Saturday, May 31, 2014

ዓባይ እንደዋዛ፤ ግድቡን ከጥላቻ አንጻር ማየት አደገኛ ነው (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ክፍል አራት)

አክሎግ ቢራራ ዶ/ር (ክፍል አራት)

Click here for PDF

የዚህ ተከታታይ ፅሁፍ መሰረታዊ ሃሳብና ትንተና፤ ኢትዮጵያ ዓባይንና ሌሎች ወንዞቿን የራሷን ኢኪኖሚ ዘመናዊነት፤ ለሕዝቧ የምግብ ዋስትና ስኬታማነት፤ እያደገ ለሄደው ወጣት ትውልድ የስራ እድል የመፍጠር ወዘተ መብት ያላት መሆኑን የሚያጠናክር ነው። The Nile is African and Ethiopia is its hub በሚል አርእስት ለአለጀዚራ ያቀረብኩት ፅሁፍ ይኼን ይገባኛልነት በማስረጃ ተደግፎ ያሳያል። በአረብኛ የተተረጎመው ትንተና የብዙ አንባቢዎችን አስተሳሰብ እንደቀሰቀሰ ሰምቻለሁ፤ አሉታዊና ነቀፋ ያለበት ትችት አልደረሰኝም። የኢትዮጵያን ይገባኛልነት ሌሎች የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች እንደሚደግፉም አሳይቻለሁ።

ኢትዮጵያ እውነተኛ ልጇን አጣች

በልጅግ ዓሊ – ፍራንክፈርት

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል።Karlheinz Böhm1
ይህንን ታላቅ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኢሊባቡር ውስጥ ጉመሮ ሻይ ተክል መጥቶ በነበረበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት የተነገረን የፊልም ተዋንያን መሆኑን ብቻ ነበር። ጀርመን ከመጣሁበት ቀን ጀምሮ ስለዚህ ሰው ደግነት በሰፊው ልረዳ ችያለሁ።
ካርልሃይንዝ በተወለደ በ86 ዓመቱ ያለፈው ሐሙስ ሌሊት ሳልዝቡርግ – አውስትሪያ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለውጥን ፈልገን ለውጥንም ፈርተን በጭራሽ አናመጣውም

ዳዊት ዳባ
የለውጥ አስፈላጊነት ላይና ወያኔ መራሹ መንግስት ይበቃው ዘንድ ባብዛኛው ዜጋ ከተቻለ የሚለው እንዳለ ብዥታ የለም። ይህ ፍላጎት የብዙ ስረአቱ ውስጥ ያሉ ዜጎችም ጭምር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎችን ጨምቆ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። በርግጥ የለውጡ አስፈላጊነት ላይ የሚስማሙና አይቀሬነቱን የሚያውቁ ነገር ግን ለውጡ የተረጋጋና ችግሮች ያልበዙበት እንዲሆን ይረዳል ብለው አገዛዙ ድርሻ በሚያደርግበት እንዲከወን የሚመኙ አሉ። ፈራ ተባ እያሉ ሀሳቡን አንዳንዴ ያነሱታል። ይህ ሀሳብ ክፋት ባይኖረውም ጥሩ ምኞት ብቻ ነው የሆነው። በትንሹ እንኳ ተቀባይነት እንዲያገኝ አይደለም እንዲሰማ ለማድረግ አገዛዙ ጉልብት አልሰጠው እያለ ብለጭ ድርግም ይላል።

Thursday, May 29, 2014

ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን

ከሮበሌ አባቢያ
በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን ላይ የተኮፈሰው የወያኔ መንግሥት አገልጋዮቹ ለፈፀሙት ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ወንጀሉን በመሸፋፈን የሕዝብ ትኩረት ወደ እርሱ ሙገሳ እንዲዞር እነሆ 23ኛውን የወረራ በዓሉን ሲያከብር በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን ተብሎ መዘከሩ አይቀርም።

የቅድመ ምርጫ አፈናው በውይይት እንዲተካ እንጠይቃለን!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

