ከትናንት በስቲያ በኬኒያ ታሲያ በተባለ ግዛት መያዛቸው የተነገረው 101 ኢትዮጲያዊያኑን ስደተኞች በህደገወጥ መንገድ ወደኬኒያ ገብተዋል በሚል እስከ 50 ሺህ የኬኒያ ሽልንግ ቅጣት ተጣለባቸው፡፡ ኢትዮጲያዊያኑ ቅጣቱን ካልከፈሉ የአንድ አመት እስር ይጠብቃቸዋል ሲል ነው የኬኒያው እለታዊ ዴይሊ ኔሽን የጻፈው፡፡
ከኢትዮጲያዊያኑ ጋር ሶስት ኬንያዊያንም ፍርድ ቤት ቀርበው ለቅጣት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡ ኢትዮጲያዊያኑ ቅጣታቸውን እንደጨረሱ ወደሀገራቸው ይጋዛሉ።
============= ወይኔ የሀገር ሰው ኬንያም በኛ ላይ እንዲህ ትዛበትብን ።
ባለቤት ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም የሚባለው ተረት እንዲህ ነው ።
የኢትዮጵያውያን ሞት
የኢትዮጵያውያን ስደት ባሁኑ ጊዜ እንኳ ለማይመለከተው ለባዕዳን ለኛው ለራሳችን የተለማመድነው ከዓምላክ የወረደብን ነው ብለን የተቀበልነው ይመስላል ። በቁጭት ለምን ብለን ራሳችን አንጠይቅም ።
ማነው የሚሰደድ ፣ ?
ማነው የሚያሰድድ ?
ብለን ጠይቀናል?
============= ወይኔ የሀገር ሰው ኬንያም በኛ ላይ እንዲህ ትዛበትብን ።
ባለቤት ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም የሚባለው ተረት እንዲህ ነው ።
የኢትዮጵያውያን ሞት
የኢትዮጵያውያን ስደት ባሁኑ ጊዜ እንኳ ለማይመለከተው ለባዕዳን ለኛው ለራሳችን የተለማመድነው ከዓምላክ የወረደብን ነው ብለን የተቀበልነው ይመስላል ። በቁጭት ለምን ብለን ራሳችን አንጠይቅም ።
ማነው የሚሰደድ ፣ ?
ማነው የሚያሰድድ ?
ብለን ጠይቀናል?
አንድ ትልቅ ነገር ሚስ ያደረግነው አለ: —
እሱም በሀገር ውስጥ መሰደድ አንችልም ። በሀገር ቤት መሰደድ የሚለው ትንሽ ግራ ያጋባል ባለፉት ዘመናት በተወለዱበት አካባቢ ሰርተህ ካላለፈልህ አካባቢ ለቀህ የፈለገውን የሥራ ዓይነት ሰርተህ ያልፍልሀል ። ይህ አሁን የለም የዘርና የጎሳ አጥር ተቀምጦልሀል በየክልሉ የጎሳ ሹሞች የኬንያ ፖሊሶች የአረብ ፖሊሶች ከሚያደርሱብህ በላይ ያለርህራሄ ይበድሉሀል ።
ግድያን የጨመረ መረን የለቀቀ የጎሳ ጥላቻ በስልጠና ወስደዋል ከመሀል አገር ሂደህ ሀረርና ጅጅጋ ብትገኝ ምን እንደሚጠብቅ ታውቃለህ በሌሎችም ክልል ብትሄድ ተመሳሳይ ዕጣ ነው የሚጠብቅህ ሁሉም የክልል መስተዳድር ከበስተጀርባ የሚዘወረው በሥውሩ መንግሥት ነው ።
ስለዚህ በሀገር ውስጥ የከፋና ተስፋ አስቆራጭ አገዛዝ እስካልተወገደ ድረስ ከሞት ጋርም ሁኖ ከሀገር መውጣቱ ይቀጥላል ።
ግን መፍትሄ አደለም መፍትሄው በእጅህ ነው አገርክን ታግለህ ወዳንተ መመለስ ነው ።
መንግሥት የለህም አገርም የለህም ላንተ የሚያስብ ወይም መብት የሚያስከብርልህ ያለዜግነት መብት ያለመንግሥት 24 ዓመት ሆነህ ።
No comments:
Post a Comment