Monday, February 17, 2014

አቡጊዳ – የዶር ያእቆብ «አሰብ የማን ናት?» መጽሃፍ ሰባት ጊዜ እንደታተመ ተገለጸ

ዶር ያእቆብ ኃይለማሪያም፣ የአሰብ ወደብን በተመለከተ የጻፉት መጽሃፍ ሰባት ጊዜ እንደታተመ ከሲ.ቢ.ኤስ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ። «ይህ የሚያመለክተዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል የአሰብ ጉዳይ እንደሚያንገበግበው ነዉ» ያሉት ዶር ያእቆብ፣ በአሰብ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በስላም መፍታት እንደሚቻልም ለማሳየት ሞክረዋል።
የኤርትራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድማማች ህዝብ እንደሆኑ የተናገሩት ዶር ያእቆብ፣ ጠቡና መለያየቱ የመጣዉ በመሪዎች ችግር ብቻ እንደሆነ ይገልጻሉ። «ተለያየትን አንቀርም። አንድ ቀን ተመልሰን አንድ መሆናችህ አይቀርም» ያሉት ዶር ያእቆብ ፣ የአሰብ ጉዳይ በሰላም የሚፈታበትንም አራት አማራጮችን አቅርበዋል።

የፈረደበትስ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ግንቦት 7 እና የኤርትራ መንግስት አይደሉም! (ለአቶ ተክለሚካሄል አበበ፤ ጥያቄዎች ምላሽ ቢሆን) ያሬድ ኃይለማርያም

በመጀመሪያ በአቅርቡ በተከታታይ ለአንባቢያን ያቀረብኩዋቸውን ሁለት ጽሁፎች አንብበህና ጊዜህንም ወስደህ በዝርዝር ላቀረብከው የሙግት ሃሳብ ምስጋናዮ የላቀ ነው። ለነገሩ የጽሑፌም ዋና አላማ ጉዳዩን ሕዝብ እንዲያውቀው ብቻ ሳይሆን በተነሱት ነጥቦችም ዙሪያ በአንባቢዎች ዘንድ የውይይት ሃሳብንም በማጫር ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝም ጭምር ስለሆነ ያንተ ምላሽ እኔንም በዚሁ ጉዳይ ላይ በድጋሚ እንድመለስበት አድርጎኛል። ምንም እንኳን ባነሳሃቸው በርካታ ሃሳቦች ፍጹም የተለያየ አቋም ያለን ቢሆንም ከእንዲህ አይነቱ የውይይትና ሃሳብን ሥልጡን በሆነ መልኩ የማንሸራሸር ልምድ ከየኮምፒቱሩ ጀርባ ተደብቀው በፈረስ ስማቸው መረን የለቀቀ እና ድንቁርና የታከለበትን ስድባቸውን ለሚወረውሩት የሳይበር አርበኞች ትምህርት ሊሆን ይችላል ብዮ አምናለሁ፡፡ አንዳንዶቹ ከእኔም አልፈው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጭምር ጸያፍ በሆነ መልኩ ለመዝለፍና ለማንቋሸሽ ሞክረዋል።

“ከኛም ቤት እሣት አለ !!” (ይፍሩ ኃይሉ )

