Friday, June 27, 2014

በፍረጃና በጥላቻ የተዋጡ 23 ዓመታት

ጌታቸው አምሳሉ በሶሻል ሚዲያ በተለይ ደግሞ በፌስቡክ ስሙን እየቀያየረ የሚጽፍ ወጣት ነው፡፡
በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰጣቸው አስተያየቶች ተመሳሳይ ቢሆኑም በተለያዩ የአማርኛ፣ የኦሮሚኛና የትግርኛ የሚመስሉ የብዕር ስሞች ይጽፋቸዋል፡፡ ስሞቹን ለመናገር ግን ፈቃደኛ አይደለም፡፡ 
ከሦስቱም ብሔሮች ስሞችን ይወስዳል፡፡ ብዙም አበላልጦ አያያቸውም፡፡ በተለያዩ ስሞች ለሚሰጣቸው አስተያየቶች የሚቀርቡለት ትችቶችና ነቀፌታዎች ግን የተጠቀመውንም ስም መሠረት ያደረጉ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ በጣም ጥቂቶች ግን በተለያዩ ስሞች እየገባ ለሚሰጣቸው አስተያየቶች የሐሳቡ ቁም ነገር ላይ ብቻ ተመሥርተው አስተያየቶች እንደሚሰጡት ያስረዳል፡፡ ቁጥራቸው እየጨመረ ወይስ እየቀነሰ ስለመምጣቱ ተጠይቆ ነበር፡፡ የፌስቡክ ተጠቃሚ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የፌስቡክ ጓደኞቹም ቁጥር ከፍ ብሏል፡፡ ሐሳባቸውን በምክንያት አስደግፈው የሚጽፉ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም፣ በሚለጥፈው ወይም ፖስት በሚያደርገው ሐሳብ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዙትና እንደልባቸው የሚጽፉት ግን ‹‹ፅንፈኞች›› መሆናቸውን፣ ኃላፊነት እንደማይሰማቸውና አብዛኛዎቹም በውጭ አገር እንደሚኖሩ አረጋግጧል፡፡

ውስጣዊ ጥራታችን በማጠናከር ጠንክረን እንውጣ !!

ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል
መቐለ 

 በአንድ “ዲሞክራሲያዊ ነኝ” የሚል ፖለቲካዊ ፓርቲ ውስጣዊ የአንድነትና የትግል 
ህይወት ከሌለው ውጤቱ ውድቀት ነው። 
 በ60ዎቹ ዓ.ም በሃገራችን ፀረ የተበላሸ ዘውዳዊ ስርአትና ፋሽሽታዊ ደርግን በመቃወም ይታገሉ የነበሩ ወገኖች አወዳደቅ 
ስንመለከት ፤መጀመርያ መደራጀቱ ሲጀምሩት የሃገራችን ሙሁራን፤ተማሪዎች ፤ወዛደሮች ጨቋኝ ስርአቶችን አስወግደው 
ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ፤ወዛደሮች፤ተማሪዎችና ሌሎች ማ/ሰብ 
በመንቀሳቀስና በመደራጀት መልካም የሚባል የኢትዮጵያ አንድነት የሚያንፀባርቅ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ 
 የኋላኋላ ግን ደርግ ሁሉም ነገር የዲሞክራሲያዊ ጥያቄ በመዝጋቱ በአንድነት ይንቀሳቀሱ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፡ 
ሙሁራኖች መሰረታዊ ባልሆነ ልዩነት፡አንዳንዶቹ “የብሄር ጭቆና ጥያቄ መመለስ አለበት” ፡አንዳንዶች ደግሞ “የመደብ ገዢዎች ከተገረሰሱ ሁሉም ነገር አልጋ 
በአልጋ በሆነ መንገድ ይፈታል”፡በማለት ሌሎች ደግሞ “ለደርግ መታገል አያስፈልግም በውስጡ ሁነን ማስተካከል ይቻላል”፡በማለት ከደርግ ታረቁ፡፡

