Wednesday, April 3, 2013

የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ


የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ፣ በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫው ላይ እንዳሰፈረው ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አውስቱአል፣  የግንቦት ሰባት ንቅናቄ    በዚሁ መግለጫ ማጠቃለያው ላይ በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በማነጣጠር እየተፈጸመ ያለው የማፈናቀልና  የማጥቃት እርምጃ በአገሪቱም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ሁሉ  በዘረኝነት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ  በደል ነው ብሎአል።
የፕሮግራማችን ተከታታዮች የዚህን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዜናው በማስከተል የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ይህ በንዲህ እንዳለ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባደሩ ሆድ አደር ባለስልጣናት አሁንም ግፍና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አመለከተ። የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከባህር ዳር ባስተላለፈልን በዚሁ ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው እነኝህ ተፈናቃዮች እያቀረቡ ላለው ጥያቄ  የክልል ባለስልጣናት ተብየዎች ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡአቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውንና ከዚህም አልፎ ከህዝብ እይታ ለመሰወር በሚል ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን  ገለጹአል።

በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥራት ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ምሁር ገለጹ


መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት በሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአቃቢህግነት በመምራት  የሚታወቁት የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት ከዚህ ቀደም በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ፣ አሁን ደግሞ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ የሚችል ዘር ማጥራት ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል።ምሁሩ እንዳሉት ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ባይሆን እንኳ የዘር ማጥራት ወንጀል በመሆኑ በይርጋ የማይታገድ በማንኛውም ጊዜ በአለማቀፍም በኢትዮጵያም ህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ቆም ብለው ሊያስቡበት እንደሚገባ መክረዋል። በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተጨባጭ ማስረጃዎችን በመያዝ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቢያቀርቡት ድርጊቱን የፈጸሙትን ለህግ ማቅርብ እንደሚቻልም ዶ/ር ያእቆብ ገልጸዋልየቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለስልጣናት ቀደም ብሎ ደግሞ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሰዎቹ የሚባረሩት አማራ ስለሆኑ ሳይሆን ደን ስለሚጨፈጭፉ ነው በማለት የተሰጠው ምክንያት ተገቢ አለመሆኑን የገለጡት ዶ/ር ያእቆብ ፣ ደን የጨፈጨፉ ካሉ በህግ ይጠየቃሉ እንጅ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ሊባሉ አይገባም ብለዋል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይህን ድርጊት ማውገዝ እንደሚገባውም ምሁሩ ገልጸዋል ።ሁሉም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆናቸውን የገለጡት ምሁሩ፣ በመንግስት በኩል የሚቀርበው መከራከሪያ ፈጽሞ ተቀባይነት የለም ሲሉ በአጽኖት ገልጸዋል።ዶ/ር ያእቆብ ድርጊቱ ስሜታቸውን እንደጎዳው አልሸሸጉም።በተመሳሳይ ዜና ደግሞ በማህበራዊ ድረገጾች ጽሁፎችን በመጻፍ የሚታወቁት መምህር አብረሀ ደስታ ” የአማራ ተፈናቃዮች በህወሀት ተግባር ምክንያት በትግራይ ህዝብ ቅር ሊሰኙ ይችላሉ። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ዛሬ በአማራ ህዝብ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ነገ በትግራይ ህዝብ መደረጉ አይቀርም። ግለሰቦች በስልጣን ለማቆየት ሲባል በሰለማዊ ንጹህ ዜጎች ግፍ እየተፈጸመ ዝም ብሎ መመልከት ተገቢ አይደለም።” ካለ በሁዋላ ፣ ይህ የማፈናቀሉ ተግባር ካልቆመ መጨረሻው ምን ሊሆን ነው? ስለሌሎች ስናስብ ስለራሳችን እአሰብን ነው።” ብለዋል

ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!!
ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ 
በተደጋጋሚ ፓርቲያችን እንደሚገልፀው አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣ ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡
ያ ለዘመናት አብሮን የቆየው በጋራ የመኖር ዕሴት እየተደመሰሰ በምትኩ የሚያጋጩ ስልቶች እየተፈጠሩና እየተተገበሩ ወደ ሰቆቃ ተለውጠው ይገኛሉ፡፡ የዜጎች ሰዋዊና ህጋዊ መብት እየተጣሰም ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ አብሮ የመኖር፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና በፈለጉት ቦታ ሃብት የማፍራት ህልውና እያከተመ መጥቷል፡፡ ለዚህ ክፉ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆነው ደግሞ የዜጎችን መዘዋወር መብትና ሃብት የማፍራት መብት ማረጋገጥ የተሳነው መንግስትና መንግስት ብቻ ነው፡፡

Tuesday, April 2, 2013

In Aid to Ethiopia, a Costly Trade-Off

April 1, 2013
written by

Chloe Schwenke
Vice President of Global Programs
A Community consultation on a draft peace accord in Hudet, Somali Region, Ethiopia.
Photo Credit: Mercy Corps

The dividing line between developmental assistance and aid that is intended to strengthen human rights and democratic governance is an obscure boundary, yet it has considerable moral and strategic significance. Donor countries must weigh a variety of factors—including security and economic questions and the geopolitical role of the beneficiary country—that often leave democracy and human rights goals on the back burner. Such a ranking of priorities has an immediate negative effect on the ground, and it ultimately represents a costly trade-off in which long-term interests are exchanged for short-term gains.

By any plausible account, the performance of Ethiopia’s current government raises daunting dilemmas of this kind. International donors have generally responded by emphasizing economic growth and all but ignoring the erosion of human rights. It is an approach that flies in the face of American values and of current U.S. policy for sub-Saharan Africa, which explicitly promotes the creation of democratic and just societies.

‹‹ርዕዮት የአቋም ለውጥ ታደርጋለች ብላችሁ ስጋት አይግባችሁ››


‹‹ርዕዮት የአቋም ለውጥ ታደርጋለች ብላችሁ ስጋት አይግባችሁ››
ሁለተኛ ዲግሪዋን ለመማር የምትገኝበትን የማረሚያ ቤት አስተዳደር በመጠየቅ ይሁንታ በማግኘቷ 16.000 ብር በመክፈል የተመዘገበችው ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት አለሙ ባልተጻፈ ህግ ትምህርቱን እንዳትከታተልና ከትምህርት ቤቱ የተላኩላት የመማሪያ መጻህፍት እንዳይገቡላት ተደርጋለች፡፡ይሁንና ርዕዮትና ቤተሰቦቿ ጉዳዮን ለሚዲያ ሳይገልጹ ቆይተዋል፡፡ርዕዮት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደርሱባትን ኢሰብአዊ ድርጊቶች ቤተሰቦቿን ጭንቀት ውስጥ ላለመክተት በማሰብ ተቋቁማ አልፋለች፡፡

የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት? “ከእንግዲህ የቀድሞው መንገድ አይሰራም”


