Friday, February 6, 2015

የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደር ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታውን እንዲመልስ እየጠየቁ ነው

• ‹‹ከምርጫው በኋላ ይመለስላችኋል ተብለናል›› አርሶ አደሮቹ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን እንዲመልሱ እያሳሰቡ መሆኑን አርሶ አደሮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ከወራት በፊት ጀምሮ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ሲጠይቁ እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሮቹ፤ አሁን ምርጫው መቃረቡን ተክትሎ ካድሬዎች ቤት ለቤትና ስብሰባ ላይ ከሚናገሩት በተጨማሪ በየ ቤተክርስቲያኑም አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብለዋል፡፡
አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ የሚጠይቁት ካድሬዎች ‹‹የእርሻ መሬት ካርታ ውስጥ ሊካተት ስለሆነ ነው፣ በህገ ወጥ መንገድ የግጦሽ መሬት የሚያርሱ ስላሉ ነው፣ መሬት ይዞታ ላይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች አሉ….›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እንደሚሰጡ የገለጹት አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን የማስረከብ ግዴታ እንዳለባቸውና ከምርጫ በኋላ እንደሚመለስ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ ምርጫ በተቃረበበት ወቅት የመሬት ይዞታ ደብተር መሰብሰቡና ከምርጫ በኋላ ይመለስላችኋል መባሉ በመጭው ምርጫ ኢህአዴግን አይመርጡም ተብለው በሚታሰቡት አርሶ አደሮች ላይ ፍርሓትና ጫና ለመፍጠር ሳይሆን እንዳልቀረም አርሶ አደሮቹ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38756#sthash.9GKLViVf.dpuf

No comments:

Post a Comment