ምኒልክ እና አርሲ

ወርቁ ፈረደ

ኢትዮጵያዊው ቢስማርክ ዳግማዊ ምኒልክ፣ አገር ለማስገበር ካደረጓቸው ዘመቻዎች ውስጥ ትልቅ ምከታ የገጠማቸው አርሲ ላይ ነው፡፡ 
ምኒልክ በአርሲዎች ክንድ ተከታታይ ሽንፈት ከቀመሱ በኋላ፣ በራስ ወልደ ገብርኤልና በራስ ዳርጌ እልክ አስጨራሽ ዘመቻ አማካኝነት፣ አሸንፈው 
አርሲን ወደ ግዛታቸው ቀላቀሉት፡: በጦርነቱ ከአስገባሪውና ከገባሪው ወገን አያሌ ወታደሮች አልቀዋል፡፡ ውጊያው የተካሄደው፣ነፍጥ በታጠቁ የንጉሱ 
ወታደሮችና ከጦርና ጋሻ ፈረስ ውጭ ምንም በሌላቸው የአርሲ ጎበዞች መካከል በመሆኑ፣ ከተከላካዩ ወገን ያለቀው በቁጥር እንደሚልቅ እሙን ነው፡፡ 
የአርሲ ጦርነት ከተካሄደ ከጥቂት አመታት በኋላ፣ ወደ ኦሮሞ ምድር የደረሰው ደ ሳልቪያክ የተባለ የፈረንሳይ ሀዋርያ ከአርሲዎች በሰበሰበው መረጃ 
ተመስርቶ እንደጻፈው፣ ራስ ወልደገብርኤል የአርሲዎችን አይበገሬነት ለመስበር ባንድ ቀን ብቻ የአራት መቶ አንጋፋዎችን ክንድ አስቆርጠዋል፡፡ይህ 
ጻሀፊ፣ ክንዳቸውን ካጡት ትልልቅ ሰዎች ጥቂቶቹን ባይኔ በብረቱ አይቻለሁ ብሏል፡፡ 

Sunday, June 22, 2014

ፖለቲከኞቻችን የእስከዛሬ ሃሳባቸውን “ዲሊት” ያድርጉት!

አዲሱ ንቅናቄ - የምስጋና አብዮት ነው! 

     ለሁሉም ጊዜ አለው ተብሏል… አሁን ጊዜው የምስጋና አብዮት ነው፡፡ የአረቡን ህዝባዊ አመፅ አይተነዋል፡፡ የቀለም አብዮት የተባለውንም በቲቪ መስኮት በእነ ዩክሬን ታዝበነዋል፡፡ እና ምን ቀረን? ሁሉም ተሞክሯል እኮ! ሰላማዊ ሰልፉም፣ የእሪታ ቀኑም፣ ቦይኮት ማድረጉም ወዘተ… ኧረ ምን ያልተሞከረ አለ! 
አሁን በአንድ ነገር እንስማማ፡፡ በድሮው መንገድ እየሰራን አዲስ ውጤት (ለውጥ) መጠበቅ ጅልነት ነው፡፡ አሰራራችንን ሳይቀይር ለውጥ ሊመጣ ጨርሶ አይችልም፡፡ ኢህአዴግ ነፍሴ እንደሚለን፤ “ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው፡፡” (It is a must! ብያችኋለሁ) እናላችሁ.. ዛሬ ስለምስጋና አብዮት እናወራለን፡፡ ምስጋናና አብዮት ምን አገናኛቸው ይሆን? በነገራችሁ ላይ ይሄ ስብከት አይደለም፡፡ እንደ ዕውቀት (መረጃ) ሽግግር ብትመለከቱት ደስ ይለኛል፡፡ የምስጋና አብዮት አመንጪዋ ማን መሰለቻችሁ? ታዋቂዋ አውስትራሊያዊት ደራሲ ርሆንዳ ባይርኔ ናት፡፡ The secret እና The power የተባሉ መፃህፍቷን በሚሊዮን ቅጂዎች የቸበቸበችውን ደራሲ ማለቴ ነው፡፡

የአሜሪካ ትላልቅ ኩባንያዎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ስለትምህርት ደረጃቸው ምን ብለው ዋሹ?

ቀለም የዘለቃቸው ዋሾዎች ከፖለቲከኞችም ይብሳሉ ተባለ!

