Tuesday, December 11, 2012

አበሻ እንኳን አሜሪካ ማርስ ላይ ቢወጣም መከፋፈሉ አይቀርም!



የዛሬውን ፖለቲካዊ ወግ በጥያቄ እንድጀምር ፍቀዱልኝ፡፡ ጥያቄው ደግሞ ለናንተ ነው፡፡
“በዘንድሮ የከፍተኛ ተቋማት ተመራቂዎች ላይ ምን ለየት ያለ ነገር አስተዋላችሁ?” በተለይ በኢቴቪ መስኮት ከምረቃ በኋላ ምን እንደሚሰሩ ሲነግሩን የሰነበቱትን ተመራቂዎች ማለቴ ነው፡፡ ተመራቂዎቹ ለኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰጡትን ምላሽ የታዘቡ አንዳንድ ተመልካቾች፤ ሁሉም አንድ ዓይነት ጥያቄ ከነመልሱ የተሰጣቸው ይመስላሉ የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ ነገርዬውን ስታዩት ግን እውነት ይመስላል (መረጃ ማቅረብ ባይቻልም!)
“ከመንግስት ሥራ ጠባቂ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ መሆን ነው የምፈልገው” ከሁሉም “የኢቴቪ ተመራቂ” አንደበት የሚሰማ ምላሽ ነበር፡፡
ባለፈው ሳምንት እዚሁ ጋዜጣ ላይ ባለድግሪ ኮብልስቶን ጠራቢዎችን አስመልክቶ ሁለት የአገሪቱ አንጋፋ ምሁራን በሰጡት አስተያየት፤ ማንም የፈለገውን ተምሮ የፈለገው ሥራ ላይ የመሰማራት መብት እንዳለው ገልፀዋል (በደንብ እስማማለሁ!)
ተመራቂዎቹም እየነገሩን ያሉት የልባቸውን ከሆነ “እሰየው” ብለናቸዋል (ንግግራቸው የተጠና ተውኔት ቢመስልም) አንድ ግልፅ ያልሆነልኝ ነገር ግን አለ - ተመራቂዎቹ “ሥራ ፈጠራ” የሚሉት ያንኑ ኮብልስቶን ይሆን እንዴ?

Monday, December 10, 2012

አገራችንን የማን እንደሆነች አላወቅናትም !

በመካከላችን አንድነት የሚኖረው መቼ ነው? መተሳሰብ የሚሰፍነው መቼ ነው? ለየራሳችን ፍላጎት መተሳሰቡን (‹‹የመረዳዳት ባህላችንን››) እናቆየውና የራሳችን የሁላችን ስለምንላት ሀገራችን የጋራ አስተሳሰብ አለን? አይመስለኝም፡፡ ብዙዎቻችን ከራሳችን ውጭ ማንም ያለ አይመስለንም፡፡ ሀገሪቱም ከእኛ ውጭ አሳቢ እንደሌላት እንድመድማለን፡፡ አለዚያም ሀገሪቱን ረግጠን እና በሀገሪቱ አላግጠን ለማለፍ መለኮታዊ ቅባት እንደተቸረን ይሰማናል፡፡ ይህማ ባይሆን እኩልነታቸውን አስከብረናል በምንልበት ሀገር ዘለፋን አፈናጥረን በተውን ! 

Saturday, December 8, 2012

“ሹመት፤ ማዕረግ ሳይሆን የአገልግሎት ቃል ኪዳን ነው”

መሥራት ካልቻላችሁ ለምን ሾምኳችሁ ከሚል አለቃ ይሠውረን፡፡ መሥራት ሳይችሉ ሹመትን ለሹመት ብቻ ብለው ከሚቀበሉም ባለሟሎች ያድነን፡፡ የህዝብን ብሶት የሚፈቱ እንጂ ህዝብን እናስወግድ የሚሉ እንዳይገጥሙን እንፀልይ፡፡ ለህዝቡ ነው ለእኔ የቆምከው? የሚል ሹም ላያችን ላይ እንዳይንሰራፋ ነቅተን እንይ፡፡ የሚያስረዳ፣ ዐይን - የሚገልጥና ለመልካም አስተዳደር የቆመ ባለሥልጣን እንጂ እኔ ያዘዝኩህን ብቻ ፈጽሞ የሚል አይዘዝብን! ገደል እንዳንገባ ገደሉን የሚያጥርና ከመውደቅ የሚያድነን እንጂ “ወዶ ገደል ገባ!” ከሚል ኃላፊ ያድነን፡፡ ከሚያየው የማያየው የሚሻልባት አገር ሳትሆን፤ ልቦና የሰጠው ህዝብ የሚኖርባት አገር ትሆን ዘንድ የልባችን ይሙላልን፡፡ 

