ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ቡሩንዲ አምርቷል። መቼም ከሰሞኑ የምስራቅ አፍሪካ አምባገነኖች እንቅልፍ አይኖራቸውም። ይሄ ኮሽታ ሕውሓቶችን ምንኛ ሊያስበረግጋቸው እንደሚችል አስቡት። በነገራችን ላይ የሕዝባዊ ማዕበሉ ቀጣይ መዳረሻ የት ይሆን የሚለው ጥያቄ አሁን ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል!?! የለውጡ ንፋስ በየ አቅጣጫው እያስገመገመ ወደ ሚገኝባት አገራችን ኢትዮጵያ ያመራ ይሆን!?! የምናየው ይሆናል። ለማነኛውም እስኪ በዚህ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እንወያይ ጎበዝ!
No comments:
Post a Comment