Thursday, March 21, 2013

የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሳዑዲ አረቢያ ሚዲያዎችን ሊከስ ነው


በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ‹‹የዜጎቼ ሰብአዊ ክብር ተደፍሯል›› ሲል የሳውዲ ሚዲያዎችንና አንዳንድ ግለሰቦችን ሊከስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ የሚፈፀሙ ማናቸውም በመሳሪያ የታገዙ የዘረፋዎች፣ የውንብድናና የማጭበርበር ድርጊቶች ‹‹ኢትዮጵያውያን ፈፀሙት›› እያሉ ማውራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ከመሆኑ በተጨማሪ በአገሪቱ የተለያዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና በሌሎች ጋዜጦች ላይ ይህንኑ ስሜት ማንፀበረቅ እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደሌባና አጭበርባሪ እየታየ መሆኑንና ዜጎችም ስራ ለመቀጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየገጠማቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Wednesday, March 20, 2013


የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን ካለፈው ታኅሳስ 6 እስከ 10 የሃይማኖት ነፃነትን ሁኔታ ለመገምገም በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጎ የጉብኝቱን ውጤት የያዘ ዘገባ ይፋ አድርጓል።
ባለፈው ሰኞ መጋቢት 2 የወጣው ይህ ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት የሃይማኖት አክራሪነት ሥጋት ቢኖርበትም በነፃነት ማምለክንና ሌሎችም መሠረታዊ መብቶችን ማፈኑ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ሊያባብስ ይችላል የሚል ሃሳብ ያቀርባል።
ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና በዋልታ የመረጃ ማዕከል ይፋ የሆነ አንድ የሕዝብ ሃሳብ መለኪያ ጥናትም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት አክራሪነት እንደሚሰተዋል በመግለፅ ማሳሰቢያ አውጥቷል።

ኢትዮጵያና የግለሰቦች ስለላ በኢንተርኔት - ጥናት፣ ክስና ምላሽ


​​​​የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ማልዌር እየተጠቀመ በተቃዋሚዎች ላይ ስለላ ያካሂዳል ሲሉ በካናዳው ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲና በዩናይትድ ስቴትሱ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለዶክትሬት ዲግሪ የሚዘጋጁት ዊልያም ማርዣክ እና ሞርጋን ማርኪስ-ቧር ያወጧቸው የክትትል ሪፖርቶች ለሕትመት በቅተዋል፡፡

Tuesday, March 19, 2013

ኢትዮጵያ የጀርመን ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት

የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚቴና በጀርመንኛው «ፔን ሴንትሩም ዶይችላንድ» ተቋም የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ስለሠብዓዊ መብትና ስለመናገር ነፃነት መገደብ በይፋ እንዲናገሩ በደብዳቤ ጠየቁ። በጀርመን ምክር ቤት የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እንደራሴና በምክር ቤት የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ም/ሊቀመንበርም ተመሳሳይ ነጥብ አንስተዋል።
እጅግ የተከበሩ የጀርመን ፕሬዚዳንት፤ ስለነፃነት መጠየቁ ተሸላሚው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ሀገርን በከፍተኛ ሁኔታ መክዳትና ሽብርተኝነት በሚል ለ18 ዓመታት እስር ዳርጎታል ይላል ይፋዊው ደብዳቤ ሲንደረደር። ደብዳቤውን ለጀርመኑ ፕሬዚዳንት ጽፈው ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚቴና በጀርመንኛው «ፔን ሴንትሩም ዶይችላንድ» የተሰኘው ተቋም በአንድነት ነው። የተቋሙ ምክትል ፕሬዚዳንትና በእስር ቤት ለሚገኙ ፀሀፊዎች የሚሟገተው ተቋም ሃላፊ ዛሻ ፎይሸርት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮኣሒም ጋውክ በኢትዮጵያ ጉዟቸው ወቅት ግልፅና ይፋ በሆነ መልኩ ሊያስተላልፉት የሚገባ መልዕክት አለ ይላሉ።

Monday, March 18, 2013

Ethiopia: Journalism under anti-terrorism law


Ethiopia: Journalism under anti-terrorism law

How the US 'war on terror' has provided cover for laws that are being used to silence dissident journalists.
When the Paris-based media watchdog group, Reporters Without Borders released its annual Press Freedom Index, 
few were surprised that Ethiopia had dropped 11 places to 137.
Journalists in the country have never truly been free to report however developments in the region over the last few years have had a detrimental effect on the media environment.
With the disputed 2005 general election, the continued conflict with separatist groups and the spectre of the Arab Spring arriving in the country – the government in Addis Abba has been cracking down on the media
And one of its most effective tools is a vague, far reaching anti-terrorism law that has sentenced at least 11 journalists to harsh prison terms.

Sunday, March 17, 2013

መንግስት በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ነው። መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ!

 ድርጅቱ  ( በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው። በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ) ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው  አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን የወያኔ ካድሬዎች አዲስ አበባን ምሮ  በሁሉም ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱ እና እየፈረሱ ካሉ ቤቶች አብዛኞቹ የአማራ ተናጋሪዎች መኖሪያ መሆናቸውን መታዘቡንገልጿል።

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ
የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!
ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