Friday, February 6, 2015

የህወሓት ገመና ሲጋለጥ:- ሰብአዊ መብቶች ያልተከበሩበት የልማት ጎዳና ጥቅሙ ለጥቂቶች ብቻ ነው – አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

በማንኛውም አገር ቢሆን ድምፅ የሌለው፤ ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት፤ ወይንም በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎች የሌለው ሕዝብ መብት የለውም። መብቱ በመንግሥት የተከለከለ ግለሰብ ሆነ ቡድን፤ ማህበረሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት አይጎናፀፍም። ህወሓት ለሃያ አራት ዓመታት በበላይነት ሲገዛት የቆየች ኢትዮጵያ ፍትህ፤ ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት፤ በሕግ ፊት የሁሉም እትዮጱያዊያን እኩልነት የማይስተናገድባት፤ ፍፁም አምባገነናዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር ሆናለች። የህወሓት መስራቾች ስሌት መስራቾቹ ለሃያ ዓምስት ዓመታት፤ እነሱ ተንከባክበውና አስለጥነው፤ ልክ በፋብሪካ እንደተመረቱ “እቃዎች” የእነሱን ርእዮት፤ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት መስመር የሚከተሉ ተተኪዎቻቸው ዛሬ ሰላማዊ ሕዝብ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርግ በጅማል በዱላ እየደበደቡት ነው። ዲፕሎማቶችና ሌሎች ታዛቢዎች እያዩ፤ ባልቴት፤ ወጣት፤ ወንድ፤ ሴት፤ የክርስትና ወይንም የእስልምና ተከታይ፤ ኦሮሞ፤ ጉራጌ፤ አማራ፤ ትግሬ፤ ሳይለዩ እያሳደዱት፤ “እንደ እንሰሳ” በዱላ እየደበደቡት፤ እያፈኑትና እያሰሩት ነው።

ያልተቀደሰው ጋብቻ (ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ) -ጌታቸው ሺፈራው


(ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ)
ጌታቸው ሺፈራው
tplfበአንድ ወቅት ኢህአዴግ ‹‹የሚወዳደረኝ ተቃዋሚ ጠፋ›› ብሎ ቀልዶ ነበር፡፡ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ተበታትነው የነበሩት ተቃዋሚዎች ቅንጅትን ፈጥረው 1997 ምርጫ ላይ ሲያሸንፉት ደግሞ ቀልዱን ረስቶት ወደ ምርጫ የሚያመራውን መንገድ ሁሉ ለመዝጋት መታተር ያዘ፡፡ የፀረ ሽብር፣ የፕሬስ፣ የሲቪክ ማህበራት….አዋጆች ‹‹ከእኔ ጋር ለመወዳደር አቅም የላቸውም፡፡›› ይላቸው የነበሩትን ተቃዋሚዎች ወደ ምርጫ የሚያመሩበትን መንገድ የሚዘጉ መሰናክሎች ሆኑ፡፡ ያም ሆኖ ግን በእነ ኢዴፓ፣ የአየለ ጫሚሶው ‹‹ቅንጅት››ና መሰል ፓርቲዎች በመታጀብ ምርጫን ለይስሙላነት መጠቀሙን ቀጥሏል፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥ ሳያሸንፍም ቢሆን አሸንፈሃል የሚለው ‹‹ምርጫ ቦርድ›› ጋር እጅና ጓንቶ ሆኖ ይሰራል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ያልሆነውን ኢህአዴግን ብቸኛ አማራጭነ አድርገው የሚያቀርት ኢቲቪና ፋና አሉ፡፡ ሚዲያና ምርጫ ቦርድ ኢህአዴግ በተቃዋሚዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች በማንሳት ተቃዋሚዎችን በህዝብ አይን ማሳነስ ዋነኛ ስራቸው ሆኗል፡፡ በተለይ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ ሆነው በአንድነት በተቃዋሚዎች ላይ መዝመታቸው የተለመደ ነው፡፡

በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ መከረ

ህብረቱ ጥር 27፣2007 ዓም በብራሰልስ ቤልጂየም የአውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ውስጥ ለ3 ሰአታት ባደረገው የኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ግምገማ በኦጋዴን ክልል እና በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃ የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታት በዝምታ መመልከታቸውን ማብቃት አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፈዋል። ስብሰባውን ያዘጋጁት የህብረቱ የሶሻሊስትና የዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ጥምር ህብረት ፣ ውክልና አልባ ህዝቦች ተቆርቋሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው።