እንደሚታወቀው የግንቦት 2ዐን 23ኛ ዓመት ለማክበር ጉድ ጉድ እያለ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ወደ ጠቅላይ አምባገነን ፓርቲነት ከተለወጠ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው በፊት በርካቶች ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን ክቡር ህይወታቸውን እንዲገብሩ ተደርጎ በተገኘ የዜጎቻችን መስዋእትነት መንበረ ሥልጣኑን ቢጨብጡም በተግባር ዋጋ የተከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት አልቻሉም፡፡ እንዲሁም የህዝቦችን ነፃነት በጉልበት በመቀማት፣ ሰብአዊ መብትን በመጋፋት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለማስመሰያነት በንድፈ ሃሳብ አስፍረው በተግባር በዜጎችዋ ግፍ በመፈፀም ነፃነውን ፕሬስ እንደጠላት በማየት፣ ተቀናቃኝ ኃይሎችንና የፖለቲካ መሪዎችን በማሰርና በማፈን፤ በነፃነት የመደራጀት መብትን በመጨፍለቅ በአጠቃላይ ፍፁም አምባገነን የሆነ ስርዓት በመዘርጋት ላይ ነው፡፡

ውሸት ሲደጋገም ዕውነት እንዳይመስል፣ ስንናገርም ሆነ ስንጽፍ ልንጠነቀቅ ይገባል!

ተክሌ የሻው
ዛሬ ከአገራችን አውራ ችግሮች መካከል ዋናው፣ የተደጋገሙ ውሸቶች ዕውነት የመሰሏቸው ቡድኖች የሚያጎኑት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ የዘር ፖለቲካ እና አንድን ነገድ፣ በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለሚባሉ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርገው ነው ብዬ አምናለሁ። አይደለም የሚለኝ ከመጣም የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ። የተደጋገሙ ውሸቶች ሀውልት ሲያስቆሙ እያዬን ነው። የአኖሌን ሀውልት ለአብነት መመልከት ነው። የከተሞችን ስም ሲያስለውጥ እያዬን ነው። አዲስ አበባን ፊንፊኔ፣ ናዝሬትን አዳማ፣ ደብረዘይትን ቢሸፍቱ፣ አዋሣን ሀዋሣ፣ ዝዋይን —ሌላ ሌም አለ። ወደ ኋላ እንይ ከተባለ ወለጋ፣ ቢዛምን፣ ኢሉባቡር እናርያ፣ አርሲ ፈጠጋር፣ ወሎ ላኮመልዛ ወዘተ ማለት ይቻላል። ይህ ግን አይጠቅምም። የኋሊት ጉዞ ያስከትላል። ይህ ደግሞ ወደ አንጋዳ በራስ ኃይል መውደቅን ያመጣል። ይህ ሁሉ የሆነው ውሸት በመደጋገሙ ነው።

Tuesday, May 27, 2014

አቶ ስብሃት ነጋ – የእንደራደር ጥያቄዎን በታማኒ ተግባር ይጀምሩት!

ከአቢቹ ነጋ
ከዚህ በፊት የግንቦት ሰባት ድርጅት የንደራደር ጥያቄ ከኢትዮጵይ መንግሥት አንደደረሰው በአፅኖት አውርቶናል። ብዙ ሕዝብ የግንቦት ሰባትን ዜና በማድቤት የተፈበረከ እራስን የመካቢያ ወሬ አድርጎት አንደነበር አይዘነጋም። እኔ ግን ዜናውን አንደወረድ መቀበል ብቻ ሳይሆን ደስተኛም ነበርሁ። ኢትዮጵያን አግዚአብሔር አንደሚጠብቃትም ያመንሁበት ወቅት ነበር ማለት ይቻላል። የዋህ ላገር ቅን አሳቢ ስለሆንህ እንጅ ከእባብ የርግብ አንቁላል እንዴት ትጠብቃለህ ብባልም የባብ መርዝም መዳህኒት ሊሆን እንደሚችል ይታወቅ ብያለሁ።TPLF power broker, Sibehat Nega
ከሁልም ያስደስተኝ ግን ግንቦት ሰባት ጥያቄውን በሕዝባዊ መግለጫው ያስተናገደበት ዘዴ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ድርጅቱ በኢሃዴግ ተጠይቆ ከሆነ ጉዳዩን በምስጢር ይዞ ማካሄድ ነበረበት ብለዋል።