           ባለፈው ሳምንት የአብዛኞቹ ሚዲያዎቻችን ሰበር ዜና የሆኑት ግለሰብ ለዚህ “ልዩ ጽሑፍ” መሰናዳት ሰበብ እንደሆኑኝ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡(እውነቱን መናገር ይሻላል ብዬ እኮ ነው!) ምስጋናውን ለማን ማቅረብ እንዳለብኝ ግን እርግጠኛ ስላልሆንኩ ለጊዜው “የምስጋና ማዕቀብ” ማድረጉን መርጬአለሁ፡፡ እናም በቀጥታ ወደ ርዕሰ ጉዳያችን እንግባ፡፡ ዛሬ አምዱ ለዋሾዎች ተለቋል (ድሮስ የማን ነበር አትሉኝም?)
ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ምን ሰማሁ መሰላችሁ? እኚህ የትምህርት መረጃቸውን አስመልክቶ ዋሽተዋል የተባሉት ግለሰብ እንግዲህ አነቃቂ ንግግሮችን በማድረግ ይታወቃሉ አሉ ?! እናላችሁ ---- በሳቸው የማነቃቂያ ንግግር ተነሳስተው ለውጥ ያመጡ አንዳንድ ግለሰቦች በጣም ተናደዱ ተባለ፡፡ ለምን መሰላችሁ? የውሸት አነቃቅቶናል ብለው እኮ ነው።

Friday, June 20, 2014

አህያ ለምን ኩሊ ሆነ

አንዳንድ ጥያቄዎች በጣም አስቸጋሪ ናቸው ። ለምሳሌ አህያ ለምን ኩሊ ሆነ ተብዬ ተጠይቄ አውቃለሁ ። የሚገርመው ጥያቄውን የጠየቀኝ አንድ የ ሁለታኛ ክፍል ተማሪ ነው። እውነት እኮ ነ " እንደነዚህ ልጆች/ ሕጣናቶች ካላሰባችሁ መንግስተ ሰማያት አትገቡም " የተባለው። በይበልጥ እንደዚህ ልጅ ። ግን አህያ ለምን ኩሊ ሆነ ? ሌሎች የጋማ ከብቶች እንደ አህያ ለሸክም የሚመች ጀርባ ስለሌላቸው ወይስ አህያ ሸክምን የ አርባ ቀን እድሌ ነው ብሎ ተቀብሎት ? በ እሪት ዘፍጥረት አባትችን አዳም የእንስሳ ስም ያወጣ እንደነበር ታላቁ መጽሐፍ ይናገራል ። ምናልባት ለሚስቱ ስም ያወጣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ወንድ አዳም ይሆናል ። ( በዚህ ጉደኛ እና ሙደኛ ዓለም ላይ ስለ ብዙ ነገር እርግጠኛ መህን ባይቻልም)። ቢቻልስ ምንም የምትቀይረው ነገር የለም። ለምሳሌ የሰው ልጅ ስለ አየር ትንበያ ያለው እውቀት እየላቀ መምጣቱ አዳም ስም ሲሰይም ከነበረው የመጀመሪያ እውቀቱ ብዙ የራቀም አይደለም ።

ነገን ለማስተካካል ዛሬ ላይ መነጋገር…

ፈረንጆቹ ፣ “አንድ ክፉ ነገር አሸንፎ የሚወጣው በጥቂት ሰዎች ዝምታ ምክንያት ነው” የሚል አባባል አላቸው፡፡ በዚህ ድሀ ሕዝብ ጫንቃ ተምረው፣ ኑሮአቸውን ካደላደሉ በኋላ አገር አማን ነው ብለው ዝምታን መርጠው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፤ ቢያንስ የሕሊና ወቀሳ እንደሚነዘንዛቸው ሊክዱ አይችሉም፡፡ በዚህ አደገኛ ጊዜ ዝምታ ወርቅ ሳይሆን ክህደት ነው፡፡
--------
የችግራችን መፍትሄው ሁሉም ሊገባው በሚችልበት፣ በሁለት ቃላት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ይህን ያህል የዘር ጥላቻ ተካርሮ ወደ ግጭት ባላመራባት ኢትዮጵያ ቀርቶ፤ በዚያ በጥቂት ቀናት ውስጥ በዓለም ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እልቂት በተፈጸመባት ሩዋንዳ እንኳን፤ ዛሬ በህዝቡ መሀከል እርቅ ወርዶ ሩዋንዳ በአፍሪቃ የሰላምና የእኩልነት ተምሳሌት ለመሆን ችላለች፡፡ ዛሬ ሩዋንዳ እንጂ እከሌ ሁቱ ነው እገሌ ቱትሲ ነው ማለት አጸያፊ ሆኗል፡፡ ስለዚህ፤ ምንም እንኳን መጪዎቹ ጊዜያት አስፈሪ ቢሆኑም ቅሉ፤ ብሄራዊ እርቅ በሚሉ ሁለት ቃላት፣ መፍትሄ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