ህልም እንደ ፈቺዉ ነዉ – ሰመረ አለሙ

tplfአንዳንዴ አያድርስ ነዉ ነገር በየት በኩል እንደሚያፈተልክ አይታወቅም:: ኢትዮጵያ የምትወጋበትንም ሆነ የምትወጋበትን የጦር መሳሪያ ህወአት እየገዛ ለኤርትራ የሚያቀብለዉ ደባ ያልጣመዉ አንድ ወዳጂ በቅርቡ ወደ ኤርትራ በተወሰደዉ አንጀት አርስ ሄሊኮፕተር MI 35 ምክንያት ሲበሳጭ እኔም ያማደርገዉ ባጣ ብስጭት ጥቅም የለዉም መላ መፈለግ ነዉ ብዬ ብመክረዉም የዜግነት ግዴታህ እስከዚህ ድረስ ነዉ በማለት በንቀት ተመልክቶኝ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ይዞ ተሰወረ።  ይህ መሳሪያን የሚያከበር  ትንታግ የሆነ የቀድሞ የአየር ወለድ ባልደረባ የእሱ መንገድ ከኔዉ  የተለየ ሁኖ ዉስጥ ዉስጡን ሲሰራ ቆይቶ በሀገር ፍቅር ሰሜት ልባቸዉ የነደደ ከዘር እና ሀይማኖት በላይ ዘራቸዉና እምነታቸዉ ኢትዮጵያዊ የሆነ በደግነት፤በጀግንነት፤በቆራጥነት መስፈርት ጣራዉን የነኩ በቅርብ የሚያዉቃቸዉን የ50 አለቃ ስንሻዉ በላይነህን፤ የ10 አለቃ ጣፋ ኢዶሳን፤ ቆራሄ ላይ በተደረገዉ ጦርነት ቦታዉን ሳይለቅ ለኢትዮጵያ ሀገሩ ሰማእት ስለሆነዉ ስለ ደጃዝማች አፈወርቅ አባቱ ዘወትር ሲተርኩለትና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ እያነጹ ያሳደጉት የሀረሩ መምህር አብዱረህማን ኡስማን፤ በትምህርት ደረጃዉ እና በሀገር መዉደድ ስሜቱ የሚነገረለት ዘለቀ ማንደፍሮ፤ ከትግራይ የፈለቁ ጉዶች ኢትዮጵያ ላይ እንዲህ ያለ በደል ሲያደርሱ ቁጭቱን ለመወጣት ቀን ሲጠብቅ የነበረዉ የራስ አሉላ የልጅ ልጂ ነዉ ተብሎ የሚነገርለት ገ/መድህን ወ/ኢትዮጵያን ያካተተ በአካል ጥንካሬዉ፤ በወገን አፍቃሪነቱ ፤በሩቅ እይታዉ የታመነበት በኮማንዶ ቡድን መሪዉ በጌታቸዉ አበጋዝ አማካይነት በስዉር ምልመላ እና ስልጠና በማድረግ 150 አባላቱን በጥንቃቄ በ3 ቦታ በመክፈል በተለያየ ጊዜ ወደ ትግራይ ልኮ ሁኔታዉን ሲያዳምጥ ቆየ።

የትግራይ ነጻ አውጪዎች ኢትዮጵያን ማጥፋት ይችላሉን – ከሳሙኤል አሊ

ነብር ዠጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊቀይር አይችልም ይላል በታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ። ይህ ቃል የኔ ወይም የናንተ አልያም የወያኔዎች ቃል አይደለም ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ሁሉን ማድረግ የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ኢትዮጵያዊ መልኩን ኢትዮጵያዊነትም ሊቀየር አይችልም ይላል እግዚአብሔር። ታዲያ  ወያኔ  ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳው ከምን ተነስቶ ነው? የሰው ልጅ መጋፋት የሚቻለው ከሰው ጋር ሊሆን ይችላል ወያኔ ግን ከፈጣሪ ዘንድ ነውና ኢትዮጵያን ማጥፋት ከቶውኑ አይችልም። ወያኔዎች ኢትዮጵያዊ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቁ አልመሰለኝም። አዎ ኢትዮጵያዊ ማለት እግዚአብሔር የመረጣት አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ህዝብ የሚኖርባት መሬት.. በህገ ልቦና ገና  ህግ ሳይሰራ  ሊቀ ነብያት ሙሴም ህግን ከእግዚአብሔር ሳይቀበል በፊት እግዚአብሔርን በማምለክ የኖረች አገር ነች።

የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደር ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታውን እንዲመልስ እየጠየቁ ነው

• ‹‹ከምርጫው በኋላ ይመለስላችኋል ተብለናል›› አርሶ አደሮቹ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን እንዲመልሱ እያሳሰቡ መሆኑን አርሶ አደሮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ከወራት በፊት ጀምሮ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ሲጠይቁ እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሮቹ፤ አሁን ምርጫው መቃረቡን ተክትሎ ካድሬዎች ቤት ለቤትና ስብሰባ ላይ ከሚናገሩት በተጨማሪ በየ ቤተክርስቲያኑም አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል!

ህወሓት ንፁሀንን ለመደብደብ የሚያበቃ በቂ ክፋት ያለው ልዩ ጦር ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ልዩ ጦር የፓሊስን መለያ እያለበሰ ነውረኛ ሥራዎችን እንዲሠራ በማድረግ በአንድ በኩል ንፁሀንን የመጉዳት በሌላ በኩል ደግሞ ፓሊስን በሕዝብ የማስጠላት መንታ ግቦችን ለማሳካት ተጠቅሞበታል። ይህ ልዩ ጦር በአለፉት ጥቂት ሳምንታት ባዶ እጃቸው ለተቃውሞ በወጡ ነብሰ ጡር ሴቶች ላይ ሳይቀር ባሳየው ጭካኔ፣ በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ባደረሰው ድብደባ መጠን እና ባካሄደው የግለሰብ ንብረቶች ዝርፊያ የሥርዓቱ ባህርይ ፈጽሞ ከሰውኛ ተፈጥሮ እየወጣ እንደሆነ አመላካች ነው። በእነዚህ ድብደባዎች ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጓል።