ቀና በል ይሉኛል– ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ በየት በኩል ልሙት::
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው ወዴት ልሸሽገው?
ዞትር የሚስቁት፣
ወዴት ገቡ አበቦች
የሚፍለቀለቁት የታሉ ኮከቦች
ምን አጋይቶት ይሆን፤ ሰማይ የከሠለ
ምን ነካው ደመናው፤ ኩበት የመሠለ
አስፋልቱስ የት ሄደ
የተለጠለጠው
ወንዙስ ተሰደደ?
ድልድዩስ ምን ዋጠው
የት ተነነ ጫካው
የት መነነ ዋርካው
በለምለም ጣቶቹ፤
ሰማይ የሚነካው
ዳበስኩኝ ፈተሸኩኝ
መረመርሁኝ ካርታ
አገሬን አጣሁዋት፤
ባስቀመጥሁዋት ቦታ፡፡
ኢትዮጵያ እመ-መከራ
የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ…
ወዴት ገቡ አበቦች
የሚፍለቀለቁት የታሉ ኮከቦች
ምን አጋይቶት ይሆን፤ ሰማይ የከሠለ
ምን ነካው ደመናው፤ ኩበት የመሠለ
አስፋልቱስ የት ሄደ
የተለጠለጠው
ወንዙስ ተሰደደ?
ድልድዩስ ምን ዋጠው
የት ተነነ ጫካው
የት መነነ ዋርካው
በለምለም ጣቶቹ፤
ሰማይ የሚነካው
ዳበስኩኝ ፈተሸኩኝ
መረመርሁኝ ካርታ
አገሬን አጣሁዋት፤
ባስቀመጥሁዋት ቦታ፡፡
ኢትዮጵያ እመ-መከራ
የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ…
No comments:
Post a Comment