ላለፉት አርባ ዓመታት ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ሲታገል የቆየው ኦነግ አመራሮቹ ሲጣሉና ሲታረቁ መስማት የተለመደ ነው። የግለሰብ ጸብ የሚመስለው የድርጅት በሽታ ሲንጠው የቆየው ኦነግ በውል ባይታወቅም ተሰነጣጥቆ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ድርጅት ከሆነም ዓመታት ተቆጥረዋል። ስህተትን ገምግሞ የትግል አቅጣጫና ፕሮግራም ከመቀየር ይልቅ ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ ባለበት ሲረግጥ እድሜውን የፈጀ ድርጅት እንደሆነ ተደርጎም ይወሰዳል።
ስለ ኦነግ ሲነሳ አብዛኞች በመገረም የሚናገሩትና ሚዛን የሚደፋው አስተያየት የሚሰነዘረው በድርጅቱ መከፋፈልና መበጣጠስ ሳይሆን ተለያይተውም አስመራን የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ህጻን እያለ ሻዕቢያ እንዳሻው ይነዳው እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች ከሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ኦነግ አገር ለቆ እንዲወጣ መንገዱን የጠረገው ሻዕቢያ መሆኑንን በቁጭት ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ለስልጣን አዲስ በሆነበት የጨቅላነት ዘመኑ፣ ኦነግ በታሪኩ ያልነበረውን ሰራዊት በመገንባት አስጨንቆት እንደነበር በመጠቆም በወቅቱ አስተያየት የሰጡ ኢህአዴግ በተለይም መለስ በሻዕቢያ በኩል ኦነግን ለመታረቅ አቅርበውት የነበረውን የሽምግልና ጥያቄ ኦነግ እንዳይቀበል ሰሚ ባያገኙም በአጽዕኖት ምክራቸውን ሰጥተው ነበር።
በኦነግ ታጣቂ ሃይሎችና በኢህአዴግ ሰራዊት መካከል እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የጡንቻ  መፈታተን ነበር። ደርግ ሲበታተን ኦነግን የተቀላቀሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አካላት ወያኔን የማዳፋት አቅሙ ነበራቸው። በወቅቱ የንስር ያህል ጉልበትና ሃይል ቢኖራቸውም ራሳቸውን ጫጩት አድርገው ተመለከቱ። አዲስ አበባ ሲገቡ የነበራቸውን የህዝብ ድጋፍ አራግፈው ጣሉት። በስሜት እየተነዱ ከሚወዷቸው ሁሉ ተቀያየሙ። ህወሃት አጋጣሚውን ለቅስቀሳና ለስም ማቆሸሻ ሰራበት። በስተመጨረሻ ኦነግ ሃይሉንና አቅሙን ዘንግቶ በአመራር ችግርና በአቋም ሸውራራነት ሃይሉን በሙሉ ወደ ካምፕ በማስገባት የኢህአዴግን የእርቅ ጥያቄ ተቀበለ። ሰራዊቱን እየነዳ በፈቃደኛት አሳሰራቸው።
በሻዕቢያ አደራዳሪነት ሁርሶ፣ ደዴሳና መስኖ የገባው ሰራዊት “በደባ” ተከቦ ትጥቁን እንዲፈታ ተደረገ። አብጦ የነበረው የኦነግ ጡንቻ በቅጽበት ከሰመ፤ ሰለለ። ኦነግ ሲቆጣጠራቸው የነበሩትን ቦታዎች ለማስተዳደርና በኦህዴድ ለመተካት ኢህአዴግ እንደ እባብ ተሹለክልኮ ዓላማውን አሳካ። ሻዕቢያም በዚሁ ውለታው ኢትዮጵያንና ኢኮኖሚዋን ብሎም የኢትዮጵያን ስነልቦና እንዳሻው እንዲጋልብ ተፈቀደለት። ብዙ አሻጥር ተፈጠረ፤ ተፈጸመም። ደንዳና ቆዳ ያላት ኢትዮጵያና ህዝቧ ተቦጠቦጡ። ተዘረፉ። አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ኤርትራ ቡና ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተሰለፈች። አፈርን።

Monday, April 1, 2013

ለ አቶ አዲሱ ለገሰ የቀረበ የህልውና ጥያቄ ? ? ?


ለመሆኑ እርስዎ አማራ ነኝ ይላሉ ከዚያም አምራውን ወክለው ለ20 ዓመታት ፀረ-አማራ ፀረ- ኢትዮጵያ አገዛዝ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘው ይገኛሉ እናም የሕውሀት መሥራቾች እንደሚሉን ከቅድመ ደርግ በፊት የነበረውን የመላ የኢትዮጵያውያንን ተማሪዎች ንቅናቄ ፀረ ፊዳሊዝም ሣይሆን ለትግራይ ሕዝብ የበላይነት የነበረ ነው ይሉናል እርስዎም የታገሉለት ለዚሁ ነበር ?
እርስዎ የተወለዱት በሓረር ሁኖ ሳለ ግን እርስዎ ለምርጫ ለመወዳደር የምረጡት በበለሳ ወረዳ ዙይ-ዝሀየ አካባቢ ቆላ ሐሙሲት ነው ምክንያትዎ ግልጽ ነበር ?
ለምን ባማራው ክልል እንዲሆን ተደረገ ወይስ ባማራው ክልል ታማኝ ሎሌ የሚሆን ስለጠፋ ይሆን ?
ውድ የነፃ አውጭ አባት ነወትና ከርስዎ እውነት አይጠፋምና መልሱን በጉጉት እጠብቃለሁ