Thursday, January 3, 2013

ሽምግልናውን ሲያካሒድ ከነበሩ አስታራቂዎች የቤተክርስትያን ኣባቶች መካከል ኣንደኛው ከኢትዮጲያ ሲባረሩ ሁለተኛው የደረሱበት ኣይታወቅም


የኣዲስ ኣበባዎቹ ተደራዳሪ ኣባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የረካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሶሳንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት ኣባቶች ኣንደኛው የሆኑት ብጹነ ብጹነ ኣቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ኣሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉኣል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ ኣለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል::

24 injured in ethnic conflict among university students

ADDIS ABABA - At least 24 students were injured on Thursday when ethnic-based clashes erupted among university students on Arat Kilo campus of Addis Ababa University.
The fights broke out when students heading to the cafeteria in the morning saw the walls of the main library on campus and other places covered with graffiti that denigrate the Oromo people.
ADDIS ABEBA UNVIVERSITY MAIN CAMPUS 
The violent clashes included window smashings and physical fights continued into the middle of the day, though police tried to quell the unrest several times. Police also threw into custody a handful of students suspected of playing leading roles in the unrest.

‹‹ሹመት ካልሠሩበት ምን ይፈይዳል?››

ሙስና እንደ ሸረሪት ድር በየቦታው አድርቷል፡፡ መልካም አስተዳደር ጠፍቷል፡፡ የሕግ የበላይነት አለ በሚባልበት አገር ፍትሕ ርቋል፡፡ በሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶች ተጨፍልቀዋል፡፡ ሥርዓቱን ሙስና እንደነቀዝ እየበላው ስለሆነ የመፍትሔ ያለህ እየተባለ ነው፡፡ እኔ የምለው ተሿሚዎቹ ይህንን ችግር ለማስወገድ ካልሠሩ ሹመታቸው ምንም አይረባንም እላለሁ፡፡ ይህንን ሐሳቤን ለጓደኛዬ ብነግረው በመገረም እያየኝ፣ ‹‹አስተያየትህን በአስቸኳይ ለኢቲቪ ለምን አትልክም?›› አለኝ፡፡ እኔስ ምኔ ሞኝ ነው? ‹‹ኢቲቪ ሐሳቤን ቆራርጦ በ‹‹አበረታች›› ሊተካው ስለሚችል ፌስቡክ ላይ ለጥፈዋለሁ፤›› ስለው አንገቱን እየወዘወዘ ሳቀብኝ፡፡ ወደ ስራችን ስናመራ፣ ‹‹ሹመት ካልሠሩበት ምን ይፈይዳል?›› ስለው፣ ‹‹ምንም! ነገር ግን ያስተዛዝባል፤›› አለኝ፡፡ ሹመት ችግር ካልፈታ ፋይዳቢስነቱ ገዝፎ ታየኝ፡፡ 
                                                  ከሰብኣዊ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያ መንግሥትን የእንነጋገር ፍላጎት ውድቅ አደረጉ


የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያቀረበውን የመነጋገር ፍላጎት እንደማይቀበሉ አሳወቁ፡፡
በአሜሪካ የተቀነባበረ ያሉትን በአገራቸው ላይ የተጣለውን የጦር መሣሪያ ዝውውር ማዕቀብም የኤርትራውያንን አንድነት የበለጠ እንዲጠናከር ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ይህንን የተናገሩት የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት አስመልክተው ሰሞኑን ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ነው፡፡ መንግሥታቸው በአገሪቱ አመጣው ያሉትን ከፍተኛ ልማትና አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባዊያን አገራቸውን ለማዳከም ያደረጉትን ጥረት እንዴት እንደተቋቋሙት በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ 

Wednesday, January 2, 2013

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ እንድትፈታ ሁለት ታዋቂ የሲኤንኤን እና ኤቢሲ ጋዜጠኞች እንድትፈታ ጥሪ አቀረቡ


Ethiopian journalist's last chance for freedom

by Christiane Amanpour and Cynthia McFadden 



A few weeks ago, we had the honor of hosting the 2012 Courage in Journalism Award for the International Women's Media Foundation. It was a moving, even glittering event. But there was one striking absence. Journalist Reeyot Alemu could not come to New York to receive her award because she is languishing in an Ethiopian prison. On January 4th, an Ethiopian court will decide Alemu’s final appeal. It is her last hope of freedom.

Tuesday, January 1, 2013

ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አወዛጋቢ መልሶችን ሰጡ


ታህሳስ  ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት መልስ በርካታ አወዛጋቢ ነገሮችን ተናግረዋል።
በኤርትራ ዙሪያ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለምልልሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተተቹት አቶ ሀይለማርያም በዛሬው ንግግራቸው በተተቹበት ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። አቶ ሀይለማርያም ” አስመራ እሄዳለሁ ያልኩት በየትኛውም ቦታ እንደራደራለን የሚለውን የመንግስት አቋም አጽንኦት ለመስጠት ነበር” ሲሉ  ተናግረዋል።

እንጠንቀቅ ! እየተበላላን እንዳንጠፋፋ፡፡

ዘረኝነት በወለደው ጦስ በአሜሪካ በነጮች መንደር ጥቁሮች ማለፍ እንኳ አይችሉም ነበር፡፡ የነጮች ምግብ ቤትና የጥቁሮች ምግብ ቤት እንዲሁም ትምህርት ቤት እስከ ቅርብ ዓመታት የተለያዩ ነበሩ፡፡ በዘረኝነት ናዚዎች ከስድስት ሚሊየን በላይ አይሁዳውያንን ጨፍጭፈዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች በውሾች ሳይቀር ተበልተዋል፡፡ በሴራሊዮን የአንድ ወር ሕፃናት አድገው ይዋጉናል ተብሎ እጃቸው ተቆርጧል፡፡ በአገራችንም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘረኝነት በወለደው ጦስ በክልሎች አሰቃቂ ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡ 
አንድ ሰው ሲናገር፣ ‹‹በሰሜን ያለ የአንበሳ መንጋ ወደ ደቡብ ቢሄድ፣ በደቡብ ያለው የአንበሳ መንጋ አንተ ከሰሜን ነህ፣ እኔ ከደቡብ ነኝና አልፈልግህም አይለውም፡፡ ሰው ግን ሰሜንና ደቡብ እያለ ይጠፋፋል፤›› ብሏል፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ ሁሉንም በየወገኑ ፈጥሮታል፡፡ የአንበሳ ወገን አንበሳ ነው፣ ስለዚህ በመንጋ ይጓዛል፡፡ የወፍ ወገንም ወፍ ነው፣ ስለዚህ በአንድነት ይበራሉ፡፡ የሰው ወገንም ሰው ነው፣ ስለዚህ በኅብረት መኖር ይገባዋል፡፡ የሰው ልጅ ግን አራዊትና አእዋፋት ያከበሩትን የተፈጥሮ ሕግ እየጣሰ በኅብረት መኖር አቅቶታል፡፡ የምዕራቡ ሰው ከምሥራቁ ሰው የዓይን አቀማመጡና የአፍንጫ ስፍራው አንድ ዓይነት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየን ሁላችንንም አንድ እጅ እንደ ፈጠረን ነው፡፡ አንድ እጅ አበጅቶን መከፋፋት፣ አንድ አባት ሳለን መለያየት አይገባም፡፡