“ለወደቀ ዛፍ ምሣር ይበዛብታል” እንደሚሉ ሆኖ ነው መሰል አገራችንን እትዮጵያንና ሕዝቧን ከያቅጣጫው የገጠማቸው ችግር ከመቼውም የበለጠ የሚያስደነግጥና፤ ሊታመንም በማቻልበት ሁኔታ በጆሮ ለመስማት እንኳ የሚቀፍና የሚዘገንን ነው። በአባቶቻቸን፤ በአያቶቻችንና በቅድመ አያቶቻቸን ደም ፍሳሽና አጥንት ክስካሽ ተፈርቶና ተከብሮ የነበረው ዳር ድንበሯ ዛሬ “የምትፈግ ገብተህ እግርህን ዘርግተህ ተዝናንተህ ፈንጪበት፤ ሁሉም በጅህ ሁሉም በደጅህ ይሁንል” የተባለ ይመስላል። የቤልጅየምን የቆዳ ስፋት የሚበልጥ ለም የኢትጵያ መሬት፤ ከግማሽ ጎንደር እስከ ጋንቤላ ድረስ ለሱዳን መንግሥት በገጸበከትነት ከመሰጠቱም በላይ እንደገና በዚሁ ባልታደለ አካባቢ የሚገኝ ለም መሬት፤ ከነዋሪው አርሶ አደርና አርብቶ አደር ሕዝብ፤ ያለ ፈቃዱና፤ለተነጠቀው ንብረቱና ሃብቱ ያለምንም የዋጋ ክፍያ፤ ለዘመናት ከኖረብት ከአያት ቅድ መአያቱ ቀዬ እየተፈናቅለ፤ በሱ ቦታ ዛሬ በአንድ ጀንበር ለተፈለፍሉ የወያኔ ቱጃሮችና፤ ለአረብ፤ለሕንድና ለሌሎች የውጪ አገር ባለሃብቶች እጅግ በሚገርምና በማይታመን ዝቅ ባለ ዋጋ እየተቸረቸረ ይግኛል።

የህወሓት ሰማዕታት አጭር ማስታወሻ (ናይ ህወሓት ሰማአታት ሐፂር መዘካከሪ)

1
ሰላሳ ዘጠኝ ዓመታት ወደኋላ…
“የአብዮቱ ደወል እየተደወለ ነው
ሕዝቦች ሆይ ተነሱ
ስለመብቶቻችሁም ቁሙ
ጠመንጃችሁን አንሱ
ጨቋኞቻችሁንም ታገሉ”
ይህ የመጀመሪያው የህወሓት መዝሙር ለ16 ዓመታት ያህል በሺ በሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች አንደበት በሰሜን ኢትዮጵያ ተራራና ሸለቆዎች መካከል ተዘምሯል፡፡ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓመተ ምህረትም እፍኝ የማይሞሉ ወጣቶች ማንም ቢሆን ‹ያደርጉታል› ብሎ ያላሰበውን ረዥሙን የትግል ምዕራፍ አንድ ብለው የጀመሩበት ዕለት መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ርግጥ ነው እነዚህ መስራቾች ብዙሃኑን ለትግል ከቀሰቀሱበት አጀንዳ ባሻገር የትግራይ ሕዝብን የማይወክል ድብቅ ፖለቲካዊ ፍላጎት የነበራቸው መንደርተኞች ስለመሆናቸው ‹‹ከትግራይ ሪፐብሊክ›› እስከ ‹‹ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም›› ድረስ የተሻሻሉ ፕሮግራሞቻቸውን ጨምሮ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

Thursday, February 13, 2014

ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
logopresentation
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤  እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ቀላሉ ዘዴ መሰንከል ነው፡፡

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ! (በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት)

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

የጤፍ ምርትን ለውጭ ገበያ፣ ይቁም ሊባል የሚገባ!

አሰግድ ኣረጋ (ኮለምበስ – ኦሃዮ)
ሰሞኑን ስለጤፍ ምርታችን የባዕዳኑ ብዙሃን መገናኛ አጀብ እያሉን ነው፤ ለዘመናት የተደበቀው የዘሩ ገመና መጋለጡን እየነገሩን ነው፤ ስለያዘው ንጥረ ነገር፣ ስለጤናማነቱ፣ በምዕራቡ ገበያ ስለመፈለጉ፣ ከሁለም በላይ ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭነቱ። ምግብነቱ ተትረፍርፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ማስቀመጫ – ቦታ ያጣ ይመስል፣ የወንዙ ልጆች ጭምር ፣ ጤፍ-የጤፍ ዘር፣ እንጀራ ፣ ብሰኩት፣ ኬክ ሆኖ ምግብ በዝቶበት ለሚቀናጣው ለውጭ ገበያ እንዲነጉድ ከምዕራባውያኑ ጋር አብረን ከበሮ እየደለቅን ነው፤ አደብ ልንገዛ ይገባል።