Friday, December 7, 2012

የተለመደው የምርጫ ውዝግብ የተጀመረ ይመስላል ?





የተለመደው የምርጫ ውዝግብ የተጀመረ ይመስላል - እዚህች አዲስ አበባ ሸገር እምብርት ላይ፡፡ በእርግጥ የማስጀመርያው ተኩስ ገና አልተተኮሰም ፓርቲዎች ግን እስኪተኮስ እንኳን አልጠበቁም፡፡ እናም በግንቦት ለሚካሄድ ምርጫ በጥቅምት ውዝግብ ተጀምሯል እያልኳችሁ ነው (በምርጫ ውዝግብ ሪከርድ ሳንሰብር አንቀርም!) ይሄ እንግዲህ ለአካባቢና ለአዲስ አበባ ምርጫ ነው፡፡ በ2007 ዋናው አገራዊ ምርጫ ላይ ምን እንደሚፈጠር የሚያውቀው አንድዬ ብቻ ነው፡፡ 

ማወቅ ያለብን ከዚህ በሁዋላ ለወያኔ/ኢሕአዴግ ተጨማሪ ዕድሜ ከተሰጠው፣ ከወያኔ/ኢሕአዴግ በላይ ወንጀለኛ የሚሆነው ተቃዋሚው ነው።






የወያኔ  ጥንካሬ፣ዓላማው፣አደረጃጀቱ፣ያሰባሰበው  የሰው  ኃይል  ወይም  የነደፈው  ፖሊሲ
አይደለም።  የጥንካሬው  መሠረቱና  ምንጩ  ወያኔ  ጠንካራ  ተቃዋሚ  የሌለው  ዕድለኛ  ቡድን
መኆኑ  ነው፡፡  የሕወሓት  ጥንካሬ  ሌላ  ምንም  ሳይሆን፣የተቃዋሚው  ሁለንተናዊ  ድክመት
ነው።  የተቃዋሚው  ድክመት  መሠረትና  ምንጩ  ደግሞ፣  የተበታተነና  እንኩዋን  አብሮ
ለመሥራትና  ለመኖር  የጋራ  ጠላቱ  በሆነው  ወያኔ  ላይ  አንድ  ዓይነት  አመለካከት  መቅረጽ
ያልቻለ  መኆኑ  ነው።  ይህም  በመሆኑ፣የተቃዋሚው  ሁለንተናዊ  ድክመት፣ለወያኔ  ዙሪያገብ
ጥንካሬ ሰጥቶት ይገኛል።

አይ ባይ ያጣው የኢህአዴግ ህገ መንግስት !


106 አንቀጽ የተዋቀረዉን የኢህአዴግን ህገ መንግስት በጨረፍታ።
ያዉ ሁላችንም እንደምናዉቀዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ህገ መንግስት የተረቀቀዉ 18 አመት በፊት ህዳር 29/1987 . ነበር። ከነሐሴ 15/1987 . ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ዉሏል።
አንቀጽ 9/1 ህገ-መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ ነዉ
አንቀጽ 10/2 የዜጎች እና የህዝቦች ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ
አንቀጽ 12/1 የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት
አንቀጽ 21/1 በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸዉን በሚጠበቅ ሁኔታዎች ሜአዝ መብት አላቸዉ
አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸዉ

Monday, December 3, 2012

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ተግባሩና ተግዳሮቱ


1. ህግ የማያከብር መንግስት
የኢህአዴግ መንግስት የፍትህ የዳኝነትና የፖሊስ አካላት እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት አንዳንድ የሚወስዱትን ህገ-ወጥ እርምጃ ሳይ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የኢህአዴግን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን ..ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች.. አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ ..አባል.. እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