ሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት በተነሳ የውጪ ዜጎችን ኢላማ ባደረገ ተቃውሞና ጥቃት ስትታመስ ቆይታለች “አፍሮ ፎቢያ” ተብሎ እስኪሰደብ ድረስ በዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ስደተኞች በዚሁ ዜኖ ፎብያ በተባለ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውም የሚዘነጋ አይደለም
አሁን ደግሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በህገ ወጥ መንገድ ወደሀገሪቱ ገብተዋል ያሏቸውን የውጪ ዜጎች ማደንና ማሰር እንደጀመሩ ነው የተነገረው ደቡብ አፍሪካ መሰንበቻዋን የመከላከያና ፖሊስ ሀይሏን በጆሀንስበርግ አሰማርታ ህገ ወጥ ስደተኞችን ማሰሯ ተሰምቷል
በዚህ ዘመቻ እስከአሁን 470 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማ ሲሆን ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ይገኛል ነው የተባለው ስለነዚሁ የውጪ ዜጎች ዝርዝር መረጃ እስከአሁን ያልወጣ ሲሆን በቀጣይነት በሀገሪቱ ህግ መሰረት እስር ይጠብቃቸው እንደሆነ ወይም ወደመጡበት ሀገር እንዲመለሱ ይደረግ እስከአሁን የተባለ ነገር አለመኖሩ ነው እየተዘገበ የሚገኘው
No comments:
Post a Comment